2017-03-23 10:16:00

"ክርስቲያኖች ተስፋን ሊዘሩ ያስፈልጋል" ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ዘወትር ርዕቡ እና እሁድ እለት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ አስተምህሮ እንደ ምያስተላልፉ ያታወቃል። በዛሬው እለትም ማለትም በመጋቢት 22/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ይህንን ቅዱስነታቸው የሚያስተላለፉትን የጠቅላላ አስተምህሮ ለመከታተል ለተገኙ የሀገር ጎብኝዎች እና ምዕመናን ያስተላለፉት አስተምህሮ ከዚህ በፊት በተከታታይ የክርስቲያን ተስፋ በሚል አርእስት ያደረጉት የነበረው አስተምህሮ ቀጣይ ክፍል እንደ ነበረም ለመረዳት ተችሉዋል።

የዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በዛሬው አስተምህሮዋቸው እንደ ገለጹት ከጥቂት ሣምንታት በፊት ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ የክርስቲያን ተስፋ ምን ማለት እንደ ሆነ በጥልቀ እንድንረዳ ረድቶን ነበር። ዛሬ ደግሞ ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ሕይወታችን እና እምነታችንን እንድንለማመድ በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ጽናት እና መጽናናት የሚባሉ ሁለት ባሕሪያትን ያቀርብልናልበማለት አስተምህሮዋቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው ዛሬ ባዳመጥነው ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክት ውስጥ እንደ ተጠቀሰው ጽናት እና መጽናናት የሚሉት ቃላት ሁለት ጊዜ ተጠቅሰው እናገኛለን ካሉ ቡኃላ የመጀመሪያው ከመልእክቱ ጋር ተያያዥነት ባለው መልኩ የተጠቀሰ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ከእግዚኣብሔር ራሱ ጋር በተዛመደ መልኩ የተጠቀሰው መሆኑን ቅዱስነታቸው አብራርተዋል።

ታዲያ የነዚህ ሁለት ባሕሪያት ማለትም ጽናት እና መጽናናት የሚሉት ቃላት ጥልቅ እና እውነተኛ ትርጉማቸው ምንድነው? በምን ዓይነት መንገድ ነው የተስፋን እውነተኛነት እንድንረዳ ብርሃን የሚሆኑን? በማለት ጥያቄን ማንሳታቸውም ተገልጹዋል።

“ጽናት የሚለውን ቃል ትዕግስት ማድረግ ማለት እንደ ሆነ አድርገን መተርጎም ወይም መውሰድ እንችላለን፣ አንድን ነገር የመቋቋም ችሎታ፣ በትክሻችን ነገሮችን በመሸከም፣ ታማኝ ሆነን መኖር፣ ምንም እንኳን አንድ አንዴ ሽክማችንን በጣም የሚከብድ ቢሆንና ልንቋቋመው የማንችለው አይነት ቢሆንም፣ በዚህም የተነሳ አሉታዊ በሆነ መልኩ ፈትናዎች ቢደርሱብንና ውሳኔ ብናደርግም ጽናት እነዚህን ነገሮች ሁሉ እርግፉ አርጎ በመተው ወደ ፊት መጓዝ ማለት ነው” ብለዋል።

“መጽናናት የሚለው ቃል ግን በማኛውም ሁኔታ እና አጋጣሚ የሚገጥሙንን ነገሮች ሁሉ በፀጋ መቀበል ማለት ነው” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ተስፋ በምንቆርጥባቸው እና በስቃይ ወስጥ በምንገኝባቸው ወቅቶች ሁሉ እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር መሆኑን እና እርሱ በምሕረቱ እንደ ሚጎበኘን አምኖ መቀበል ማለት ነው ብለዋል።

“ዛሬ ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ እነዚህን ጽናት እና መጽናናት የሚሉት  ሁለት ባሕሪያት ለየት ባለ ሁኔታ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካይነት መረዳት እንደ ምንችል ያስታውሰናል” ያሉት ቅዱስነታቸው እርግጥ ነው የእግዚኣብሔር ቃል በቀዳሚነት በኢየሲስ ላይ እይታችንን እንድናደርግ ያስተምረናል ካሉ ቡኃላ በሚገባ ኢየሱስን እንድናውቀው እና ሁል ጊዜ እርሱን በመምሰል እንድንኖር ያስተምረናል ብለዋል።

በሁለተኛ ደረጃ የእግዚኣብሔር ቃል ጌታ በእውነት “የመጽናትና የመጽናናት” አምላክ መሆኑን ይገልጽልናል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ጌታ ሁል ጊዜ በፍቅሩ ለኛ ታማኝ ሆኖ፣ በጽናትና በፍቅሩ ከእኛ ጋር በመሆን ቁስላችንንም በመልካምነቱና በምሕረቱ በመዳሰስ መጽናናትን ይሰጠናል ብለዋል።

“ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ! እግዚኣብሔር ለሚያደርግልን መልካም ነገሮች ሁሉ ቃሉ በምያዘን አጠን የሚገባውን ያህል ምስጋና ችረነው አናውቅም ያሉት ቅዱስነታቸው መጽሐፍ ቅዱሳችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “የጽናት እና የመጽናናት አምላክ” እንደ ሆነ አድርጎ ያቀርበዋል ካሉ ቡኃላ በዚህም ምክንያት የእኛ ተስፋ የሚመነጨው ከራሳችን ብርታትና ኃይል ሳይሆን በእግዚኣብሔር ፍቅር በመታመን በአጠቃላይም በእግዚኣብሔር ኃይልና በእግዚኣብሔር ጽናት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።  

 








All the contents on this site are copyrighted ©.