2017-03-22 16:39:00

ሁለተኛ ስብከት ዘዓቢይ ጾም፥ መለኰተ ክርስቶስ የእምነት ማእከል ነው


የካፑቺን ንኡሳን አኃው ማኅበር አባል ሰባኬ ቤተ ጳጳስ አባ ራኒየሮ ካንታላመሳ እ.ኤ.አ. መጋቢት 18 ቀን 2017 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና መላ የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የበላይ ጳጳሳዊ አቢያተ ምክር እንዲሁም ቅዱሳን ማኅበራት ሊቀ መናብርትንና ኅየንተዎችን ያሳተፈው በሐዋርያዊ መንበር በሚገኘው እመ መድኃኔ ዓለም ቤተ ጸሎት የዓቢይ ጾም ሁለተኛ ስብከት ማቅረባቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ ገለጡ።

አባ ካንታላመሳ እ.ኤ.አ. መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. “በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ ካልሆነ በስተቀር ‘ኢየሱስ ጌታ ነው’ የሚል እንደሌለ እነግራችኋለሁ” (1ቆር. 12,3) በማለት አስምረውበት ከነበረው ሃሳብ በመንደርደር የመጋቢት 18 ቀን ስብከታቸውን ሲያቀርቡ፥ ከጥንት ጀምሮ በዚያ የድህነት ምንጭ የሆነው በክርስቶስ መለኰታዊነት ላይ ያጸናው የቤተ ክርስቲያን እምነት በማስታወስ ለእያንዳንዱ ክርስቲያን እምነት ማለት ምን ማለት ነው? የሚል ጥያቄ በማንሳት፡ በዚያ የኒቅያ የማይለወጥና የማይሻር በማለት ያሰፈረው ጠመቅ ውሳኔ ላይ ተንተርሰው፡ “ለአብ አንድያ ልጁ በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አናምናለን” ብለን ለማረጋገጥ ከአብ ጋር የሚስተካከል ሁሉ በእርሱ ለሆነው ኢየሱስ አምልኰና ስግደት ለማቅረብ የመጽሓፍ ቅዱስ እና የአይሁድ ባህል ለብቻው በቂ መሠረት ነው። ሆኖም ይኽ “በአንድያው በአብ ልጅ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን” የሚለው የኒቅያው ውሳኔ በዚያ በተለያዩ ብዙ ጌቶች ለሚያመልክ በግሪከ ሮማዊ አረሜን ባህል ውስጥ ይኖር ለነበረው አረማዊ ሕዝብ እጅግ አስፈላጊ ነበር። ይኽ አንቀጸ እምነት ለገዛ እራሱ አዲስ ግኝት አልነበረም። ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን ከጥንት ጀምራ በክርስቶስ መለኰታዊነት እምነት ነበራትና። ስለዚህ የኒቅያ አበው በዚያ በጠመቅ ሃይማኖታዊ ትምህርት ውሳኔ አማካኝነት በክርስቶስ መለኰታዊነት አምናለሁኝ የሚለውን የቤተ ክርስቲያን እምነት ለሚያሰናክሉና ይፈጸሙ የነበሩትን ድንግርግሮችን ሁሉ ለምሳሌ በግሪካዊ ባህል “መለኰታዊ ባህርይ አይወለድም” የሚለውና ይኸንን መሳይ ትምህርቶችን ለማስወገድ ያለመ ነበር። የክርስትናው እምነት “ወልድ፥ ከእውነተኛው አምላክ የተወለደ፤ በእግዚአብሔርና በፍጥረት ዘንድ የሚያገናኝ ወይን አስታራቂ መለኰት”  መሆኑ የሚያረጋግጥ ነው።

“የኒቂያው የእምነት ውሳኔ በሁሉ ባህልና በሁሉም ዘመናት ክርስቶስ ‘እግዚአብሔር’ ተብሎ እንዲታወጅ ሲያሳብ ተያይዞ የሚመጣ ወይንም የሚመነጭ በሁለተኛ ደረጃ የሚቀመጥ አለ መሆኑ አስተውል ለማለት ነው። በቲዮሎጊያዊው ክርክር አታናስዮስና ሌሎች ጥበብቃውያን ማለትም ወግ-ጠበቅ ቲዮሎጊያውያን ይኸንን ሃሳብ ማመንጨት የሚችሉት ከማውጣትና ከማውረድ ወይን ከመመራመር ብቃት ሳይሆን የሕይወት የቤተ ክርስቲያን ተመክሮ በማስተንተን ነው። ይኽ ደግሞ ድህነት በኢየሱስ ክርስቶ መሆኑ የሚያረጋግጥ የመንፈስ ቅዱስ ተግባር ነው”

ክርስቲያናዊ እምነት ይላሉ አባ ካንታላመሳ፥ “የክርስቶስ መለኰታዊነትን የሚያምን ነው”  ይኽ እምነት ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስ በክርስቲያን ማኅበርሰብና በማኅበረ ክርስቲያን ያለውና የሚሰጠው ቦታ ምን ይመስላል፡ ምን ዓይነት ቦታ ነው የሚሰጠው? የሚለውን ጥያቄ አንስተው ስለዚሁ ጉዳይ በባህል በተለያዩ መጻሕፍትና በኪነ ፊልም ደረጃ ብዙ ይነገራል ይባላልም ብለው፥ 

“ሆኖም በእምነት ደረጃ ስንመለከት ብዙውን ግዜ የሚዘነጋና የሚያውክ መዘንጋት ከመሆን አልፎ የማግለል አዝማሚያ ይታያል። በስነ ጽሑፍ በድርሰትና በኪነ ፊልም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ብዙ እየተባለ ነገር ግን በሕይወታችን ሲዘነጋ ይታያል። ቦታ የማይሰጠው ህላዌ ይሆናል። በኤውሮጳ አማኒያን ነን የሚሉ እምነታቸው ምን ላይ ነው የሚያጸኑት? ባጠቃላይ በአንድ ልዑል የላቀ ህልወተ ኃይል - አንድ የላቀ ኃይል አለ ብሎ ማመን ላይ እንጂ ክርስቲያናዊ እምነት ጋር ምንም የሚያገናኝ የለውም። ይኽ  አይነቱ አዝማሚያ ማለትም በአንድ የላቀ ኃይል ላይ የሚኖር እማኔ ለገዛ እራሱ ብዙ የሥነ-ማኅበራዊ አጥኚዎች እንደሚሉት ባለፈው ጥንታዊ ዘመን ከክርስትና እምነት ጋር የተቀላቀለ ዝምባሌ እንደነበር ይናገራሉ። እንዲህ ባለ እምነት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ይዘነጋል።”

በክርስቶስ መለኰታዊነት ላይ እምነትን የመፈለጉ ጉዳይ ካለ ምንም መጠራጠር በሙላት አስፈላጊ ነው። ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፡ መንገድ ሓቅና ሕይወት ነኝ” ብሏል። እኛ በወቅታዊው ዓለም፥ “ያንን እናንተ ሳታውቁት ነገር ግን የምትፈልጉትን ማን መሆኑ እናበስራችኋለን”  ያንን ሳይረዱት የሚፈልጉት ማን መሆኑ ለማበሰር የተጠራን ነን ያሉት አባ ካንታላመሳ አያይዘው፥ ኢየሱስም “ያ እናንተ የምታዩትን የሚያዩ ብፁዓን ናቸው” ያዩት ለእነዚያ ላላዩት በማበሰር እነሱ ባዩት እውነት ላይ እንዲያምኑና ያዩትን ሌሎች በእምነት እንዲያዩ ያደርጋሉ። ይኽ ደግሞ ሳያዩ የሚያምኑትን ብፁዓን የሚያደርጋቸው እምነት ነው እንዳሉ የቫቲካን ርዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ማሶቲ አስታውቋል።

አባ ካንታላመሳ ያቀረቡት ሁለተኛው የዓቢይ ጾም ስብከት ሲያጠቃልሉ፥

“እኛ አማንያን በክርስቶስ የምናምን መሆናችን የማናስተነትን ከሆን እንድግዲህ ተለውጠንና መልስ ብለን የምናስተነትንበት ወቅት ደርሷል። ማኅበረ ክርስቲያን ከሌሎች በላይ ደስተኞች የሚያደርጋቸው ነገር ከሌላቸው እንዴት ብለው ብፁዓን ሊባሉ ይችላሉና? ለምንስ ብዙዎች በተለያየ የዓለማችን ክልሎች በክርስቶስ ላይ ባላቸው እምነት ምክንያት የሚገደሉት? ለዚህ ጥያቄ መልስ ኢየሱስ እንደ ሚለውም፥  … ስላያችሁና የሕይወትና የሞትንም ትርጉም ስለ ተረዳችሁ ‘የእግዚአብሔር መንግሥት የናንተ ነው!’ … ማለት ገና ቀደም ተብሎ የእግዚአብሔር መንግሥት አባላት እንድትሆኑ ተደርጓልና የዚህ ቀዳሚ መሆናችሁንም ገና ከወዲሁ እያጣጣማችሁት ትገኛላችሁ። እኔ ያለሁላችሁ ናችሁ። በእውነት ይኽ አለሁልህ አለሁልሽ የሚለው ቃል እንዲት ሙሽራ ከሙሽራዋ እንድ ምሽራ ከሙሽራይቱ የሚጠበቅ ቃልና ተግባር ነው። ይኽ ነው ደስተኛ የሚያደርገው። ኢየሱስ እንዲህ የምትለውና ሙሽራ የምትሆነው ቤተ ክርስቲያን የሚገባው ነው። ተገቢዎቹና የሚገቡት እንሁንለት። ኢየሱስ ደስተኞች እንደሚያደርገን የሚሰማቸው ካልሆንን በእርሱ ደስተኞች እንዳንሆን የሚያሰናክለን ሁሉ ምን ይሆን ብለን ለመለየት ገዛ እራሳችንን እንመርምር”

 እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ አድሪያና ማሶቲ አስታውቋል።   








All the contents on this site are copyrighted ©.