2017-03-19 16:01:00

ቅዱስነታቸው በጠቅላላ አስተምህሮዋቸው "ዓብይ ጾም ወደ ክርስቶስ የምንቀርበት አጋጣሚን የሚፍጥርልን ወቅት ነው" አሉ።


“ምን አልባት ኢየሱስን በግል ሕይወታችን እስከ ዛሬ አግኝተነው የማንውቅ ከሆነ፣ ኢየሱስን የእኛ አዳኝ አድርገነው ልንቆጥር አንችልም”። ይህ ቀደም ሲል የተጠቀሰው ሀረፍተ ነገር ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በመጋቢት 10/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ አስተምህሮን ለመከታተል ለተሰብሰቡት ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ካስተላለፉት አስተምህሮ የተቀነጨበ ነው።

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አስተምህሮ በእለቱ እንደ የላቲን ስርዓተ አምልኮ አቆጣጠር በሦስተኛው የዓብይ ጾም ሳምንት ሰንበት በተለበበውና ከዩሐንስ ወንጌል 4:5-42 ላይ በተወሰደው የኢየሱስ እና የሳምራዊቱዋ ሴት ውይይት ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን ምንም እንኳን ይቺህ ሴት ከሳምራዊያን ወገን የሆነች  ሴት ብትሆንም ቅሉ ኢየሱስ ከዚህች ሳምራዊት ሴት ጋር አድርጎት የነበረው ውይይት በታላቅ አክብሮት ላይ የተመሰረተ እንደነበረ ጠቅሰው ምንም እንኳን ይቺህ ሴት የተመሰቃቀለ ሕይወት የነበራት ሴት ብትሆንም ኢየሱስ ስለ እውነተኛ እምነት ይነግራት የነበረውን ቃል ግን ለመስማት ዝግጁ ነበረች ብለዋል።

እሷ ኢየሱስ ነብይ መሆኑን እውቅና ስጥታው ነበር፣ መሲሕ ሊሆን ይችላል የሚልም ግምት ነበራት ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንን ጥርጣሬዋን ለማስወገድ በማሰብ ኢየሱስ እርሱ ነቢይ መሆኑን በቀጥታ ነግሩዋት ነበር ካሉ ቡኋላ በእርግጥ እርሱ መሲሕ ነው ይህም በወንጌል ውስጥ አንድ አንዴ የሚገኝ እውነታ ነው ብለዋል።

“ውድ ወንድሞቼ ሆይ፣ የዘላለም ሕይወት የሚሰጠን ውሃ በጥምቀታችን ወቅት በልባችን ውስጥ ፈሱዋል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በዚያው የጥምቀታችን ቀን እግዚኣብሔር ማንነታችንን ለውጦ በፀጋው ሞልቶናል ብለዋል። ነገር ግን እኛ አንድ አንዴ በጥምቀት የተቀበልነውን ፀጋ እንዘነጋለን በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም በምናደርግበት ወቅት ሁሉ ጥማችንን ሊቆርጥ የማይችለውን የውሃ ጉድጓድ ፍለጋ እንኳትናለን በዚህም ምክንያት ያዛሬው ወንጌል የሚምለለከተው ከሰማሪያ ወገን የሆነችሁን ሴት ብቻ ሳይሆን የእኛንም ሕይወት የሚዳስስ እና የሚመለከት የወንጌል ክፍል ነው ብለዋል።

ይህ የዓብይ ጾም ወቅት ወደ ኢየሱስ እንድንጠጋ የሚያደርገን መልካም አጋጣሚ ነው በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም አጋጣሚ ተጠቅመን በጸሎት አማካይነት ከኢየሱስ ጋር ልብ-ለልብ የምንወያይበት፣  ፊት ለፊት የምንተያይበት በተለይም በችግር ውስጥ የሚገኙትን ወንድም እና እህቶቻችንን የምንጎበኝበት ወቅት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

በዚህ መንገድ ብቻ ነው በጥምቀት የተቀበልነውን ፀጋ ማደስ፣ ለእግዚኣብሔር ቃልና ለመንፈስ ቅዱስ ያለንን ጥማት ማርካት የምንችለው ያሉት ቅዱስነታቸው በዚህም የተነሳ ዘወትር በሕይወታችን የእርቅ እና የሰላም መሳሪያና ተዋናይ መሆን እንችላለን ካሉ ቡኃላ ለእለቱ ያዘጋጁትን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.