2017-03-10 16:14:00

የሰባተኛው ቀን ሱባኤ አስተንትኖ፤ አባ ሚከሊኒ፥ የኢየሱስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ መሞት እንቅፋት ነው


በአቢይ ጾም ምክንያት ቅዱስ አባታችንና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት አቢያተ መማክርት ሊቀ መናብርት የቅዱስን ማኅበራትና አቢያተ ዋና ጸሓፍት ህየንተዎች ብፅዓን ካርዲናሎች ጳጳሳትና የኔታዎችን በማሳተፍ እ.ኤ.አ. መጋቢት 5 ቀን ሮማ አቅራቢያ አሪቻ ከተማ በሚገኘው መለኮታዊ መምህር የሱባኤ ቤት የተጀመረው እ.ኤ.አ. መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዚጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

እ.ኤ.አ. መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የተካሄደው ሰባተኛው አስተንትኖ“ለስርየተ ኃጢአት” ከኢየሱስ ጎን ውኃና ደም ፈሷል የሚለውን ሃሳብ ያማከለ አባ ጁሊዮ ሚከሊኒ ጧት በሰጡት ቃለ አስተንትኖ ስቁል ኢየሱስን “በጥልቅ ፍቅር መመልከት”  ያለው አስፈላጊነት አበክረው በወንጌለ ማቴዎስ የመሲሕ ሞት ላይ አስረግጠው፡ በተለይ የመሲሕ ሞት “ተጨባጭ” እንጂ “ለይምሰል” አይደለም እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ አስታውቋል።

“ከሞት ተነስቶ መምጣቱንም ደቀ መዛሙርት ብቻ ሳይሆኑ ብዙዎች ለማመኑ ያዳግታቿል፡ ተንስቷል ብለው ለማመን ይከብዳቿል፡ መሞቱን ሳይሆን መነሳቱን ነው ያላመኑት፡ ይኽ ደግሞ በእውነት እንደ ሞተ የሚያረጋግጥ ጉዳይ ነው፡ የሞተ ሰው እንዴትስ ይነሣል? ነውና ጥያቄአቸው” የኢየሱስ መሞት የሚገልጡ ዝርዝር ሁኔታዎች “አያመቹም መሰናክል ናቸው”  ለምሳሌ “አንድ ነገር እንቀፋት የሚያስብለው መመዘኛዎች” ሁኔታው በትክክልና ክውንነቱ የተረጋገጠ እውነት በመሆኑ”  እንጂ ልበ ወለድ ወይንም የሰው ልጅ አእምሮ ያልፈጠረው ሁነት አለ መሆኑ ከመስቀል ላይ ሆኖ ወደ ኣባቱ ሲጮኽ ተሰምቷል። “እየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ የኖረው የመሞትና ለብቻ የመቅረት ሁነት” በጥልቀት መተንተን ያለበት ጉዳይ ነው። “አባቴ ሆይ አባቴ ሆይ ለምን ተውከኝ እያለ ሲጮኽ፡ ሲሰቀልና በመስቀል ላይ የመዋሉ ጭካኔ የተሞላበትን ትርኢት ያዩ የነበሩት ሁሉ ለመረዳቱ ያዳግታቿል”  ይባስም ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ ሲል አይ ኤሊያስን እየጠራ ነው ብለው ነው የገለጡት፡

“ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ማን ቢሆን ነው ኤሊያስን የሚጣራው? ኤሊያስን የሚጠራው ከመስቀል እንዲያወርደው ነውን፡ ኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ የሚጣራው ኤሊያስን ነው ወይንም መጥመቁ ዮሐንስን ነው? በእርግጥ ኢየሱስ የሚጠራው የኤሊያስ ወይንም የመጥመቁ እርዳታ ሳይሆን አባቱን ነው የሚጠራው። ሆኖም አባቱም ጽሞናን ይመርጣል” 

አባቱ ለልጁ ጥሪ ከመመለስም ይልቅ ዝምታን መረጠ በማለት አባ ሚከሊኒ የአብ ዝምታን ሲያስረዱ፥ “የአብ ዝምታ ሌላው የኢየሱስ ሞት ከሚያወሱት እንቅፋቶች ውስጥ አንዱና ትልቅ እንቅፋት ነው”  ክርስቶስ በዚያኑ ወቅት የኖረው በአባቱ ለብቻው የመተዉ ጉዳይ “ትልቅ እንቅፋት”  ነው፡ የፈጠራ ጉዳይ ሳይሆን ተጨባጭ ሁነትም ነው።

ኢየሱስ የሚያሰማው “ሰቆቃ”  በአባቱ በመተዉ ወይንም በመሰቃየቱ ምክንያት ሳይሆን “በጠቅላላ ሰብአዊ አቅሙ በመሟጠጡ ምክንያት ነው” ኢየሱስ ጮኸ ብሎ መናገሩ በጣም እንቅፋት ስለነበር የየውሐንስ ወንጌል ወይንም የሉቃስ ወንጌል የኢየሱስ በመስቀል ላይ ሆኖ ወደ አባቱ ያሰማው ጩኸት አይገልጡም። ኢየሱስ ይኽ ጥልቅ ስቃዩ መግለጫ የሆነው ጩኸቱን ማንም ሊረዳለት ባለ ምቻሉ ለገዛ እራሱ አንድ አቢይ ስቃይ ነው። ስለዚህ ሁኔታህን ለማይረዳልህ ሰው ለማስረዳት የሚቻል ቢሆንም ከመስቀል ላይ ሆኖ ማስረዳቱ ግን የሚቻል አይደለም፡ ይኽ ደግሞ አንድ ትልቅ ስቃይ ነው።

“መስቀል ሁሉን ነገር ግልጥ አድርጎ የሚያስረዳ መሆኑ እናውቃለን፡ ሆኖም ኢየሱስ ከመስቀል ላይ ሆኖ ለእነዚያ ኤሊያስን እየጠራ ነው ለሚሉት ሁሉ አባቱን እንጂ ኤያስን እንዳልጠራ ሊያስረዳ አይችልም፡ ሆኖም በዚህ ወቅት ሊያደርገው የሚችለው ሁኔታውን ለመንፈስ ቅዱስ መተው ነው፡ ምክንያቱን ያንን በተለያየ ምክንያቱም ኢየሱስ በገዛ እራስ ሊያስረዳው ያልቻለው ነገ ሁሉ የሚያስረዳውምመንፈስ ቅዱስ በመሆኑ ነው። ካልሆነ በግብረ ሐዋርያት የመጀመሪያ ምዕራፍ እንደተመለከተው ነገሩን ሁሉ ለመረዳት የእርሱ ከሞት መነሣትና አብሮአቸው መገኘት አስፈላጊ ይሆናል። ከሞት ከተነሣ በኋላ አርባ ቀን አብሮ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀምጧል፡ ይኽም የሆነበት ምክንያትም ሁሉን ነገር እንዲገጥላቸው ነው”

ክርስቶስ ሁኔታው ሌሎች ሊረዱለት ካለ መቻላቸው ከመሰቀሉ በተጨምሪ ሌላ ስቃይ ይደርብበታል። ነገር ግን ከዚህ ዓይነቱ ስቃይ በላይ የስቃይ ምክንያት የሚሆንበ ሁኔታ ደግሞ በአንድ ወታደር ጎኑ በጦር መወጋቱ ይሆናል የስቃይ ስቃይ። ይኽ ወታደር ያንን በቀፈርናሆን ኢየሱስ ልጁን ያዳነለት ወታደር ያስታውሰናል።

“አንደ የቅዱስ ማቴዎስ ምስክርነት ኢየሲስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እያለ ለሞት የዳረገው በወታደሩ ጦር ጎኑ መወጋቱ ነው። ኢየሱስ በተራራው የብፅዕና አስተምህሮው ዘንድ እንዳለው ሁለተኛን ጉንጩን ለወታደሩ መልሱ ይሰጣል። የመጀመሪያው በቀፈርናሆም ልጁን ላዳነለት ወታደር ሁለተኛው ደግሞ ጎኑን ወግቶ ለገደለው ወታደር… ስለ የሁሉም ኃጢአት ስርየት ከኢየሱ ጎን ውኃና ደም ይፈሳል። ማቴዎስ እንደ ዮሓንስ ወንጌል ሳይሆን ኢየሱስ ጎድኑ በጦር የተወጋው ገና ከመሞቱ በፊት መሆኑ ያረጋግጥልና”

ያሉት አባ ሚከሊኒ በመጨረሻ ያቀረቡት የሱባኤ አስተንትኖ እነዚያ ኢየሱስ ሲሰቀል ባካባቢው የነበሩት ሴቶች ላይ በማተኮር፥

“ማቴዎስ ኢየሱስ ሲሰቀል ብዙ ሴቶች በአካባቢው ነበሩ ይልና ክእነርሱም ውስጥ የያዕቆብና የዮሴፍ እናት ማርያም አንዷ ብሎ ይጠቅሳል፤ ብዙዎች ይህች ማርያም የኢየሱስ እናት የሆነችውን ዮሐንስ በወንጌሉ የሚገልጣት በመስቀል ሥር የነበረቸው ማርያም መግለጫ ነች ብለው ይገልጥዋታል፡ ይኸንን ጉዳይ በተመለከተም ለዮሐንስ ፍንጭ የሰጠው ማቴዎስ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ሁለቱም ማርያም እንደነበረች ቢናገሩም ነገር ግን ዮሓንስ የጌታ እናት በማለት ሳይሆን የዕቆብና የዮሴፍ እናት ማርያም ሲል ይገልጣታል። አዎን ማርያም የኢየሱ እናት ብቻ ሳትሆን የሁሉም ደቀ መዛሙት እናት ትሆናለች ለማለት ነው። ስለዚህ የቤተ ክርስቲያን እናት ትሆናለች”

ሌሎች እንዳንረዳቸው እንዳናስተውላቸው የሚያደርገን በገዛ እርስ መዘጋት በትዕቢት ገዛ እራሳችንን መዘጋት ነው፡ የሚሉት ስላልገባን ሳይሆን ገዛ እራሳችን በመዝጋታችን ምክንያት ሳንረዳቸው እንቀራለን፡ ይኽ ደግሞ ልንረዳቸው ስላልፈለግን ብቻ መሆኑ ነው የሚያረጋግጠው። ምንም’ኳ የሚለውም ባይገባን ለመረዳት መመኮር ያስፈጋል። በማዳመጥና በመረዳቱ ረገድ ትሕትና ማድረግ ያስፈልጋል። በዕለታዊ ሕይወት የእግዚአብሔርን ህላዌ ማስተናገድ። በዕለታዊ ሕይወት በሌላው ስው ውስጥ ያለውን ጌታ ለመለየትና ለማስተናገድ መትጋት እንጂ እርሱ ሌገለጥበት ለሚሻው ሁነት እንደ መስቀል እንቅፋት እንዳይሆንብን እራሳችንን አንዝጋ ብለው ያስደመጡት አስተንትኖ ማጠቃለላቸው አኵይሊኖ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.