2017-02-27 17:03:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ባለ ትዳሮች በማንኛውም ሁኔታ ቢገኙም ቅርብ ሆኖ መደገፍ አስፈላጊ ነው አሉ


የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሮማዊ መደበኛ የበላይ ፍርድ ቤት፥ አዲሱ የምስጢረ ተክሊል ጉዳይ የሚመለከተው ሕግ ዙሪያ ሕንጸት እንዲያገኙ አልሞ ለመላ ቆሞሶች የጠራው እ.ኤ.አ. ከየካቲት 22 ቀን እስከ የካቲት 25 ቀን በተካሄደው ዓውደ ጥናት የተሳፉትን ቆሞሶች ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት 25 ቀን 2017 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካ ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታወቁ።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በለገሱት ምዕዳን፥ ቆሞሶች አለ ምንም ቅድመ ፍርድ በክርስቶስ ማእከልነት በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በተሠራው ምሥጢረ ተኪሊልም ይሁን በፍትሓ ብሔርም ቃል ኪዳን ለሚያስሩት ደስተኞች ቢሆኑም ባሆኑም በጠቅላላ ለባለ ትዳሮችና ለጣምሬዎች በማኛውም ሁኔታ ቢገኙም ቅርብ እንዲሆኑ ማሳሰባቸው የጠቀሱት ልእክት ጋዜጠኛ ዲኒኒ አክለው፥ ቆሞስ በሕይወት ጉዞና ጎዳና ሰውን ምእመንን የሚሸኝ ነው፡ ተጨባጩን የክልል ማሕበራዊ ሁነት በቅርብ ጠንቅቀው የሚያውቁ ናቸው። ስለዚህ አለ ምንም ቅድመ ፍርድ አደራ ለባለ ትዳሮች ለጣምሬዎች ቅርብ እንዲሆን አደራ ማለታቸው አስታውቋል።

ብዙ ወጣቶች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ምሥጢረ ተክሊል እንዲሠራላቸው ለሚጠይቁ ከወላጆቻቸው ቀጥለው ቅርብ የሚሆኑት ቆሞሶች ናቸው። እንዲሁም ጣምሬዎችም አኃድነታቸው በሚሥጢረ ተክሊል ይጸና ዘንድም ለሚጠይቁትና በተለያየ ችግር ለሚገኙትም ሁሉ ባለ ትዳሮች ቆሞሶች ቅርብ ናቸው ፡ እንዲህ በመሆኑም ዓውደ ጥናቱ ወቅታዊው የትዳር ሁኔታ ግምት በመስጠት ቤተሰብ ርእስ ዙሪይ የመከሩት ሁለቱ ሲኖዶሶችና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “Amoris laetitia - የፍቅር ሐሴት”  በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳንና ቅዱስነታቸው ባላቸው ቅዱስ ጴጥሮሳዊ ሥልጣን መሰረት Mitis Iudex e Misericors Jesus - ርኅሩኅና መሓሪው ኢየሱስ”  በሚል ርእስ ሥር ያወጁት ሕግ ላይ ያማከለ እንደነበርም ዶኒኒ ገልጧል።

“Catecumenato - የኃይማኖት ትምህርት ተማሪ” ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ  ለባለ ትዳሮች፥ እጮኛሞችን ማሰናዳት ወጣት ባለ ትዳሮችን መሸኘት፥ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይላሉ ቆሞሶች በቅድሚያ ምሥጢረ ተክሊል በወንድና በሴትች መካከል የሚጸና ጸጋ መሆኑ ለጋብቻ በማሰናጃም ሆነ ከጋብቻም በኋላ መመስከርና ባለ ትዳሮችን በደስታም ሆነ በችግር ቅርብ ሆነው ሊሸኑዋቸው ይገባል። ብዙውን ጊዜ ለመጋባት የሚጠይቁት እጮኛሞች ይኸንን በክርስቶስና በቤተ ክስቲያን መካከል ያለው አኃድነት የሚል ትርጉም ያለው ጋብቻ ጠንቅቀው የሚውቁ ስንቶች ናቸው የሚለውን ጥያቄ ቅዱስነታቸው በማቅረ። ብዙዎች ለጋብቻ የሚሰናዱት አዎ ምሥጢረ ተክሊል ተረድቶኛል ይላሉ ነገር ግን ተረድቶኛል በማለት የሚስጡት  መልስ በእምነት ላይ የጸና ነውን? ስለዚህ ምሥጢረ ተክሊል ያማከለ ትምህርተ ክርስቶስ ለተጋቢዎች ጥልቅና ሰፊ መሆን ይኖርበታል እንጂ እንዲሁ በሁለትና በሦስት የምሥጢረ ተክሊል የትምህርት ክፍለ ጊዜ ከፍፋሎ የሚቋጭ መሆን የለበትም ምክንያቱም የሕይወት ውሳኔ ነውና እንዳሉ ዶኒኒ ያመለክታሉ።

ምሥጢረ ተኪሊል ጋብቻ እንደ አንድ ማሕበራዊ ተግባር ተደርጎ የሚታሰብና የሚኖር አይደለም። በመሆኑም በምሥጢረ ተክሊል ዙሪያ የሚሰጠው  ትምህርተ ክርስቶ፡ ጥልቅና ረዥም መሆን አለበት። ጋብቻ የእግዚአብሔር ቅዱስ ምስል ነው፡ ማለትም የአሃዱና የሥላሴ እግዚአብሔር እንዲሁም በክርስቶስና በቤተ ክርስትያኑ መካከል ያለው ፍቅር የሚመሰክር ነው።  በመሆኑም ቆሞሶች ይኸንን ጥልቅ የምሥጢረ ተክሊል ትርጉም በማስተዋል ለሚሥጢረ ትክሊል ተማሪዎች እንደ የሕገ ቀኖና ሊቃውንት የሕግና የሥርዓት ጠበብት በመሆን ወይም እንደ የቢሮ የመስተዳድር ጉዳይ አዋቂ ተመስለው ሳይሆን እረኞችና የክርስቶስ ምስክሮች መሆናቸው ተለይተው ሊታወቁ ይገባል። ትዳር ለመመሥረት ለሚሻው ሁሉ፡ ጋብቻቸው ቅዱስ ምሥጢራዊ ባለ መሆኑ ቅዱስ ምሥጢራዊ ይሁንልኝ ብለው ቤተ ክርስትያንን ለሚጠይቁ ሁሉ ቅርብ መሆን ይጠበቅባችኋል ያሉት ቅዱስ አባታችን አያይዘውም፥ አለ ምሥጢረ ተኪል እንዲሁ አብረው ባልና ሚስት ሆነው ለሚኖሩት ካለ ጋብቻ አብሮ መኖርን ለሚመርጡት ቅርብ ሁኑ፡ ምክንያቱም ቤተ ክርስቲያን እናት ነች። የሁሉም እናት ነች። ሁሉም በክርስቶስ የተፈቀረ ነው። ምሥጢረ ተክሊል መንከባከብና ወንጌላዊ ትእዛዝ መሆኑ ታውቆ ነገር ግን ይኽ እውነት ለማስተማር ክርስቶሳዊ ሕይወት መኖር ያስፈልጋ። ምክንያቱም ጳውሎስ ስድስተኛ እንዳስተማሩት ቁምስና የነፍሳት መዳኛ ሥፍራ ነው። ስለዚህ ቆሞሶች አጽናኞች በተለይ ለድኾች ለተናቁት በችግር ላይ ለሚገኙት አጽናኝ ጸላያን መሆን ይጠበቅባቸዋል እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.