2017-02-24 16:52:00

ቫቲካን፥ እ.ኤ.አ. የ 2017 ዓ.ም ዓቢይ ጾም መንፈሳዊ ሱባኤ


እንደ ተለመደው በየዓመቱ ዓቢይ ጾም ምክንያት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይና የቅርብ ተባባሪዎቻቸው የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ለቅድስት መንበር ጳጳሳዊ ምክር ቤቶችና ቅዱሳን ማኅበራት ሊቀ መናብርትና ኅየንተዎች ጉባኤ አባላት ብፁዓን ካርዲናሎችና ሊቀ ጳጳሳትና አቡናት በማሳተፍ የሚካሄደው መንፈሳዊ ሱባኤ እ.ኤ.አ. ዘንድሮ ከመጋቢት 5 ቀን እስከ መጋቢት 10 ቀን 2017 ዓ.ም. በአሪቻ ከተማ በሚገኘው በመለኰታዊ መምህር ቤተ ሱባኤ እንደሚከናወንና የሱባኤ ሰባኬ እንዲሆኑ በቅዱስ አባታችን የተሰየሙት የፍራንቸስካውያን ንኡሳን አኃው ማኅበር አባል የቲዮሎጊያና የቅዱስ መጽሓፍ ሊቅ በአሲዚ የቲዮሎጊያ ተቋም የሥነ አዲስ ኪዳን ትንተና መምህር የቤተ ክርስቲያን ለባህል ትጋት እንቅስቃሴ ረዳት አባ ጁሊዮ ሚከሊኒ የሱባኤው መርሐ ግብር ዙሪያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፥ ሱባኤው በማቴዎስ ወንጌል የተማከለ ከዚህ አልፎ አበይት ደራሲያን እንደ ፍራንዝ ካፍካ፡ ኦዝና ኤማኑኤል ካረረ የመሳሰሉት ሊቃውንት ህማም ስቃይ ሕይወት በተመለከቱ የሰጡበትን ትንትነና የሚጠቀስበት ቤተሰብ ድኾች በስቃይ ላይ የሚገኙት ተጠቓሽ እንደሚሆኑ ገልጠዋል።

የሱባኤው ርእስ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ ሞና ትንሣኤ በማቴዎስ ወንጌል ሥር የሚያነብ ሲሆን። እኚህ በመጽሓፍ ቅዱሳዊ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ፡ ለባለ ትዳሮች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ እንዲሁም በፐሩጃ ሰበካ ለቋሚ ድቁና ለሚሰናዱት የሚሰጠው ቀጣይ ሕንጸት ኃላፊ በመሆን ጭምር የሚያገለግሉት አባ ሚከሊኒ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የ2017 ዓ.ም. ዓቢይ ጸሞ ሰባኬ እንዲሆን ሲመርጡኝ ይላሉ በትልቅ ኃላፊነትና በደስታ ነገር ግን መጠነኛ ፍርሃት ባለበት መንፈስ በእሺታ መቀበላችውና ሆኖም ኃላፊነቱን ከመቀበላቸው በፊት ከነፍስ አባታቸው ጋር እንደመከሩበትም ጠቁሟል።

የሱባኤው ርእስ ወደ ዓቢይ ጾም የሚያሸጋግር ወደ የክርስትና እምነት ጥልቅ ምስጢር ወደ ሆነው ወደ የሕማማት ሳምንት የሚሸኝ የጌታችን ኢየሱስ ሕማማት ሞትና ትንሣኤን ያማከለ፡ በማቴዎስ ወንጌል ዘንድ ስለ የኢየሱ ሕማማት ሞትና ትንሣሴ ዙሪያ ያለውን ክውንተኛውን ታሪክ በጥልቀት በመመርምር በዚሁ ዙሪያም የተሰጡት የተለያዩ ጥናቶች ዋና ዋና ሃሳቦችን በሥነ መንፈሳዊ ቲዮሎጊያ ሥር በመተንተን እንኳር ሃሳብ የሚቀርብበት ነው ካሉ በኋላ፥ በላቲን ሥርዓትና ባሕረ ሐሳብ መሰረትም የዘንድሮው ሊጢርጊያዊ ዓመት በማቴዎስ ወንጌል ላይ ያተኮረ መሆኑም አስታውሰው፡ እሳቸው በሥነ ቅዱስ መጽሓፍ የላቀውን የትምህርት ማዕረጋቸውን ለማጠናቀቅ ልዩ ጥናት በማካሄድ የምርምር ጽሑፍ ያቀረቡትም ወንጌላዊ መሆኑም በዚህ አጋጣሚም በማስታወስ፡ ይኽ ወንጌል የቅዱስ ጴጥሮስና የቤተ ክርስትያን ወንጌል ተብሎም ሊገለጥ ይችላል ምክንያቱን እርሱ ብቻ ነው ኤክለዚያ-ጉባኤ የሚለውን ቃል የሚጠቀም፡ በመሆኑን በቤተ ክርስቲያን እረኞች ፊት ሆኜ ስብከቱን ሳቀርብ መግቢያውን ከኢየሱ ጋር መሆን ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር መሆን በተሰኙት ነጥቦች ላይ ያተኰረ ለማድረግ ጥሩ አጋጣሚ ነው ብሏል።

በማቴዎስ ወንጌል የጴጥሮስ ቤተብን እናገኛለን ስለዚህ ቤተሰብ ዙሪያ አስተንትኖ ለማቅረብ መሰረት እንደሚሆናቸውና በመቀጠልም ኢየሱስ  በማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 26 ቁ. 11 ላይ “ ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር እልኖርም …” ሲል የተናገረው ቃል መሠረት በማረግም ደግሞ ከእናንተ ጋር ይሆናሉ ተብሎ ስለ ተነገረላቸውና እነርሱም ለጴጥሮስ የተሰጡ የመንግሥተ ሰማያት ቁልፍ መሆናቸው በማመላከት ስለ ስቃይ ያማከለ አስተንትኖ የኢየሱስ ስቃይ በጌተ ሰማኔ ትርጉሙን ስቃይና የእግዚአብሔር ፈቃድ ትርጉም ለማቅረብ እንደሚሞክሩ ከገለጡ በኋላ፥ በዚህ እሳቸው በሚያቀርቡት አስተንትኖ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሥልጣናዊ ትምህርት ያለው አስተዋጽኦ ሲያብራሩም፥ የከተሞቻችን የህልውና ጥጋዊ ክልል በማለት ቅዱስ አባታችን የሚገልጡት ሃሳብ ለሕዝብ ቅርብ መሆን ከሕዝብ ጋር መኖር፥ ከሕዝብ ጋር በሕዝብ መካከል አብሮ በመኖር የሚኖር ወንጌል ማበሰረ የሚለው ቃልና ሕይወታቸው በእርግጥ በሚያቀርቡት አስተንትኖ አቢይ አወንታዊ ተጽእኖ እንደሚኖረው ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.