2017-02-23 09:56:00

ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ "“ራስ ወዳደነትና ኋጢያት የተፈጥሮን ውበት ገጽታ ያጠለሻሉ" ማለታቸው ተገለጸ።


“ራስ ወዳደነትና ኋጢያት የተፈጥሮን ውበት ገጽታ ያጠለሻሉ፣ ነገር ግን እግዚኣብሔር የሰው ልጅን እርግፍ አድርጎ በመተው የሰው ልጅ አዲስ የሕይወት ተስፋን በመሻት በመቃተት እንዲኖር አይፈቅድም”። ይህ ቀደም ሲል የነበባችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ልማዳዊ በሆነውና ዘወትር ረዕቡና እሁድ እለት ከሚያቀርቡ የጠቅላላ አስተምህሮ አንድ አካል በሆነው፣ “የክርስቲያን ተስፋ” በሚል አርዕስት በየካቲት 15/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በጳሎስ ስድስተኛ አዳራሽ የጠቅላላ አስተምህሮዋቸውን ለመከታተል ለተገኙት ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ካደረጉት አስተምህሮ የተቀነጨበ ነው።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

የቅዱስነታቸው የእለቱ አሰትምህሮ ትኩረቱን ያደረገው ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ሮም ሰዎች በጻፈው መልእክቱ በምዕራፍ ስምንት ላይ ተመርኩዘው ከእዚህ ቀደም “የክርስቲያን ተስፋ” በሚል አርዕስት ጀምረውት የነበረው አስተምህሮ ማጠናከሪያ ይሆንላቸው ዘንድ በማሰብ ጠፈጥሮ ከእግዚኣብሔር ለሰው ልጅ በስጦታነት የተሰጠ መሆኑን ገልጸው ነገር ግን የሰው ልጅ በኋጢያቱ ይህንን ተፈጥሮ እየበደለ እንደ ሚገኝ በአጽኖት ገልጸዋል።

“ተፈጥሮ ከእግዚኣብሔር ለሰው ልጅ የተሰጠና በእጃችን ያኖረው ድንቅ ስጦታ መሆኑን  ቅዱስ ሐዋሪያ ጳውሉስ ያስታውሰናል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር ይህንን ያደረገበት ምክንያት የሰው ልጅ በተፈጥሮ አማካይነት ከእግዚኣብሔ ጋር ያለውን ቁርኝት ያጠናክር ዘንድ በማሰብ መሆኑን ገልጸው ተፈጥሮ የእግዚኣብሔር እጅ የፈቅር አሻራ ያረፈበት በመሆኑ ከተፈጥሮ ጋር በእየእለቱ እየተባበርን መኖር ይገባናል ብለዋል።

በራስ ወዳድ መንፈስ ተነሳስተን ኋጥያትን በምንፈጽምባቸው ወቅቶች ሁሉ ከእግዚኣብሔር ጋር ያለንን ኅብረት እናፈርሳለን በማለተ አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱሰታቸው በእዚህም የተነሳ  የሰው ልጅ የመጀመሪያውን የተፈጥሮ ውበትና ተፈጥሮ ራሱን እያበላሸ ይገኛል ብለዋል።

“ከእግዚኣብሔር ጋር ያለንን ኅብረት በምናፈርስበት ወቅት የምናበላሸው ከእግዚኣብሔር ጋር ያለንን ኅበረት ብቻ ሳይሆን ከወንድም እህቶቻችን ጋር ያለንን ኅበረት አደጋ ላይ እንዲወድቅ እናደርጋለን በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም የተነሳ ተፈጥሮን እንበድላለን ወደ ባርነትም እንቀይረዋልን በተጨማሪም ለእኛ ደካማነት የተመቻቸ እንዲሆንም እናደርጋለን ብለዋል። ያለመታደል ሆኖ የእዚህን ትይንት እውነተኛነት በእየ እለቱ እየታዘብን እንገኛለን ያሉት ቅዱስነታቸው ምን ጊዜም ቢሆን የሰው ልጅ ከእግዚኣብሔር ጋር ያለውን ኅበረት በሚያፈርስበት ወቅቶች ሁሉ ተፈጥሮአዊ ውበቱን ያጣል፣ በዙሪያው የሚገኙትን ነገሮች ተፈጥሮአዊ ገጽታቸውን እንዲያጡ ያደርጋል ብለዋል።

ከሁሉም በላይ አስገራዊ የሆነው ነገር ፈጣሪ የሆነው አብ ወሰን በሌለው ፍቅሩ ይህንን የሰው ኩራትና እብሪተኛነትን፣ በተጨማሪም የሰው ልጅ አሳዛኝ መሆኑን ስለሚረዳ የሰውን ልጅ ትክክለኝ የሆነ መንገዱን እስኪ ይዝ ድረስ መንከባከቡን በፍጹም አያቋርጥም፣ የሰው ልጅ ግን የእግዚኣብሔርን ዘላለማዊ ፍቅር ከመግለጽ ይልቅ በሚያሳየው ኩራት እና እብሪት የተነሳ ተፈጥሮን ዋጋ እያስከፈለ እንደ ሚገኝ ገልጸዋል።

ምንም እንኳን የሰው ልጅ እነዚህን የበደል ተግባሮች እየፈጸመ ቢገኝም ቅሉ፣ እንደ ሰው ያልሆነው እግዚኣብሔር ግን የሰው ልጅን አልረሳውም፣ አዲስ የሆነ የነጻነትና የደኅንነት አድማስ ይጎናጸፍ ዘንድ ይጠራዋል ብለዋል።

“በእርግጥ ልብ ብለን ካደመጥን በአከባቢያችን ያሉ ነገሮች ሁሉ በመቃተት ላይ ይገኛሉ፣ ተፍጥሮም በራሱ በመቃተት ላይ ይገኛል፣ የሰው ልጆችም ቢሆኑ በመቃት ላይ ይገኛሉ፣ መንፈስ ቅዱስም በልባችን ውስጥ በመቃተት ላይ ይገኛል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ሁሉ መቃተት መጽናኛ የሌለው መቃተት አይደለም፣ ነገር ግን ልክ በምጥ ላይ እንደ ምትገኝ ሴት አዲስ የሕይወት ብርሃን እንደ ሚመጣ የሚያበስር ነው ብለዋል።

ምንም እንኳን ኋጥያተኞች ብንሆንም በእግዚኣብሔር መልካምነት መዳናችንንና ያም የደኅንነት ስሜት በሕይወታችን እንዳለ ይሰማናል ካሉ ቡኋላ ክርስቲያኖች ሁላችን በምንም ዓይነት መልኩ ተስፋ መቁረጥ የለብንም መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ደካማነት ባሻገር እንድንመለከት በማድረግ እግዚኣብሔር ለእኛ ያዘጋጀውን አዲስ ሀገር በተስፋ እንድንመለከት ያግዘናል ካሉ ቡኋላ የእለቱን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.