2017-02-17 17:56:00

ዓለም አቀፍ የባብቲስትና መጦዲስት አቢያተ ክርስቲያን የጋራው ዓውደ ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ከየካቲት 1 ቀን እስከ የካቲት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. እምነትና ፍቅር በሚል ርእስ ዙሪያ ዓለም አቀፍ ውይይት የባብቲስትና መጦዲስት አቢያተ ክርስቲያን ዓውደ ጉባኤ በአገረ ጃማይካ ራንዋይ ባይ ከተማ በኪንግስቶን የቲዮሎጊያ ኅብረት መንበረ ጥበብ መምህር የቲዮሎጊያ ሊቅ መጋቤ ቶማስ ኦራል፤ ማቴዎስ ወንጌል ምዕ. 5, 20 “ የእናንተ ጽድቅ ከሙሴ ሕግ መምህራንና ከፈሪሳውያን ጽድቅ ካልበለጠ ወደ መንግሥተ ሰማይ ከተ አትገቡም እላችኋለሁ” ሲል ኢየሱስ የተናገረውን ቃል በማስደገፍ ባስደመጡት ንግግር ተጋባእያንን ተቀብለው ያስጀመሩት ጉባኤ የጋራ ሰነድ በማርቀቅ የተጠናቀቀ መሆኑ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አሊና ቱፋኒ የህዳሴ ቤተ ክርስቲያን ይፋዊ የኢጣሊያው ድረ ገጹ አማካኝነት ያሰራጨው የዜና ምንጭ ጠቅሰው አስታውቋል።

ከዓለም አቀፍ የባብቲስት አቢያተ ክርስቲያን ቃል ኪዳን እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የሜጦዲስት አቢያተ ክርስቲያን ምክር ቤት የተወጣጡ ልኡካን ያሳተፈው ለአንድ ሳምንት በጃማይካ የተካሄደው አራተኛው ዓውደ ጉባኤ “በፍቅር አማካይነት በሥራ ላይ የሚውል እምነት” (ገላ. ምዕ. 5)፥ ጸጋ (ጽድቅ) እና እምነት፡ በመኖርና በመካፈል ዘምሩ ስበኩ” በማለትም ተጋባእያኑ ማኅበራዊ ተግባሮችና ምሕረት ስግደትና አምልኮ እንዲሁም ስብከተ ወንጌል በተሰኙ ተልእኮዎች የባብቲስት አቢያተ ርስቲያንና የመጤዶስት አቢያተ ክርስቲያን የሚሰጡት አገልግሎትና የሚመሰክሩት ሱታፌ ምን እንደሚመስል በመምከርም እነዚህ አቢያተ ክርስትያን በተለያየ ክፍል ዓለም የሚኖሩት እምነትና ትግባሬው በተሰኙት ርእሰ ጉዳዮች ሥር ሰፍ የሓሳብ ልውውጥ ማካሄዳቸው የኢጣሊያ የተሃድሶ ቤተ ክርስቲያን ድረ ገጽ የጠቀሱት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ቱፋኒ አያይዘው፥ ከዚህ ባለ አሥር ነጥቦች ሰነድ ላይ ተንተርሶ ለአንድ ሳምንት የተካሄደው ዓውደ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከመጋቢት 14 ቀን እስከ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. በእንግልጣር ሳሊስቡርይ በሚገኘው የአቢያተ ክርስቲያን የጋራ ሳሩም ተቛም ሊካሄደው ለተወሰነው ዓውደ ጉባኤ ማካሄጃ ሰነድ ማጠናቀሩ አስታውቋል።

የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን የጋራው ዓለም አቀፍ ምክር ቤት የጉባኤ ተሳታፊያን በኪንግስቶን የሚገኙትን የባብቲስትና የሜጦዲስት አቢያተ ክርስቲያን እንዲሁም የጋራው የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ መጎብኘታቸውና በሳይንት ኤን በሚገኘው የሜጦዲስት ቤተ ክርስትያን የጋራ የስግደትና የአምልኮ ሥነ ስርዓት መፈጸማቸው የኢጣሊያ የተሃድሶ አቢያተ ክርስቲያን ድረ ገጽ የጠቀሱት የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ አሊና አያይዘው እንዳመለከቱቱም  የጸሎቱ ስነ ሥርዓት የመሩትም ክብሩ አቡነ ኤቨራርድ ጋልብራይዝ ሲሆኑ  ክብሩ መጋቤ ኦራል በጸሎቱ ስነ ሥርዓም አብነት መሆን ክርስቲያናዊ ምስክርነትና የምትናዘዘውና የምትኖረው እምነት ትውስብ መሆን እንዳለበት የሚያስገነዝብ ስብከት ያስደመጡትም አስታውቋል።

ዓውደ ጉባኤው በካሪቢያን የመጦዲስት ማኅበረ ክርስቲያን ህልውና ዝክረ 200ኛው ዓመት ምስረታ ጋር ተያይዞ የተከናወነ መሆኑ ቱፋኒ ገልጠው፡ የመጦዲስት ማኅበረ ክርስቲያን ሃይቲ የገባው እ.ኤ.አ. በ 1817 ዓ.ም. ከእንግልጣርና ከአየርላንድ በመጡት የመጦዲስት ልኡካነ ወንጌል አማካኝነት ሲሆን ማኅበረ ክርስቲያኑ የደረሰበት የተለያየ ሰብአዊ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ችግሮችን ተሻግሮ እምነቱን አቅቦ የቆየና በሕንጸት ዘርፍ በአገሪቱ የሚሰጡት አገልግሎት እጅግ የሚደነቅ ከመሆኑም ባሻገር በተለያየ ወቅት በአገሪቱ ሕዝብና መንግስት ተመስጋኝና ለተለያዩ ሽልማቶችም የበቃና በጠቅላላ 105 የአንደኛ ደረጃ ትምህርት በቶች 15 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችና የተለያዩ የተግባረ ዕድ ትምህርት ቤቶች ያሉት መሆኑ ሲነገር፡ በቅርቡም በካናዳና በአየርላንድ የሜጦዲስት አቢያተ ክርስቲያን ድጋፍና ትብብር አማካኝነት አንድ አዲስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገንቦት ለአገልግሎት ማብቃቱም የኢጣሊያ የተሃድሶ ቤተ ክርስቲያን ድረ ገጽ ያሰራጨውን ዜና ዋቢ በማድረግ ይጠቁማሉ። 








All the contents on this site are copyrighted ©.