2017-02-13 16:57:00

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሱዳን ለኤል ኦባይድ ሰበካ አዲስ ጳጳስ ሰየሙ


የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል እ.ኤ.አ. የካቲት 13 ቀን 2017 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሱዳን ለኤል ኦባይድ ሰበካ ጳጳስ እንዲሆኑ የሰበካው ካህን በጁባ የአቢይ ዘርአ ክህነት ተማሪዎች አለቃ አባ ዩናን ቶምበ ትሪለኩኩ አንዳሊን መሰየማቸው ለማወቅ ተችሏል።

አዲሱ የኤል ኦባይድ ጳጳስ በመሆን የተሾሙት ብፁዕ አቡነ ዩናን ቶምበ ትሪለኩኩ አንዳሊ እ.ኤ.አ. ጥር አንድ ቀን 1964 ዓ.ም. በሱዳን የኑባይ ተራራማው ክልል በሚገኘው በቶጆሮ ከተማ የተወለዱ በኤል አባይድ በሚገኘው በኮምቦኒ ሁለተኛ ክፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን አጠናቀው በጁባ የፍልስፍና ትምህርት በካርቱም የቲዮሎጊያ ትምህርታቸውን ካጠናቀቁ በኋላ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 7 ቀን 1991 ዓ.ም. ድልው ወእቱ ተብለው ማእርገ ክህነት መቀበላቸውም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ጠቁሞ ማእርገ ክህነት ከተቀበሉ በኋላ እ.ኤ.አ. ከ1991 ዓ.ም. እስከ 1995 ዓ.ም. በኤ ሃሁንድ፡ በናያላ በኤል ፋሸርና በካዱጉሊ ረዳት ቆሞስ ከ 1995 እክሰ 2002 ዓ.ም. ደግሞ በኤል ኦበይድ ዘርአ ክህነ ትምህርት ቤት አለቃ በተጨማሪም ከ 1997 እስከ 2002 ዓ.ም. የሰበካው ሓዋርያዊ መሥተናብር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን እ,ኤአ.አ. ከ 2002 እክሰ 2009 ዓ.ም. ናይሮቢ በሚገኘው የካቶሊክ መንበረ ጥበብ በሥነ ሕገ ቀኖና ሊቅነት አስመስክረው እንዳበቁም ከ 2009 ዓ.ም. እስከ 2012 ዓ.ም. በሳራፍ ጃሙስ በሚገኘው የሁሉም ቅዱሳን ቤተ ክርስቲያን ቆሞስ ሆነው እንዳገለገሉ የቅድስት መንበር የዘናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ያመለክታል።

የኤል ኦባይድ ሰበካ እ.ኤ.አ. በ 1974 ዓ.ም. የጸና በዚያ ክልል 9 ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺህ ነዋሪ እንዳለና ከእነዚህም ውስጥ 10 ሺሕ ደግሞ የካቶሊም እምነት ተከታይ መሆኑ ይነገራል። 14 ቁምስናዎች ያሉት በክልሉ በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ የተሰማሩ 24 የሰበካ ካህናት 6 ገዳማውያን በጠቅላላ 30 ካህናት እንዲሁም 19 ደናግል በማገልገል ላይ እንደሚገኙ የጠቆመው አቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አያይዞ በአሁኑ ወቅት 15 የዘርአ ክህነት ተማሪዎችም እንዳሉ አስታውቋል።

የኤል ኦባይድ ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሚከለ ዲዲ አድጉም ማንጎሪያ እ.ኤ.አ. ከ 2005 ዓ.ም.  ወዲህ የካርቱም ሰበካ ሊቀ ጳጳስ ረዳት እዲሆኑ ከተሾሙ ወዲህ ሐዋርያዊ መንበር ክፍት ሆኖ መቆየቱንም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.