2017-02-11 10:14:00

ር.ሊ.ጳጳሳት ፍራንቸስኮ "ሴቶች ባይኖሩ ኖሮ በዓለም ውስጥ ምንም ዓይነት ስምምነት ሊኖር አይችልም” ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “ሴቶች ባይኖሩ ኖሮ በዓለም ውስጥ ምንም ዓይነት ስምምነት ሊኖር አይችልም” ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ይህንን ያሉት በየካቲት 2/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ ባሰሙት ስብከት እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን በእለቱ ያሰሙት ስብከት ዋነኛው ትኩረቱ አድርጎ የነበረው በእለቱ ከኦሪት ዘፍጥረት በተወሰደው የመጀመሪያ ምንባብ ላይ ተጠቅሶ የነበረው የሄዋን አፈጣጠር ታሪክ ላይ መሰረቱን አድርጎ እንደ ነበረም ታውቁዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

“ወንድ እና ሴት እኩል አይደሉም፣ አንዱ የሌላው የበላይም አይደለም” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ማንኛውም ነገር ተስማሚ እንዲሆን በማድረግ ዓለማችን ውብ የሆነ ስፍራ  እንዲሆን ያደረገው ወንድ ሳይሆን ሴት ልጅ ናት ብለዋል።

እንደ ጎጎሮሳዊያኑ የስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር በእዚህ እያገባደድን በምንገኘው ሳምንት በመስዋዕተ ቅዳሴ ላይ የሚነበቡት የመጽሐፍ ቅዱስ ቃላት የተወሰዱት ስለ ዓለም እና የሰው ልጆች አፈጣጠር ከሚያወሳው የኦሪት ጸፍጥረት መጽሐፍ ላይ ሲሆን ቅዱስነታቸው እነዚህን ምንባባት ከግምት ባስገባው ስብከታቸው እንደ ገለጹት እግዚኣብሔር አምላክ የተለያዩ ዓይነት እንስሳትን ፍጥሮ እንደ ነበረ አውስተው ነገር ግን ከእነዚህ አምላክ ከፈጠራቸው እንስሳት ውስጥ ለሰው ልጅ አጋር የሚሆን ባለመገኘቱ የተነሳ ብቻውን ቀርቶ እንደ ነበረም ገልጸዋል።

ነገር ግን እግዚኣብሔር አዳም ብቻውን ሊሆን አይገባም በሚል እሳቤ ከጎኑ አጥንት በመውሰድ ሄዋንን መፍጠሩን ከገለጹ ቡኋላ አዳምም ይህቺ “ከሥጋዬ የተገኘች ሥጋዬ ናት” ብሎ በደስታ እንደ ተቀበላትም ገልጸዋል።

“ብዙን ጊዜ ስለ ሴቶች ስናወራ በቅድሚያ የምናወሳው የሚሰሩት ሥራ ላይ ብቻ ትኩረቱን ያደረገ ወሬ ላይ ነው የምናተኩረው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን በአንጻሩ ሴቶች ወንዶች የሌላቸውን ትልቅ ሐብት አላቸው ያሉት ቅዱስነታቸው ይሄው ትልቅ ሐብታቸው በፍጡራን መካከል ሕብረት እንዲመጣ የማድረግ ክህሎታቸው መሆኑን ጨምረው ጠቅሰዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት ዓለም በተፈጠረበት ወቅት በነበሩት 3 ዋና ዋና ወቅቶች ላይ አትኩሮ የነበረ ሲሆን እነዚህም አዳም ብቻውን የነበረበት ወቅት፣ ሕልም ያለመበት ወቅት እና የአዳም እና የሄዋን የወደ ፊት እጣ ፈንታቸው በሚሆነው “አንድ አካል የመፍጠር እቅዳቸውን” ያጠቃለለ መሆኑንም ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት ሐሳባቸውን በሚገባ ለማስረጽ በማሰብ የሕይወት ገጠመኛቸውን ያካፈሉ ሲሆን ይህም ሁለት ጥንዶች የተጋቡበትን 60ኛ አመት በዓል በሚያከብሩበት ወቅት ተገኝቼ “እስቲ ከእናንተ ከሁለታችሁ በእነዚህ 60 አመታት የጋብቻ ጉዞዋችሁ ከሁለታችሁ ማነኛችሁ ናችሁ ከፍተኛ የሆነ ትዕግስት የነበራችሁ?” ብለው ጠይቀ እንደ ነበረ አስታውሰው ይህንን ጥያቄ በጠየኩዋቸው ወቅት . . . “ይህ አጋጣሚ መቼም ቢሆን አይረሳኝም፣ ሁለቱም አትኩረው ተመለከቱኝ፣ ያዩኝ የነበረውም ዐይን ዐይኔ ውስጥ ነበረ፣ ሁሉቱም በአንድነት “እኛ በከፍተኛ ፍቅር ውስጥ ነን!” በማለት በአንድነት መለሱልኝ። ይህም ማለት ለ60 አመታት አንድ አካል ሆነው ነበር የኖሩት ማለት ነው። ለእዚህም ነው ቀደም ሲል ሴቶች ለየት ያለ ስጦታን ለማኅበረሰቡ ያጎናጽፋሉ ያልኩዋችሁ። ሴቶች እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ የማድረግ ስጦታ አላቸው። ዓለማችን ሕብረት እንዲኖራትም ያደርጋሉ። ሴቶችን መበደል ማለት እግዚኣብሔር ለዓለማችን የሰጠውን ሕብረት ማፍረስ ማለት ነው” በማለት ቅዱስነታቸው ገጠመኛቸውን አካፍለዋል።

ስለ እዚህም ሴቶችን መጨቆን ወንጀል ብቻ ሳይሆን ሕብረታችንን እንደ ማፍረስም ይቆጠራል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ ከሰጣቸው ስጦታዎች ትልቁ ስጦታ ለአዳም የተሰጠችሁ ሴት መሆኑዋን ጠቅሰው ያለ ሴቶች ዓለማችን ውብ ዓለም ልትባል ወይም ልትሆን አትችልም ካሉ ቡኋላ ዓለም ያለ ሴቶች ሕብረት በፍጹም ሊኖረው አይችልም እግዚኣብሔር ሴትን ባይፈጥር ኖሮ ሁላችንም እኖቶች ሊኖረን አይችልም ነበር ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.