2017-02-06 15:18:00

ቅዱስነታቸው "ክርስቲያኖች ከሐሜት፣ ከምቀኝነት እና ከራስ ወዳድነት” መራቅ ይኖርባቸዋል ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፈራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 28/2009 ዓ.ም. ሳምንታዊውን የጠቅላላ አስተምህሮዋቸውን ለመከታተል  በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ባስተላለፉት አስተምህሮዋቸው ክርስቲያኖች  ልክ ነደ እንደ የባዕድ ሕዋስ ሕይወታቸውን ሊበክሉ ከሚችሉት “ሐሜት፣ ምቀኝነት፣ ራስ ወዳድነት” መራቅ ይኖርባቸዋል ማለታቸው ተገለጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ!

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው አጽኖት ሰጥተው እንደ ገለጹት ክርስቲያኖች ሊኖራቸው የሚገው ተልዕኮ በእምነት እና ክርስቶስ በሰጣቸው ፍቅር ተሞልተው  በማኅበረሰቡ ውስጥ የሕይወት ጣዕም እንዲኖር ማድረግ ነው” በማለት ለክርስቲያኖች ጥሪ ማድረጋቸውም ተገልጹዋል።

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጥር 28/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት የመልአከ እግዚኣብሔር ጸሎት በፊት ያደረጉትን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በእነዚህ ተከታታይ እለተ ሰንበቶች ውስጥ በስርዓተ ሉጥርጊያችን ደንብ መሠረት የምናገኛቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ቃለት የተወሰዱት በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ከሚገኘው ኢየሱስ በተራራ ላይ ያደረገውን ስብከት ነው። የባለፈው ሰንበት አስተምህሮየደስታ ምንጭበሆኑት ነገሮች ዙሪያ ያጠነጠነ አስተምህሮ የነበረ ሲሆን የዛሬው እለት አስተምህሮ ደግሞ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት የሆኑት ሁሉ በዓለም ውስጥ ሊኖራቸው ስለሚገባው ተልዕኮ ያስረዳል (ማቴዎስ 5, 13-16) ኢየሱስ የጨውን እና የብርሃንን ምሳሌ በመጠቀም በሁሉም ዘመን ለሚገኙ ደቀ መዛሙርት እኛንም ጨምሮ ማለት ነው መልዕክቱን ያስተላልፋል።

ኢየሱስ በመልካም ሥራ የታጀበ ምስክርነትን በመስጠት የእርሱ ብርሃን ነጸብራቅ እንድንሆን ይፈልጋል። እንዲህም ይላልሰዎች መልካም ሥራችሁን አይተው የሰማይ አባታችሁን እንዲያመሰግኑት የእናንተም ብርሃን በሰው ፊት ሁሉ ይብራ!” ይለናል (ማቴዎስ 5,16) እነዚህም ቃላት በአጽኖት የሚያሳስቡን የእርሱ ትክክለኛ ደቀ መዛሙርት መሆናችን እና የዓለም ብርሃን መሆናችን የሚገለጸው በቃላት ብቻ በምንላቸው ነገሮች ሳይሆን በተግባራችን ሲደገፍ መሆኑን ጭምር ያሳየናል። በእርግጥ ከሁሉም በላይ የእኛ በሕሪይ ጥሩ ይሁን መጥፎ ለሌሎች አንድ መልእክት ማስተላለፉ አይቀሬ ነው። ስለ እዚህም ለተሰጠን ፀጋ አላፊነት እና ግዴታ አለብን በክርስቶስ አማካይነት በውስጣችን በሚገኘው የእምነት ብርሃን እና በመንፈስ ቅዱስ ተግባራዊ እንቅስቃሴ አማክይነት የራሳችን የግል ንብረት አድርገን ብቻ መጠቀም የለብንም። በምትኩም ይህ ብርሃን በዓለም ውስጥ እንድናበራ ነው የተጠራነው፣ በመልካም ተግብራችን ለሌሎች ይህንን ብርሃን ለመስጠት ነው የተጠራነው። ዓለማችን በእመነት ለሚቀበሉት ሁሉ የሚቀይራቸውን፣ የሚያድናቸውን እና የደኅንነታቸውን ዋስትና የሚያረጋግጠውን የወንጌል ብርሃን በጣም ያፈልጋታል! ይህንንም ብርሃን በመልካም ሥራችን አማካይነት ማዳረስ አለብን።

ይህንንም ብርሃን ለሌሎች በመስጠታችን የተነሳ በእኛ ውስጥ ያለው ብርሃን አያልቅም ወይም አይጠፋም ነገር ግን ይበልጡኑ ይጠናከራል። በተቃራኒው በፍቅር እና በምሕረታዊ ተግባሮቻችን ይህንን ብርሃን የማንኮተኩተው ከሆነ ይጠፋል። በእዚህም ረገድ የብርሃን ምሳሌ ከጨው ምሳሌ ጋር ይገናኛል። በእርግጥ በወንጌላችን ውስጥ ተጠቅሶ እንደ ምናገኘው የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት በመሆናችን የተነሳየምድር ጨው ነን!” (ማቴዎስ 5,13) ጨው ለምግብ ጣዕምን ከመስጠቱም ባሻገር የማቀዝቀዣ መሣሪያ ባልነበረበት የክርስቶስ ዘመን ምግብ ሳይበላሽ ለብዙ ጊዜ  እንዲቆይ ለማድረግ ይጠቀሙበትም ነበረ። ስለ እዚህም ክርስቲያኖች በማኅበረሰቡ ውስጥ ሊኖራቸው የሚገባው ተልዕኮ በእምነት በተሞላ ሕይወት አማካይነት እና ክርስቶስ በሰጣቸው ፍቅር በመሞላት በተመሳሳይ መልኩም ሕይወታችንን እንደ ባዕድ ተዋሲያን ሊበክሉ ከሚችሉ ራስ ወዳድነት፣ ምቀኝነት፣ በጣም ጎጂ የሆነ ሐሜት. . . ወዘተርፈ ራሳችንን በመቆጠብ ለማዕበረሰቡ ጣዕምን ለመስጠት ነው የተጠራነው። እነዚህ የባዕድ ተዋዕሳት ማኅበረሰባችን እንግዳ ተቀባይነቱን፣ ሕብረት ፈጣሪነቱን እና የእርቅ አድራጊነት መንፈሱን ጠብቆ እንዲጓዝ የሚያደርገውን የማኅበረሳባችንን መዋቅር ያፈራርሱታል ወይም ያበላሹታል። ይህንን ተልዕኮ በሚገባ ለመፈጸም ከተፈለገ እኛ ራሳችንን በቅድሚያ ከኢየሱስና ከወንጌል  ፍላጎት በተቃራኒ ጎራ የሚገኘውን  ከተጠናወተን  የዓለማዊነት ስሜት መላቀቅ ይኖርብናል፣ ይህም ታዐድሶ በአንድ ጊዜ የሚጠናቀቅ ተዐድሶ ሳይሆን በእየ እለቱ በሕይወታችን የሚተገበር ታዐድሶ ሊሆን ይገባል።

እያንድ አንዳችን የተጠራነው እለት በእለት በምናከናውናቸው ተግባሮቻችን ብርሃን እና ጨው እንድንሆን ነው፣ እውነተኛ የሆኑትን የሰው ልጆች እሴቶችን በወንጌል እና በእግዚኣብሔር መንግሥት አስተሳሰቦች ወይም ምልከታዎችን ከግምት በማስገባት ተጠብቀው እንዲኖሩ ማድረግ ይኖርብናል። የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት አብነት የሆነችው እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም አማኞችን በጥሪያቸው እና በትልዕኮዋቸው እንድትረዳ መማጸን ያስፈልጋል። ራሳችንን ሁል ጊዜ ማንጻት እንድንችል በጌታ ብርሃን ተሞልተንየምድር ጨውእናየዓለም ብርሃን መሆን እንድንችልትርዳን አሜን!

ክቡራን እና ክቡራት አድማጮቻችን ቀደም ሲል ስትከታተሉት የቆያችሁት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በጥር 28/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ከምዕመናን ጋር በመቀባበል ከሚደግሙት የመልአከ እግዚኣብሔር ጸሎት በፊት ያደረጉትን አስተምህሮ ሙሉ ይዘት ነበር ስለ ተከታተላችሁን ከልብ እናመሰግናለን።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.