2017-02-06 17:01:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ርእሰ ንዋይነት ኤኮኖሚ(የግል የኤኮኖሚ ዘዴ) ድኻን የሚያገል ነው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም. እዚህ በሮማ አቅራቢይ ካስተልጋንዶልፎ ከተማ በሚገኘው በአፍቅሮተ ዘቤት ማእከል በሆነው በማሪያፖሊ ሕንፃ በዚሁ በካቶሊካዊ እንቅስቃሴ አዘጋጅነት እ.ኤ.አ. ከየካቲት 2 ቀን እስከ የካቲት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በተካሄደው የሱታፌ ኤኮኖሚ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ ተሳታፍያንን ተቀብለው “ትርፍ ብቻ የሚል ገንዘብን የሚያመልክ ኤኮኖሚ ማሸነፍ ያስፈልጋል” የሚል ግብረ ገባዊ ትእዛዝ አዘል መልእክት ላይ ያነጣጠረ ሥልጣናዊ ምዕዳን መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

በዚህ አፍቅሮተ ዘቤት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ ባሰናዳው ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ የዚህ ዓለም አቀፍ የሱታፌ ኤኮኖሚ ማኅበር ቅርንጫ ከሚገኙባቸው ከስምንት የአፍሪካ አገሮች እነርሱም ከቡርኪናፋሶ ከብሩንዲ ከካመሩን ከአቨርይኮስት ከኢትዮጵያ ከናይጀሪያ ከደሞክራሲያዊት ረፓብሊክ ኮንጎና ከኡጋንዳ ከሰሜን አመሪካ ደግሞ ከካናዳና ከተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ከላቲን አመሪካ አገሮች ውስጥም ከአርጀንቲና ከቦሊቭያ ከብራዚል ከቺለ ከኩባ ከመክሲኮ ከፓናማ ከፓራጉዋይና ኡራጉዋይ ከእስያም ከቻይና ኮረያ ከፊሊፒንስ ከሆንግ ኮንግ ከማለዢያ ከሲንጋፑር ከታይላንድ ከቨትናም ከምስራቅ ኤውሮጳ ክልል አገሮች ደግሞ ከክሮአዚያ ከሮማኒያ ከራሻ ከሰርቢያ ከስሎቫኪያ ከኡክራይንና ከሃንጋሪ ከምዕራብ ኤውሮጳ ደግሞ ከኦስትሪያ ከበልጂም ከፈረንሳይ ከጀርመን ከአይርላንድ ከጣሊያን ከሆላንድ ከፖርቱጋል ከተባበሩት የንጉሣን ግዛቶችና ከስፐይን ከኦቻይና ክልል ደሞም ከአውስትራሊያ የተወጣጡ በጠቅላላ አንድ ሺሕ አንድ መቶ ተጋባእያንን በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው መሪ ቃል የለገሱት ቅዱስ አባታችን፥ በአሁኑ ሰዓት በዓለማችን እየታየ ያለው እርግጠኛነት አልቦ በተጨባጭ ላይ ሳይሆን ግምት ላይ የሚንተራስ ለአደጋ የሚያጋልጥና ቆማርተኛ ኤኮኖሚ በሚልዮን የሚገመቱ ቤተሰቦች ለከፋ አደጋ እያጋለጠ ይገኛል። በሌላው ረገድ ለአንዲት አገር መሰረት ከሚባሉት ሕጎች ውስጥ ያንን ለእርስ በእርስ መተሳሰብ መሰረት የሆነው  እርሱም የገቢ ግብር  ክፍያ ወይንም ከገቢ መጠን ለመንግሥት የሚከፈል ቀረጥ መጣስም የብዙ ሰዎች ሕይወት ለአደጋ ማጋለጥ ይሆናል። ስለዚህ እነዚህ ሁለቱ ግድፈቶች ድኾችን ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን የኅብረሰተስብ ክፍሎች ለከፋ አደጋ ያጋልጣሉ።

የአንድ የኤኮኖሚ ዜዴ ማእከል ድኾች መሆን አለባቸው፡ ስለዚህ የአፍቅሮተ ዘቤት ካቶሊካዊ እንቅስቅሴ መሥራች ነፍሰ ኄር ኪያራ ሉቢክ እንዳሉት ኤኮኖሚና ሱታፌን ያጣመረ መሆን አለበት። ይኽ ዓለም አቀፍ የሱታፌ ኤኮኖሚ ማኅበር ኪያራ ሉቢክ እ.ኤ.አ. በ 1991 ዓ.ም. በብራዚል ካካሄዱት ጉብኝትና እዛ ካዩት የተለያዩ የእርስ በእርስ መደጋገፍ የሚል እሴት ላይ የጸና ሁሉም የሁሉ በማድረግ ማንም የማይነጥል የሱታፌ ኢኮኖሚ ማኅበራት ያላቸው ተመክሮ በማድነቅ ይኽ ዓይነቱ የኤኮኖሚ ዓለም አቀፋዊ ቅርጽ እንዲይዝ በማድረግ ያቆሙት ማኅበር ሲሆን። ይኸው 25ኛ ዓመቱን እያስቆጠረ መሆኑም ቅዱስ አባታችን በለገሱት ምዕዳን አስታውሰው፥

ገንዘብን ጣዖት ለሚያደርግ ርእሰ ንዋይነት ኤኮኖሚና ለአደጋ የሚያጋልጥና ቆማርተኛ ኤኮኖሚ እምቢ ማለት ያስፈልጋል።

ገንዘብ አስፈላጊ ነው ሆኖም ጣዖት ሲሆንና ሲመለክ አደገኛ ይሆናል። ስለዚህ ገንዘብን ከማምለክ ፈተና እንጠበቅ፡ ርእሰ ንዋይነት ኤኮኖሚ ትርፍ ማካበት ላይ ሲያተኩር ትርፍ ብቸኛው ተደራሽ ዓላማው በማድረግ ሲያስቀምጥ፡ የኤኮኖሚው ዘዴው ጣዖት የሚመለክበት መዋቅር ይሆንና የብዙዎችን ሰዎች ሕይወት በተለይ ደግሞ የድኾና ደካማ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለከፋ አደጋ ያጋልጣል፡ መስዋዕት ያደርጋል።

በገንዘብ ሁሉን ነገር መግዛት ይቻላል ነገር ግን ዘለዓለማዊ ሕይወት አይገዛም፡ ይኽ የሱታፌ ኤኮኖሚ ባንጻሩ ገንዘብ ግብረ ገባዊና መንፈሳዊ እሴት ሥር እንዲመራ በማድረግ ትርፍ ለጋራ ይሁን ይላል። ተካፍሎ መኖር በተለይ ደግሞ ከድኾች ጋር ተካፍሎ መኖር የሚል ኤኮኖሚ ሃብታም ያደርጋል፡ ሃብታም የሚያደርገው በተካበተው ገንዘብ ብቻ ሳይሆን በሰው ሃብታም ያደርጋል። ሁለት ጌቶችን ማገልገል አይቻልም፡ ሰይጣን በኪስ ነው የሚገባው አደራ ወንድሞቼ ከዚህ ዓይነቱ የገንዘብ አጠቃቀም ስልት እንጠንቀቅ።

ሌላው ትልቅ ችግር የገቢ ግብር ወይንም ከገቢ መጠን አንዱን ክፍል ለመንግሥት የሚከፈል ቀረጥ እንዲከፈል የሚያዘው ያንድ መንግሥት ሕግ የእርስ በእርስ መደጋገፍ ባህል የሚያጸናና መተሳሰብ እንዲኖር የሚያደርግ ነው፡ ነገር ግን ይኽ ሕግ አለ ማክበርና መጣሱ ብዙ ቤተሰቦች ከመሠረታዊ አስፈላጊ ጉዳዮች ተጠቃሚነት ያገላል። ስለዚህ ከቀረጥ ክፍያ ማምለጥ ድኾች እንዳይረዱ ማድረግ ይሆናል። ይኽ ደግሞ አቢይ ኃጢአት ነው፡ ተደጋግፎ የመኖር ኃላፊነትን ያስወግዳል። እንዲህ ሲሆን ርእሰ ንዋይነት ሥርዓት ተገለው የሚኖሩት የኅብረተሰብ ክፍሎችን ይፈጥራል የሚፈጥራቸው ድኾንችን ማየትም አይፈልግም። እንዳይታዩ ለማድረግ ተገለው የሚኖሩበት መንደር እንዲኖራቸው በማድረግ እንዳይታዩ ያደርጋ። ድኾቹ እርስ በእርሳቸው ብቻ እየተያዩ እንዲኖሩ ያደርጋል። በድኽነት የሚኖር እንዳይኖር እንጂ ድኻው እንዲፈጠር ካደርግክ በኋላ እንዳይታይ ማድረጉ ትልቅ ክፋት ነው፡

ለምሳሌ የአካባቢ ተፈጥሮ አየር የሚበክሉ የተለያዩ ኢንዳስትሪዎች ብከላው እንዲቀነስ ለሚደረገው ጥረት ማስፈጸሚያ በማለት ከገቢያቸው ትንሹን ክፍል ያውላሉ ወይንም ይለግሳሉ። የተለያዩ መቆመሪያ ቤቶች የቁማር ሱሰኞች ሆነው ለዚህ ዓይነት ተግባር ገንዘባቸው ንብረታቸውን የሚያባክኑ የስነ አእምሮ ሕክምና የሚያገኙብቸው ማእከሎች እንዲቋቋሙ ድጋፍ ያደጋሉ። የጦር መሥሪያ አምራቾችም በተለያዩ ግጭቶና ጦርነቶች ለሚጎዱት ሕጻናት ማከሚያ ቤቶች እንዲቋቋሙ  በሚደረገው ጥረት በመሳተፍ ድጋፍ ያደርጋሉ ነገር ግን ይኽ ዓይነቱ ሂደት በእውነቱ አስመሳይነትና ተመጻዳቂነት ነው።

ለዚህ ሁሉ ችግር ትክክለኛውና ተገቢው መልስ የሱታፌ ኤኮኖሚ ነው፡ ማንም ተገሎ እንዳይኖር የከተሞቻችንና የህልውና ጥጋውያን ክፍሎች እንዳይኖሩ ያደርጋል። ባጠቃላይ ሁሉም የሁሉም ስለሚያደርግ አብሮነት እንጂ ተነጣጥሎነት እንዳይኖር ያደርጋል። መልካም ሳምራዊ ብቻ መሆን በቂ አይደለም። ተረጂው እራሱን ችሎ ለመኖር የሚያስችለውም እድል መፍጠር ያስፈልጋል።

ብዙዉን ጊዜ ቤተ ክርስቲያንም ብትሆን ሁሉም ለማለት ይቻላል በቁጥር ማደግ ላይ በማተኰር ድኾን በመርሳት የሥልጣን ተቋሞች ሆነው ይታያሉ። ስለዚህ ኤኮኖሚያችን ለማዳን ከፈለግን የምድር ጨውና የኅብረተሰብ እርሾ ሆነን መገኘት ግድ ነው፡ ሱታፌን ማእከል ማድረግ እንጂ እንደ ርእሰ ንዋይነት ዘዴ ትርፍ ላይ በማተኮር አልፎ አልፎ መጽዋች መሆን አይጠቅምም፡ ይኽ አሰመሳይነትና ተመጻዳቂነት ነው፡

ድኾችን የሚያስቀድም የወጣቶች ተስፋን ብሩህ የሚያደርግ የኤኮኖሚ ስልት ያስፈልጋል። ሱታፌአዊ ኤኮኖሚም ገንዘብ ለብቻው እንደማያድን በማስተዋል ከገንዘብ በፊት ሰውን ማስቀደም የሚል፡ ትርፍ ለሁሉም የሚል ዘዴ ነው፡ ርእሰ ንዋያዊ የኤኮኖሚ ዘዴ መመጽወትን እንጂ ሱታፌን አያውቅም፡ ከማእድ የሚወድቀውን የሚያድል እንጂ በማዕድ የሚያሳትፍ አይደለም። አምስት ዳቦና ሁለት ዓሳ ሁሉንም ሊያጠግም ይችላል። በወንጌል አመክንዮ ያለህን ካልሰጠህ መቼም ቢሆን የምትሰጠው ብቂ አይሆንም፡ ስለዚህ አግላዩን ለሞት የሚዳርገውን ድኾችን የሚነጥለውን ትርፍ ብቻ የሚለውን ኤኮኖሚ እምቢ እንበል። ትርፍ ሱታፌን የሚፈጥር ሲሆን በዚህ ስልት የሚመራ ኤኮኖሚ ሲኖር ሁሉም የሁሉም ይሆናል ግብረ ሐዋርያት ምዕ. 4 ከቁጥር 32 እስከ 35 “ያላቸውም ሁሉ የጋራ ነበር እንጂ የራሱ የሆነውን ሃብት እንኳ እንደ ግሉ የሚቈጥር ማንም አልነበረን … ሐዋርያትም ስለጌታ ኢየሱስ ትንሣኤ በታላቅ ኃይል መመስከራቸውን ቀጠሉ፡1 በሁላቸውም ላይ ታላቅ ጸጋ ነበር። ከመካከላቸው አንድም ችግረኛ አልነበርም ምክንያቱም መሬትም ሆነ ቤት የነበራቸውን ሁሉ እየሸጡ ዋጋውን አምጥተው በሐዋርያት እግር ሥር በማስቀመጥ ለእያንዳንዱ በሚያስፈልገው መጠን ያካፍሉት ነበር” የሚለው ቃል የኤኮኖሚ ዘዴ መሆን አለበት፡ ሱታፌአዊ ኤኮኖሚ ማለትም እርሱ ነው፡ ሁሉም የሁሉ ሲሆን አንድም ችግረኛ አይኖርም። ሁሉም እንደሚያስፈገው መጠን ይካፈላል። ይኸንን ማሕብራዊ መደጋገፍ የኤኮኖሚ ማእከል መሆን አለብት የሚል ሃሳብ በሚያስታውስ ቅዉም ሃሳብ የለገሱት ሥልጣናዊ ምዕዳን ማጠቃለላቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.