2017-01-28 10:40:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የአርብ የጥር 19/01/2009 ዓ.ም. ዜና።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በክርስቲያኖች መካከል እውነተኛ የሆነ እርቅ ሊመጣ የሚችለው እኛ ክርስቲያኖች አንዳችን ለአንዳችን የተሰጠን ስጦታ መሆናችንን ስንቀበልና አንዳችን ከአንዳችን በትህትና መማር ስንችል ብቻ ነው ማለታቸው ተገለጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውም ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቅዱስነታቸው ይህንን መልእክታቸውን ያስተላለፉት ከጥር 10-17/2009 ዓ.ም. ለአንድ ሳምንት ያህል ለክርስቲያኖች ኅብረት ሲካሄድ የነበረው ጸሎት የማብቂያ ስነስርዓት ላይ ለተገኙ ከተለያዩ እህት አብያተ ክርስቲያናት የተውጣጡ ተወካዮች በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ በተገኙበት ቅዱስነታቸው በመሩት የመዝጊያ ጸሎት ቡኋላ ባስተላለፉት መልእክት መሆኑም ተዘግቡዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.