2017-01-25 16:56:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ የመልካም ዜና አመክንዮ እንጂ የክፋቱን መንፈስ ለትርኢት የማቅረብ አመክንዮ አንከተል


የቅድስት መንበር የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ኅየንተ የኔታ ዳሪዮ ኤድዋርዶ ቪጋኖ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንፃ ተገኝተው ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡበት  ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ 51ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ምክንያት ያስተላለፉት መልእክት እንደሚያመለክተው፥

በቅድሚያ የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የመልካም ዜና አመክንዮ እንጂ የሚከሰተው አሉታዊ ሁነት ለትርኢት የማቅረቡ አመክንዮ የሚከተል መሆን እንደማይገባው የሚመክርና ይኽ “ተስፋንና ባለንበት ጊዜ እማኔ ማገናኘት” በሚል ርእስ ሥር የሚመራ የዘንድሮው 51ኛው የዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ክርስቲያን ያንን የታሪክን እጅግ ግራጫማውን ሁነት የሚያበራው የወንጌል ህያው አገናኝ መሆን እንደሚጠበቅበት ያስገነዛባ,ል።

የመገናኛ ብዙኃን በሌላው ላይ ሊኖረን የሚችለው አሉታዊ ቅድመ ፍርድ እምቢ የሚል ገንቢና የግኑኝነት ባህል የሚደግፍ መሆን አለበት። ስለዚህ ጻርና ጭንቀት ላይ የሚጠነጠን መልካም ባልሆኑ ዜናዎች ገዛ እራሱን የሚያነቃቃ መገናኛ ብዙኃን ሳይሆን የመልካም ዜና አብሣሪ ይ አሆአ የመገናኛ ብዙኃን አስፈላጊ መሆኑ ቅዱስታቸው ባስተላለፉት መልእክት ሲያሳስቡ፥

የመገናኛ ብዙኃን ክፋትና መከራዊ ክስተት ችላ ሊለው አይገባውም ሆኖም የክፋቱን መንፈስ ለትርኢት የሚያቀርብ መሆን የለበትም

ፍርሃት ለማዛመት ፍርሃን የሚጠቁስ ሁነት ለማርገብገብና እይታው አሉታዊ ዜናዎች ላይ የማተኮሩ ሂደት ሊገታ ይገባዋል። እርግጥ ነው እንዲህ ሲባል መረጃ ከማቅረብ ኢመረጃ ማቅረብ ማለት አይደለም፡ በተያያዘ መልኩም ገራገር መሆን ገራገር ተስፈኛነት መንዛት ማለት አይደለም፡ ምክንያቱም እውነታው ማቅረብ ያስፈልጋል፡ እውነተኛውን ክስተትና መረጃውን ማቅረብ ሲባል ግን በመረጃው መነካት ያስፈጋል። አንድ ችግር ሲከሰት ችግሩ ዙሪያ ዜና ማቅረብ ተገቢ ነው ነገር ግን በጉዳይ ላይ ማስተንተን ማሰላሰልና በጉዳዩ ተአክቶም ለመልካም ነገር መታጠቅ የሚገፋፋ መሆን አለበት። የተከስተውን መጥፎ ዜና ላይ ማደንዘዣ መውጋት ተገቢ አይደለም። ወይንም መጥፎውን ዜና ማርገብገብ አያስፈልግልም። እንዲህ ካልሆነ ለትርኢት ማቅረብ ነው የሚሆነው።

መጥፎው ዜና ለመካም ዜና የሚገፋፋ መሆን አለበት፡ ተጨባጩና እውነታውን ማገናኘት ነው። ይኽ ደግሞ በመካምም ዜና አመክንዮ የሚመራ መሆን አለበት፡ ተጨባጩና እውነታውን ለይቶ በትክክል ለማንበብ ተገቢ መነጽር ማጥለቅ ያስፈጋልል። የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ክፍትና የፈጠራ ብቃት ሊኖረው ያስፈልጋል እንጂ መልካም ያልሆነውን ዜና የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ ዋና ተወናያን ማድረግ አያስፈልግም፡ ስለዚህ የመገናኛ ብዙኃን ተጨባጩን ክስተት ያሚያቀርብ ተስፋን የመጠቆም  ክህሎት ያለው መሆን አለበት። የተከሰተው አሉታዊ ዜና ያቀራረቡ ሂደት የችግሩ መፍትሔ ጠቋሚ ሊሆን ይገባል። ክስተተኖች በሚገባ አንብቦ ለማገናኘት የሚያስፈልግ ተገቢው መነጽሩ የመልካም ዜና አመክንዮ ነው። ስለዚህ የላቀው መልካም ዜና ደግሞ የኢየሱስ ወንጌል ነው።

እያንዳንዱ ክስተት ለመልካም ዜና አቅርቦት መድረክ መሆን አለበት

ያ መልካም ዜና ኢየሱስ ነው። ዜናው ዜና የሚያስብለውም ሕይወት አልቦ የሆነ ስቃይና መከራ የሚያቀርብ ሳይሆን መከራን በሙላት ገጽታው የሚኖር በመሆኑ ነው። ክርስቶስ ያንን የእግዚአብሔር ከሰዎች ሁነት ጋር እራሱን ቅርብ ያደረገበትና በላቀ ደረጃም በዚያ ሰብአዊ ሁነት ለመተባበር ዝቅ የማድረጉ ሕይወት ትስብእት ነው በማለት በመልእክታቸው ያብራሩት ቅዱስ አባታችን ነቢይ ኢሳያስን ጠቅሰው እትፍራ እኔ ካንተ ጋር ነኝ ከሚለው ቃል ጋር በማጣመር በማብራራት ኢየሱስ ክርስቶስ “እግዚአብሔር ለሰው ልጅ ካንተ ጋራ ነኝ እትፍራ ያለበት ሕይወት መሆኑ ገልጠው ፡ እግዚአብሔር በሕዝቡ ታሪክ ውስጥ እራሱን በማስገባት የገለጠው መልካም ዜና እለታዊ ሁነት የምናነብበት ታሪክ ነው። ፍቅር ሁሌ ለሌላው ቅርብ የሚያደርገው መንገድ አያጣም። ኢየሱስ የእግዚአብሔር መንግሥትን ለሰዎች ለማበሰር ምሳሌ ይጠቀም ነበር። ከዚህ በመንደርደርም ቅዱስ አባታችን ምስያና ዘይቤያዊ አነጋገር መጠቀም ያለው አስፈላጊነት አበክረው ዛሬም ጽንሰ ሃሳብ ከማቅረብ ይልቅ ምስያ መጠቀም ለመገናኛ ብዙኃን አገልግሎት እጅግ አስፈላጊ ነው።

የመገናኛ ብዙኃን ሠራተኞች ለዛሬ ሰው የመልካም ዜና ሕያው አገናኝ ይሁኑ

በእግዚአብሔር መንግሥት ዘር ላይ እማኔ ማኖር ያስፈልጋል፡ በትንሳኤ አመክንዮ የሚቀረጽ ግኑኝነት ነው የሚያስፈልገው። ይህ አመክንዮ በማንኛው ክስተትና ታሪክ በእያንዳንዱ ሁነት ውስጥ ያለውን መልካም ዜና እንድናይ ያደርገናል። ዛሬም ይላሉ ቅዱስ አባታችን መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ ሕያው መገናኛዎች አማካኝነት የእግዚአብሔር መንግሥት ላይ ፍላጎት እንዲኖረን የሚያደርግ ዘሩን ይዘራል። ማለትም በእነዚያ በዛሬው ታሪክ ውስጥ ያለው መልካም ዜና ሊያበስሩ ለመልካሙ ዜና ገዛ እራሳቸውን የሚፈቅዱና እነሆኝ የሚሉት ለዚህ ዓለም የብርሃን ጮራ ናቸው። ይኽ ጮራ ደግሞ መንገዶችን በማብራት አዲስ የእማኔና የተስፋ መንገዶችን ይከፍታሉ በማለት ያስተላለፉት መልእክት ይደምድማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.