2017-01-24 14:08:00

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው "መንፈስ ቅዱስን የሰደበ ኋጢያቱ ያቅር አይባልለትም" ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትንው እለት ማለትም በጥር 15/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት፣ ደናግላንና ምዕመና በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ያሰሙት ስብከት የክርስቶስ ክህነት ላይ ያጠነጠነ ሲሆን አስደናቂ ስለሆነው የክርስቶስ ክህነትና ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ፣ የእኛን ሐጥያት ለማስተሰረይ ራሱን በመስዋዕትነት ስላቀረበው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ትኩረቱን አድርጎ የነበረ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ክርስቶስ ሁልጊዜም ቢሆን በአባቱ ጎን ሆኖ ለእኛ እንደ ሚማልድ፣ እኛን ወደ አብ ለመውስድ ወደ ምድር ተመልሶም እንደ ሚመጣ ገልጸው እነዚህ ሦሶቱ ማለትም ለእኛ ሲል መስዋዕት መሆኑ፣ ሞቶ ሞትን ድል ነስቶ በአባቱ ጎን ሆኖ ለእኛ እየማለደ መሆኑና ዳግመኛ ወደ ምድር መጥቶ እኛን ወደ አባቱ እንደ ሚውስደን. . . እነዚህ 3ቱ የክርስቶስ የክህነት ደረጃዎች መሆናቸውንም ቅዱስነታቸው ገለጸው “መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ግን በፍጹም ሊሰረይ የማይችል ሐጥያት መሆኑንም” በአጽኖት ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት የክርስቶስ ክህነት በሚል አርዕስት ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ ያታወቀ ሲሆን በእለቱ በተነበበውና ወደ ዕብራዊያን ከተጻፈው መልዕክት በተወሰደው የመጀመሪያ ምንባብ ላይ ተመርኩዘው እግዚኣብሔር ከሰዎች ጋር የገባውን ቃል ኪዳን የሚማልደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

ኢየሱስ ሊቀ ካህን መሆኑንና የእርሱም ክህነት እጅግ ድንቅ የሆነ ክህነት መሆኑን በመግልጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም የክርስቶስ ክህነት አዲስ መዝሙር ለእርሱ እንድንዘምር ያስገድደናል ብለዋል።

የክርስቶስ ክህነት ሦስት ደረጃዎች አሉት በማለት በድጋሜ በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በብሉይ ኪዳን ጊዜ የነበሩ ካህናት በመስዋዕትነት ያቀርቡት የነበረው በአመት አንድ ጊዜ የሰውት የነበረው የእንስሳት ደም እንደ ነበረ ጠቅሰው ክርስቶስ ግን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለሐጥያታችን ስርዕዬት ራሱን መስዋዕት ማድረጉን ገልጸው በእዚህ ድንቅ በሆነ ተግባሩ እኛን ወደ እግዚኣብሔር አባቱ አቀረበን ከፍጡራን ጋር ኅብረት እንዲፈጠርም አደረገ ብለዋል። ክርስቶስ በሁለተኛ ደረጃ እያከናወነ የሚገኘው ድንቅ ነገር ዛሬ በእኛ ሕይወት ውስጥ እየፈጸመው የሚገኘውና ለእኛ የሚያደርገው ጸሎት ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እኛ እዚህ በምድር ላይ ሆነን ስንጸልይ እርሱ ደግሞ በሰማይ ሆኖ ለእያንዳንዳችን ይጸልይልናል፣ እምነታችን እንዳይቀንስ በአባቱ ጎን ሆኖ ለእኛ ይማልድልናል ብለዋል። “የካህናት ጸሎት በተለይም ደግሞ መስዋዕተ ቅዳሴን በሚያቀርቡበት ወቅት የሚያቀርቡት ጸሎት ልዩ የሆነ ኋይል አለው” ለእዛም ነው ብዙን ጊዜ ምዕመናን ካህናትን እባኮሆን ይጸልዩልኝ የሚሉት በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱነታቸው ሦስተኛው እና እጅግ አስደናቂው የክርስቶስ የክህነት ደረጃው ደግሞ ዳግም በሚመጣበት ወቅት ከኋጢያታችን ጋር የተገናኘ አመጣጥ ሳይሆን፣ ኢየሱስ ዳግም የሚመጣው “ፍጹም የሆነ መንግሥት ለመገንባትና እኛን ወደ አባቱ ሊወስደን እንደ ሚመጣ” ጨምረው ገልጸዋል።

“በሦስቱ የክርስቶስ የክህነት ደርጃዎች ውስጥ እጅግ ታላቅ ድንቅ ነገር አለ፣ ይህም ለአንዴና ለጨረሻ ጊዜ ኋጢያታችንን የቅር ማለቱ፣ አሁን ደግሞ በአባቱ ጎን ሆኖ ለእኛ መማለዱና እርሱ ዳግም ተመልሶ በሚመጣበት ወቅት ሰለሚፈጸሙ ተግባሮች የሚገልጽ ነው። በተቃራኒው “ይቅር የማይባል ኋጢያት አለ። ከኢየሱስ አፍ ይህንን መስማት በጣም ከባድ ነገር ነው። ነገር ግን ኢየሱስ ይህንን ተናግሩዋል ስለእዚህም እውነት ነው። “እውነት እላችኋለው ሰዎች የሚሠሩት ኋጢያትና የሚናገሩት ስድብ ሁሉ ይቅር ይባልላቸዋል- ልባቸውን ክፍት የሚያደርጉት ሁሉ ጌታ ይቅር እንደ ሚላቸውም እናውቃለን፣ የምንሠራቸውን ኋጢያቶችና የምንሳደባቸው ስድቦችን ጨምሮ ሁሉንም ኋጢያቶች ይቅር ይላል። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን የሚሳደበ ሰው ለዘለዓለም ይቅር አይባልም”።

“መንፈስ ቅዱስን የሚሳደበ ሰው ለዘለዓለም ይቅር አይባልም” የሚለውን ለማብራራት ታላቁ የክርስቶስ ክህነት የተቀባበትን ሚስጢር በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስ የተጸነሰው በመንፈስ ቅዱስ እርዳት መሆኑን፣ አንድ ካህን ደግሞ ሚስጢረ ክህነትን በሚቀበልበት ወቅት በቅባ ቅዱስ እንደ ሚቀባም በመጥቀስ፣

“ሊቀ ካህን የሆነው ኢየሱስ በእዚህ ቅባ ቅዱስ ተቀብቱዋል። ይህን የመጀመሪያ የሆነውን ቅባ ቅዱስ የተቀበለው የት ነበር? በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ከማሪያም ሥጋን በነሳበት ወቅት ነበር። ይህንን የሚሳደቡ ሁሉ የእግዚኣብሔርን ፍቅር ሥር መሠረት ይሳደባል፣ ይህም የደኅንነታችን መሰረት ነው፣ አዲስ ሰው ሆነን የተፈጠርንበት ነው፣ የኢየሱስን ክህነት መሳደብ ነው። “ነገር ግን ጌታ ይህንን ክፋት ይቅር የማይል ይመስላችኋልን? አይደለም እግዚኣብሔር ሁሉምን ኋጢያት ይቅር ይላል! ነገር ግን ይህ ኋጢያት ይቅር የማይባልም ብሎ ራሱን ዝግ የሚያደርግ ሰው ይቅር ለመባል የማይፈልግ ሰው ነው። ይቅር ይባል ዘንድ ራሱን ያላዘጋጀ ሰው ነው! ለእዚህም ነው መንፈስ ቅዱስን መሳደብ ጥሩ የማይሆነው። ይቅር ይባል ዘንድ ራሱን እንዳይከፍት ያደርጋል፣ ምክንያቱም የኢየሱስ ክህነት የተቀባበትን መንፈስ ቅዱስን በመካዱ የተነሳ ነው”።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማገባደጃ ላይ እንደ ጠቀሱት የኢየሱስ እጅግ ታላቅ የሆነ ክህነትና ይቅር የማይባል ስድብን በተመለከተ ጠለቅ ብለው ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት “ይቅር የማይባለው” ጌታ ሁሉንም ነገር ይቅር ለማለት ስላልፈለገ ሳይሆን፣ ነገር ግን ይህ መንፈስ ቅዱስን የተሳደበው ሰው ይቅር ያባል ዘንድ ራሱን ክፍት ባለማድረጉና ከኢየሱስ እጅግ ታላቅ የክህነት ሚስጢር በተቃራኒው በመሄዱ የተነሳ መሆኑንም ገልጸዋል።

“ዛሬ በእዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ኢየሱስ በመንበረ ታቦቱ ላይ ሕያው ሆኖ እንደ ሚኖር ማሰብ ጥሩ ይመስለኛል፣ ምክንያቱም በእውነት እርሱ ሕያው ስለሆነ፣ ራሱን የሰዋልን የመጀመሪያ ደረጃ የክርስቶስ ክህነት ከእኛ ጋር እዚህ ይገኛል። የእርሱ ሕያው የሆነ ሁለተኛው ክህነትም በእዚህ ይገኛል፣ ምክንያቱም እርሱ እዚህ ከእኛ ጋር እየጸለዬ ይገኛል። በተጨማሪም በእዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ላይ በቀጣይነት በምንጸልየው ‘አባታችን ሆይ’ በተሰኘው ጸሎትም ውስጥ ‘መንግሥትህ ትምጣ’ በምንልበት ወቅት የኢየሱስ ሦስተኛ ክህነት በእዛው ይገኛል። በእዚህ መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ስለእነዚህ መልካም ነገሮች እናስብ። ልባችን መቼም ቢሆን ለእርሱ እጅግ ድንቅ ለሆኑና በነጻ ለሚሰጡን ነገሮች እንዳይዘጋ ይረዳን ዘንድ ወደ ኢየሱስ እንጸልይ”።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.