2017-01-24 10:31:00

"ማርያምን ተመልከት፣ ጥራትም፣ አትጠፋምና!" ቅዱስ በርናዶስ።


ማርያምን ተመልከት፣ ጥራትም፣ አትጠፋምና!

ጌታችን በቅዱስ መስቀሉ ላይ ሳለ ለሰው ልጆች በሙሉ ሊሰጥ ያለውን  ልዩ ስጦታ በሐዋርያው ዮሐንስ በኩል አደረገው፤ እናም «ይህችውልህ እናትህ አለ፣ ለእርሷም እነሆ ልጅሽ» በማለት በእመቤታችንና በተከታዮቹ መካከል ያለውን የልጅና የእናትነት ትስስር በጉልህ አሳየ። በዮሐ. 19፡26-27 ላይ እንደምናነበው ቅ. ዮሐንስም ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ወደ ቤቱ ወሰዳት። ከዚያን ሰዓት ጀምሮ እስከ እድሜያችን ብዙ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች የዮሐንስ ወንጌላዊውን አደራ ተረክበው፣ የክርስቶስ በመሆናቸው እናቱንም እናታቸው በማድረግ በሕይወታቸው የእርሷን አብነትና አማላጅነት እንደ ትልቅ ትሩፋት ኖረው አልፈዋል። እመቤታችንም እናት የመሆን አደራዋን ልጅ ለሆኑላትና ለቀረቧት ከልጇ ጋር እያጣመረች ታቅፋቸዋለች። ከነዚህ የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች አንዱና «የእመቤታችን ዘማሪ» በመባል የሚታወቀው የ12ኛው ክ.ዘ. ቅ. በርናርዶስ ዘክለርቮ (ሲታዊ) ይጠቀሳል (ክብረ በዓሉ ነሐሴ 14 ነው)። በልዩ የአጻጻፍና አገላለጽ ዘዬው ስለእመቤታችን ማርያም ልዩ መንፈሳዊ ሥልጣንና ርኅራኄ በመደነቅ ልጇንና ጌታዋን በታማኝነትና በፍቅር ባሳደጉ፣ በያዙ እጆቿ መያዝን እንመርጥ ዘንድና እርሷ እናታችን ክርስቶስንም ወንድማችን ይሆኑ ዘንድ እንዲህ አለ፡-

ምንጭ ፣ የሲታዊያን ማሕበር በኢትዮጲያ

www.ethiocist.org/2014-12-05-15-37-40/our-lady/1386-2015-08-21-02-45-38

 








All the contents on this site are copyrighted ©.