2017-01-23 16:56:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ በዚህ ፈሳሽ ኅብረተሰብ ውስጥ የመልካም ሥራ ጥበበኞች ሁኑ


የቅዱስ ዶመኒኮ ገዳማውያን ማኅበር 800ኛው ዓመት ምሥረታ ምክንያት በማኅበሩ ውስጥ ለአንድ ዓመት ሲካሄድ የቆየው ኢዮበልዩ ዓመት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ጳጳሳዊ ቅዱስ ዮሐንስ ዘላተራኖ ባሲሊካ ባሳረጉት ምሥዋዕተ ቅዳሴ መጠናቀቁና ቅዱስነታቸው መሥዋዕተ ቅዳሴውን መርተው ባሰሙት ስብከት፥ ቀኑን በዓለም ውጫዊ ውበት ካለ መማረክ የወጌልን ትክክለኛውን ጣዕም በማጣጣምና የመልካም ሥራ ጥበበኞች ለመሆን ስላበቃቸው ብዙ ወንዶችንና ሴቶችን መልካም ተግባር ምክንያት ለእግዚአብሔር ክብርና ውዳሴ እናቅርባለን እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጋብሬላ ቸራዞ አስታውቋል።

ይኽ  ማራኪና ውስጥን የሚነካ ስሜት ዳግም እንዲደመጥና እንዲኖር ያደረገው የዛሬው ታሪካዊው ሁነት ያንን እ.ኤ.አ. ጥር 21 ቀን 1217 ዓ.ም. በዚህ በላተራነንሰ ር.ሊ.ጳ. ሖኖሪዩስ ሦተኛ ድልው በማለት ያንን በስፐይን ተወላጁ ቅዱስ ዶመኒኮ ዘጉዝማን የተመሠረተው ገዳማዊ ማኅበር በይፋ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲወለድ ሲያደርጉ የነበረው ታሪካዊ ሁኔታ እዲኖር የሚያደርግ ነው። በዚያን ዕለት በይፋ የተነቃቃው የማኅበሩ የሰባኪነት መንፈሳዊ ጸጋ በቁጥራቸው አነስተኛ በሆኑት ሕይወታቸው ለወንጌል ሴባኪነት በሰጡት የተጀመረው ዛሬ በቁጥር እጅግ ብዙ ካህናትና ወንድሞችን በአባልነት ያቀፈ በመምህር አባ ብሩኖ ካዶረ የሚመራው ገዳውያን ማኅበር ዛሬም በታማኝነት ያ በቅዱስ ዶመኒኮ የተነቃቃው መንፈሳዊ ተግባር በቤተ ክትርስቲያን ውስጥ ያለው ሱታፌው እያደሰ ይገኛል።

በእያንዳንዱ ዘመን ዛሬም ልክ ቅዱስ ዶመኒኮ እንደ ነበረበት ወቅት፡ የዛሬ ሁለት ሺሕ ዓመት በፊት ቅዱስ ጳውሎስ ለተከታዩ ጢሞቴዎስ በጻፈው መልእክት ዘንድም ሁለት ተጻራሪያን ሰብኣዊ ሁነቶች መኖሩን እንድረዳለን። በአንድ በኩል የዓለም የመጓጓት ፍንጥዝያ በሌላው ረገድ ደግሞ በመልካም ተግባር አማካኝነት እግዚአብሔር የማመስገን ሁነት እንዳሉ ናቸው፡ እነዚህ ሁለት ተጻራርያን ተግባሮች ነበሩ ዛሬም አሉ። ቅዱስ ጳውሎስ ለጢሞቴዎስ በዚያ አዳዲስ መምህራን የነበርያ ነበር የተለዩ ጠመቅ ትምህርቶችና ርእዮተ ዓለም ይሻ በነበረው ሕዝብ መካክል ወንጌል ሊሰብክ እንደሚገባው ያስጠነቅቀዋል።  ያንን ፈንጠዝያ ዓለማዊነት በሚታይበት ዓለማዊ ማራኪነትና አታላይነት ሁነት ውስጥ ቅዱስ ጳውሎስ ጠንካራ ቃላቶችን በመጠቀም ደቀ መዝሙሩን በሚገባ እንዲሰናዳ ያስገነዝበዋል። ጽና ሳትፈራ ገስጽ ሲያፈልግም ተቆጣ ምዕዳን ስጥ ንቃ ስቃይ ተጋፈጥ ሲል ይመክረዋ። 

ያጢሞቴዎስ በነበረበት ዘመን የነበረው ዓለማዊ ፈንጠዝያ አሁን በዚህ ባለንበት ዘመን ተስፋፍቶ በዓለማዊነት ትሥሥር ደረጃ የእኔነኝነት ተዛማጅ ባህል ሆኖ ይታያል። አዳዲስ ነገራትን መፈለግ በትክክል የሰው ልጅ ባህርይ ነው። በዚህ መሆንነት ሳይሆን ውጫዊነት በሚል ፍጆት ብቻ በሚለው አስተሳሰብ ሥር ስሙን ቀየር በማድረግ እውነት ተመስሎ ይቀርባል። ይኽ ደግም አንድም የጸና ራእይ የሌለው ጠንካራ የሆኑትን ባህላዊ ሰብአዊ ማኅበራዊ እሴቶች ያጠፋ ፈሻሽ ማኅበረሰብ ፈጥሯል። ጠፊውን ነገር ላይ የሚያተኵር ተጠቅሞ መጣል የሚለው ባህል የሚኖር ኅብረተሰብ፡ እሴታዊ መልህቅ የሌለው።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የማቴዎስ ወንጌል ጠቅሰው ቤተ ክርስቲያን ለዚህ ለተደናገረው ጸንቶ የሚቆምበት እሴት ያጣ የሕይወት መሪ እሴት የሌለው ጥልቀት የሌለው እውነተኛ በዓል መሳይ ለሚኖረው መታየትን ለሚለው ፈሻሽ ኅብረተሰብ መልካም ሥራዎች አማካኝነት ያንን በሰማየ ሰማያት ያለው እግዚአብሔርን የሚወድስ የሚቀድስ እውነተኛውን በዓል ለይቶ እንዲያውቅ ታደርጋለች።፡ ኢየሱስን የሚከተሉ የምድር ጨውና ብርሃን ናቸው፡ ጨውና ብርሃን በመሆን መልስ መስጠት፡ ትላንትናም ዛሬም ለዚያ ፍንጥዝያ ለሚለው መታየትን እንጂ መሆንን የማይወድ ዓለም ኢየሱስና ቤተ ክርስቲያን መልካም ተግባር አማካኝነት እውነተኛ መልስ ይሰጣሉ። ቤተ ክርስቲያን በኢየሱስ ተመርታ በጸጋው አማካኝንትም መልካም ተግባሮች ለፈሳሹ ኅብረተሰብ እውነተኛውን ሕይወት ትመሰክራለች። ወንጌል በቃልና በሕይወት በመስበክ የሚሰጥ መልስ ታመላክታለች እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸራዞ አያይዘው፥ ቅዱስ ደመኒኮ ብዙ ወንዶችና ሴቶች የመልካም ሥራ ሠራተኞች እንዲሆኑ አድርጓል። ወንድ ሴት መንፈሳዊ ማህበርና ቤተ ክርስቲያንም ትሁን ጣዕሙን የሚያጣ ሁሉ ወዮውለት። ቅዱስ ዶመኒኮ በክርስቶስ ብርሃን ቦግ ብሎ በክርስቶስ ጨው ጣዕም ታድሎ በቃልና በሕይወት ወንጌልን አገለገለ። ለዚህ መልካም ሥራው እግዚአብሔርን እንወድስ። በመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አማካኝነት በዚያ በተቀበለው ስጦታ ብዙ ወንዶችና ሴቶች በዚህ በዓለም ፍንጥዝያ እንዳይዋጡ አደረገ። ያንን ጤናማውን የወንጌል ጠመቅ ትምህርት እንድናዳምጥ ረዳን። ብዙዎች የዚህ መልካም ተግባር ጥበበኞች በመሆን በሕይወታቸው ጌታን ይወድሳሉ፡ ጌታን ማወደስን በቃልና በሕይወት ያስተምራሉ በማለት ያስደመጡት ስብከት ማጠቃለላቸው አስታወቁ።








All the contents on this site are copyrighted ©.