2017-01-16 16:55:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐውፆተ ኖልዎ በሮማ ክፍለ ከተማ ሰተቪለ ዘጉይዶኒያ ቁምስና ዘቅድስተ ማርያም


ቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም. በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከሰዓት በኋላ ልክ ሦስት ሰዓ ከአርባ ደቂቃ ገደማ ለሐውፆተ ኖልዎ በሮማ ክፍለ ከተማ ሰተቪለ ዘጉይዶኒያ ወደ ሚገኘው ቅድስተ ማርያም ቁምስና እነደረሱ እዛው የሚገኙትን የቁምስናው ምክትል ቆሞስ 50 ዓመት ዕድሜ ያላቸው በጡንቻ መስለል በሽታ ከተጠቁ ይኸው ሁለተኛውን ዓመታቸውን ያገባደዱትን ኣባ ጁዘፐ በራርዲኖን ጎብኝተው ከሳቸው ጋር የ 10 ደቂቃ ቆይታ በማድረግ በማጽናናት ምስጢረ ቀዲል ሠርተው ከባረኳቸው በኋላ ተሰናብተው የቁምስናውን የተለያዩ ተጨባጭ የሐዋርያዊ ግብረኖልዎ ማኅበራት ጋር የተገናኙ ሲሆን፡ ከ 30 በላይ የሚገመቱት በእድሜ የገፉና እንዲሁም የተለያየ ሕመም ካጋጠማቸው የቁምስና አባላት፡ እ.ኤ.አ. በ 2016 ዓ.ም ምስጢረ ጥምቀት የተቀበሉት ከወላጆቻቸው ጋር ተቀብለው አዛውንቶች በእድሜ የገፉት የኅብረተሰብ ሕያው ተዘክሮ የሆኑትን መንከባከብና ማፍቀር ኃላፊንት ብቻ ሳይሆን ስብአዊና ክርስቲያናዊ ጥርያቸውን መሆኑና በተጨማሪም የቤተሰብ አስፈላጊነት ዙሪያ ምክር ለግሰው እንዳበቁም፡ የቅድስት መርያም ሰተቪለ ዘጉይዶኒያ ቆሞስ አባ ልዊጂ ተዶልዲን በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ከሚተባበሩዋቸው ከመቶ በላይ ከሚገመቱት የቁምስና ምእመናን ጋር ተገናኝተው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎና ወንጌላዊ ልኡክነት ዙሪያ ምዕዳን መለገሳቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ቅዱስነታቸው ከካህናትና ከቁምናው አምስት የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ጋር ከተገናኙ በኋላ ወደ ማናዘዣ ስፍራ በመሄድ በጅማት መስለል በሽታ የተጠቁትን ምክትል ቆምስ አባ በራርዲኒን የሚንከባከቡ ባለ ትዳሮች በተናጥል አንድ የድኅረ ምሥጢረ መሮን ትምህርተ ክርስቶ  በመከታተል ላይ የሚገኘው ወጣትና የአንድ እጅግ በሕመም ላይ የሚገኝ ወጣት ወላጅ አባት  በማናዘዝ ምስጢረ ንስሐ ሠርተው እንዳበቁም፡ ልክ በሮማ ሰዓት አቆታጠር ከሰዓት በኋላ አምስት ሰዓት ከአርብ ደቂቃ በቀጥታ መሥዋዕተ ቅዳሴ መሥራታቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ቅዱስ አባታችን በላቲን ሥርዓት የዕለቱ ምንባባት ትንቢተ ኢሳያስ ምዕ. 49 ቁ. 3 ከቁ. 5-6፡ ሁለተኛ ምንባብ አንደኛ ቆሮንጦስ ምዕ. 1 ከቁ. 1-3፡ የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 1 ከቁ. 29-34 ያለውን በማስደገፍ በለገሱት ስብከት፥ “ … ዮሓንስ በማግሥቱ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ … ‘እነሆ! የዓለም ኃጢኣት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ። ከእኔ በኋላ የሚምጣው ከእኔ በፊት ስለ ነበር ከእኔ ይልቃል” መሲሕ እርሱ ነው። ይኸንን የሰሙ ደስ ተሰኝተውም በመሄድ “መሲሕን አገኘነው አሉ” (ዮሓ.1,41) … እንዴት ወደ ኢየሱስ ለመሄድ ተነሱ ከእርሱ ጋር እንዴትስ ተገናኙ?በማለት የጠየቁት ቅዱስ አባታችን መልሱም ይላሉ ስለ ኢየሱስ የተናገራቸው ኢየሱስን የሰበከላቸው ታማኝ መስካሪ በማግኘታቸው ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታወቀ።

ብዙ ምእመና ካህናት ጳጳሳት ኢየሱስ ጌታ ነው በማለት የእምነት ኑዛዜ ይፈጽማሉ፡ ሆኖም እንዲህ ሲሉ ኢየሱስን ነው የሚመሰክሩት? እምነት እንደ የእግር ኳስ ብድኖች ደጋፊ በሆነ መንፈስ መኖር ማለት ነውን? አይደለም ሆኖም ክርስቲያን መሆን ግብረ ገብ ሕጎችን አክባሪ ማለት ሳይሆን ኢየሱስን መኖርና መመስከር ማለት ነው። ደቀ መዛሙርት ይኸንን ነው ያደረጉት። እነርሱ በሰጡት የቃልና የሕይወት ምስክርነም ክርስትና ተስፋፋ። ደቀ መዛሙርት መስካሪያን ለመሆን የተሰጣቸው የትምህርት ሕንጸት አልነበረም። ኃጢአተኞች ነበሩ። ቀዳሚው ሥልጣን ሊሰጣቸው የተመኙ እርሱ በሞት እንደተለየም ፈርተው በራቸውን ውስጥ ዘግተው የተደበቁ ነበሩ፡ ኢየሱስ ሲያዝም የሸሹ፡ ጴጥሮስ ቀዳሜ ር.ሊ.ጳ. ሆኖ በኢየሱስ የተመረጠው  ኢየሱስ ወደ ሚሰቀልበት ሥፍራ በመወሰድ ላይ እያለ በካህናት አለዎች የእርሱ ተከታይ ነህን በማለት ኢሰጠየቅ፡ አይ እኔ አላውቀውም ሲል የከዳው። ሆንም ምኅረት ላይ ታምነው ተለውጠው ኢየሱስን በመመስከር ሰማዕትነት ተቀብሏል። “ጌታ ሆይ ኃጢአተኛ ነኝና ከእኔ እራቅ” (ሉቃ. ምዕ. 5 ቍ. 8) የኢየሱስ መስካሪ መሆን ፍጹም መሆንን አይጠይቅም። ኃጢአተኛ መሆንህን መታመን በምሕረቱ ማመን ነው የሚያስፈልገው።

ደቀ መዛሙርት፥ ከድተዉታል ፈርተው ተደብቋል፡ በኃይሉ አልታመኑም፡ ይኽነንን የፈጸሙት ለመሆናቸው የዚህ የፈጸሙት ኃጢአት ዝርዝር ሁሉ በወንጌል ተጽፎ እናገኘዋለን ነገ ግን እርስ በእርሳቸው ይተማሙ ነበር የሚል ደቀ መዛሙርት የፈጸሙት ኃጢአት ግን አናነብም። አዎ መተማመትና ሐሜትን ጨርሰው የማያውቁ ነበሩ። አንዱ ሊላውን የማማትና ክፉ የመናገር ስም ይማጥፋት ኃጢአት እንዳልፈጸሙ ነው። እስቲ መለስ ብለን ቁምስናችን ማኅበረ ክርስቲያናችንን እናሰብ፡ በምላሳችን ቆዳን መላላጥ፡ እከሌ እንዲህ አደረገ እርሱ እርሷ እንዲህ አደረገች፡ አንዲህ አለ እዲህ አለች አየተባባልን በመተማማት ለምስክርነት ሳንብቃ እንቀራለን።

ፍጹም ቁምስና የምትመኙ ከሆነ ኃጢአተ የሌለባት ሳይሆን ኃሜት የማይፈጸምበት ማኅበረ ክርስቲያን የሚኖርበትን መፈለግ ነው። ፍጹም የሚባል ቁምስና ከማማት ነጻ የሆነ ቁምስና ነው። ሁላችን ኃጢአተኞች ነን፡ መተማማትና ኃሜተኛነት ግን ማኅበረ ክርስትያንን ያፈርሳል እንዳሉ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ ፥ቅዱስ አባታችን ለቁምስናው አባላት የሳቸው በዚያ ለሐውፆተ ኖልዎ መገኘት ሁሉም የዚያ ቁምስና ማኅበረሰብ እርስ በእርስ ላለ መተማማት፡ አንዱ ሌላውን በምላሱ ሳያስቀይም በልቡ ክፉ ላለ ማሰብ ቁርጥ ፈቃድ ለማረግ የሚያነቃቃ እንዲሆንላቸው ተመኝተውም፡ ለማማት ሲቃጣህ ምላስሕን ቆርጠም አድርግ፡ ምላስህ ስለ ቆረጠምክ ሊያምህና ምላስህም ሊያብጥም ይችል ይሆናል ሆኖም ማማት ከምላሱ ማበጥ እጅግ ከፍ ባለ ደረጃ የሚያሳምም መንፈስንና ስጋን የሚጎዳ ነው። የኢየሱስ ተከታዮች ክደዉታል፡ አናውቀውም ብለው ከእርሱ ሸሽቷል ይኽ ደግሞ ወንጌል የሚያረጋግጠው እውነት ነው ነገር ግን ሲተማሙ ወይንም እርስ በእርሳቸው ሲተማሙ የሚናገር አንድም ቃል አናገኝም። ሁላችን አዎ ኃጢአተኞች ነን ነገር ግን ምስክሮች እንሁን። ቀደምት ክርስቲያኖች የሰጡት ምስክርነት ፍቅር ነው። በመካከላቸው የነበረው የእርስ በእርስ መዋደድ እና መፋቀር ነበር የመሰከሩት። የእኔ ተከታዮች መሆናችሁ በመካከላችሁ ባለው ፍቅር ይመስከር ያለው የጌታችን ኢየሱስ ፍቅር ህያውነቱ የመሰከሩ ናቸው ክርስቲያኖች ከሆን እንደ እነርሱ እንሁን እርስ በእርስ የሚተማማ ሳይሆን የሚፈቃቀር የፍቅር ማእድ እንሁን። ጌታ ከእርስ በእርስ መተማማት ያቅበን ላለ መተማማት ጸጋውን ይስጠን፡ አመስገናልሁ በማለት ያስደመጡት ስብከት እንዳጠቃለሉ አስታውቋል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ, መሥዋዕተ ቅዳሴ አጠናቀው በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ወደ መንበራቸው ለመመለስ ከመነሳታቸው በፊት ቀደም በማድረግ ቅዱስነታቸው ሰላም ለማለት ይጠባበቁ ወደ ነበሩት በብዙ መቶዎች ወደ ሚቆጠሩት ቤተ ክርስቲያኑ በምእመናን ብዛት በመጨናነቁ ምክንያት ከቁምስናው ውጭ በተተከለው በየድምጽ ርእየት መሣሪያ አማካኝነት ይከታተሉ ወደ የነበሩት ምእመናን በመሄድ ቀረበው ሰላማታቸውን ሐዋርያዊ ቡራኬ በመስጠት ያካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ማጠናቀቃቸው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ይጠቁማል። 








All the contents on this site are copyrighted ©.