2017-01-11 16:50:00

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፥ ችግረኞችንና ድኾችን በማገልገሉ ረገድ ክርስቲያኖች ውህደት ይኑራቸው


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሌ በእያንዷ ወር በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የጸሎት ሃሳብ ምን መሆን እንዳለበት የሚሰጡት ምዕዳን  መሠረት እ.ኤ.አ. ጥር ወር 2017 ዓ.ም. “ክርስቲያኖች በሙሉ የሰውን ልጅ ተጋርጦዎችን በመግጠም አገልግሎት” የሚል ሃሳብ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ጸሎት እንዲሆን ባስተላለፉት የድምጸ ራእይ መልእክት አማካኝነት ይፋ ማድረጋቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ አስታወቁ።

ይኽ የጸሎት ሃሳብ በዚያ በአንድ መቶ አገሮች በሚገኘው እ.ኤ.አ.  በ 1844 ዓ.ም. በተቋቋመው ዓለም አቀፍ የጸሎት ድረ ግኑኝነት ማኅበር በአደራ የሚሰጥ ሲሆን፡ ይኽ ማኅበር በመላ ዓለም በሚገኙት መናብርቶቹ አማካኝነትም በዚህ እ.ኤ.አ. 2017 ጥር ወር ማኅበረ ክርስቲያን ሁሉ በዚህ የቅዱስነታቸው የጸሎት ሓሳብ ላይ የተማከለ መንፈሳዊና ሰብአዊ አገልግሎቶች ያነቃቃል። በተያያዘ መንገድም በማላይቱ ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የጸሎት ሃሳብ ተብሎ በመሥዋዕተ ቅዳሴና በተለያዩ የጸሎት ሥነ ስርዓት ውስጥ ታስቦ ይጸለያል።

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላፉት የድምጸ ራእይ መእክት አማካኝነትም፥

በጋራ የመጓዝ ፍላጎት እርሱም ድኾችን በችግር ላይ የሚገኙትን በማገልገል በግብረ ሠናይ ዘርፍ መተባበር ለሁላችን የሐሴት ምንጭ ነው። ስለዚህ በጸሎና በግብረ ሠናይ በድኽነትና በችግር ላይ ለሚገኙ ወንድሞቻችን ቅርብ እንሁን፡ እንዲህ በማድረም የዘንድሮው የክርስቲያኖች አንድነት እውን እንዲሆን ታልሞ በየዓመቱ በጥር ወር የሚካሄደው የጸሎት ሳምንት፡ የክርስቲያኖች አንድነት ጎረቤትን (ድኻው፡ ችግረኛው) በማፍቅርና በማገልገል ላይ የጸና ውህደት በሚል መርህ የተመራ እንዲሆን ማመልከታቸው ጂሶቶ ጠቅሷል።

ድምጾቻችሁ ከድምጼ ጋር አስተባብሩ፥ ያሉት ቅዱስነታቸው አያይዘው የአቢያተ ክርስቲያን ምሉእ ውህደት እውን እንዲሆን ሁሉም በጸሎትና በወንድማዊ ግብረ ሠናይ አማካኝነት አስተዋጽኦ ይኑረው ሲሉ፡ የዓለም አቀፍ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የጸሎት ሃሳብ ድረ ማኅበር ዋና አስተዳዳሪ የኢየሱሳውያን ልኡካነ ወንጌል ማኅበር አባል አባ ፍረደሪክ ፎርኖስ በበኩላቸውም ያንን የቅዱስ አባታችን የጸሎት ሃሳብ በመቀበል፥ “በተጨባጩ ዕለታዊ ሕይወት በእምነትና በምስክርነት አማካኝንት የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ወደ ውህደት የሚያደጉት ጉዞ እንዲመሰክሩና ኢየሱስ ሁሉም አንድ እንዲሆኑ በልበ ሙላት ወደ አባቱ ያቀረበው ጸሎት እርሱም እንተ በእኔ እኔም በአንተ እንዳለሁ እንዲያውቁና እነርሱም በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ የሚል ይኽም ኢየሱስ ከአብ መላኩ ዓለም አንዲያምን የሚል ሲሆን፡ እኛ ኢየሱስ ከአብ መላኩ የምናምን ሁሉ አንድ ልንሆን ይገባናል። የቅዱስ አባታችን የጸሎት ሃሳብ ውህደት በጸሎትና በግብረ ሠናይ ይገለጥ የሚል ነው በማለት ማብራሪያ እንደሰጡበት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂኮቲ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.