2017-01-10 10:33:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የሰኞ የጥር 1/2009 ዓ.ም. ዜና።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በታኅሣሥ 30/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለጠቅላላ አስተምህሮ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ገለጹት በየጎዳናው ላይ ለሚኖሩ ቋሚ የመኖሪያ ስፍራ ለሌላቸው ሰዎች መጸለይ እንደ ሚገባ ማሳሰባቸው ተገለጸ።

የእዚህ ዜና ሙሉ ይዘቱን ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቅዱስነታቸው ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት በእለቱ እንደ ጎሮጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የተከበረውን የጌታችን የመዳኋኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ የተጠመቀበትን ቀን በሚዘከርበት የጥምቀት በዓል መስዋዕተ ቅዳሴን ካሳረጉ ቡኋላ ሲሆን ይህንንም የጥምቀት በዓል ማዕከል ባደረገው የጠቅላላ አስተምህሮዋቸው እንደ ገለጹት ኢየሱስ በዩሐንስ ለመጠመቅ በመጣበት ወቅት ዩሐንስ ኢየሱስን አንተ ነህ እንጂ እኔን የምታጠምቀኝ እኔ አንተን ማጥመቅ አይገባኝም በማለት ልያስቆመው ሞክሮ እንደ ነበረም ገልጸዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.