2017-01-10 10:18:00

ቅዱስነታቸው ቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት 28 ሕፃናትን ማጥመቃቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በታኅሣሥ 30/2009 ዓ.ም. እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የተከበረውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አስመልክተው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት 28 ሕፃናትን ማጥመቃቸው ተገለጸ።

የእዚህን ዜና ዝርዝር ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ሕጻናት የመጀመሪያ እምነታቸውን የሚጎናጸፉት በጥምቀታቸው ቀን መሆኑን ገልጸው እምነት ማለት አሉ ቅዱስነታቸው እምነት ማለት በሰንበት እለት ጸሎተ ኋይማኖትን መድገም ማለት አይደልም ካሉ ቡኋላ ነገር ግን በእውነት እና በእግዚኣብሔር በማመን ለሌሎችም ይህንን እምነታችንን በሕይወታችን በሚገለጽ ምስክርነት ማስተማር ማለት ነው ብለዋል።

እምነት በልባችን ውስጥ የሚያድግ ብርሀን ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ለእዛም ነው ሰው በሚጠመቅበት ወቅት የእዚህ ብራሃን ተምሳሌት የሆነው ሻማ ይዞ የሚጠመቀው ብለዋል። በጥንት ጊዜ ሚስጢረ ጥምቀት መብራት የሚል መጠርያ ነበረው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም በጥምቀት የምንቀበለው እምነት ነገሮችን ለየት ባለ መንገድ እንድንረዳ ስለሚያደርገን ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ልጆቻቸውን ለማስጠመቅ በእዚያ ለተገኙ ወላጆች ባስተላለፉት መልዕክት እንደ ገለጹት “ልጆቻችሁ ለሌሎችም ምስክር ይሆኑ ዘንድ በጥምቀት የተቀበሉትን እምነት ኮትኩቶ የማሳደግ ኋላፊነት አለባችሁ” ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.