2017-01-10 11:49:00

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮ የሁሉም ሐይማኖት መሪዎች በእግዚኣብሔር ሥም የሚፈጸመውን የአሸባሪዎች ጥቃት እንዲያወግዙ አደራ አሉ።


ርዕሰ ሊቅነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በጥር 1/2009 ዓ.ም. የሁሉም የሐይማኖት ተቋማት መሪዎች የእግዚኣብሔርን ሥም ያለቦታው በመጠቀም ለሽብር ተግብራቸው ማስፈጸሚያ የሚያውሉትን ሰዎች ሁሉ በድፍረት ያወግዙ ዘንድ ጥሪ ማቅረባቸው ተገለጸ።

እንደ ጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የተከበረውን አዲስ ዓመትን አስምልክቶ የተለያዩ ሀገራትን በመወከል የቅድስት መንበር ሉዑካን ከሆኑ የዲፕሎማሲ አካላት ጋር ቅዱስነታቸው በተገናኙበት ወቅት እንደ ገለጹት “ማንም ሰው በእግዚኣብሔር ሥም ተጠቅሞ ነብስ ማጥፋት ተገቢ አይደለም” ካሉ ቡኋላ በአሁኑ ወቅት ግን ዓለማችን “በእብደት የእግዚኣብሔር ሥም ያለ አግባቡ በመጠቀም ሞትን በመዝራት የበላይነትን እና ስልጣንን ለማግኘት በተነሱ ነውጠኞች እየተሞላች መምጣቱዋን ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው የተለያዩ ሀገራትን በመወከል የቅድስት መንበር ልዑካን ለሆን የዲፕሎማሲ አካላት እንደ ገለጹት “አክራሪ አሸባሪነት የመንፈሳዊ ድኽነት ፍሬ በመሆኑ ይህም ከማኅበራዊ ድኽነት ጋር ቁርኝት እንዳለውም” ገልጸው የህም የአሸባሪዎች ጥቃት ሙሉ በሙሉ ሊወገድ የሚችለው የሐይማኖት እና የፖሌቲካ መሪዎች በሚያደርጉት የተቀናጄ ተግባር መሆኑንም” ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው የተለያዩ ሀገራትን በመወከል የቅድስት መንበር ልዑካን ለሆኑት የዲፕሎማሲ አካላት ልማዳዊ በሆነው እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ መልእክታቸው ወቅት ያስተላለፉት መልእክት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው ሰላም እና ደኽንነት በሚሉት ሁለት ጭብጦች ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን በእዚህ አመት ለየት ባለ ሁኔታ ያሰተላለፉት መልዕክት 34 አንቀጾች እንደ ነበሩትም ለመረዳት ተችሉዋል።

ቅዱስነታቸው አክለውም እንደ ገለጹት “ዛሬ በዓለማችን የሚታየውን ጠቅላላ ሁኔታ ከግምት በማስገባት፣ ስለ መጭው ጊዜ አስተማማኝነት እና አሳቢነት በምንጨነቅበት በአሁኑ ወቅት ወደ ፊት መጓዝ መጀመር እንድንችል እና አንድ መንገድ ላይ እንድንጓዝ ስለሚረዳን ስለ ተስፋ መነጋገር ስአስፈላጊ ሆኖ ይሰማኛል” ካሉ ቡኋላ በጦርነት እና ግጭት የሚታመሱ አንድ አንድ የዓለማችን ክፍሎችን በዋቢነት ጠቅሰዋል።

“እነዚህ አክራሪ የሽብር አካላት ባነሳሱት ግጭት በዓለማችን ዙሪያ በሚገኙ ሀገራት በአለፈው አመት ከፍተኛ እልቂትን አስከትለዋል ያሉት ቅዱስነታቸው የእዚህ አደጋ ሰለባ ከሆኑት ሀገራት መካከልም አፍጋኒስታን፣ ባንግላዲሽ፣ ቤልጄይም፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ግብፅ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ዮርዳኖስ፣ ኢራቅ፣ ናይጀሪያ፣ ፓኪስታን፣ አሜርካ፣ ቱኒዚያ እና ቱርክ እንደሚገኙበት ገልጸዋል።

“እነዚህ ለመግደል ልጆችን የሚጠቀሙ ክፉ ተግባራት ናቸው፣ በዋቢነትም በናይጄሪያ በጸሎት ላይ የነበሩ ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት፣ በግብፅ በኮፕቲክ ካቴድራል ላይ የተደረገ የሽብር ጥቃት ወይም ደግሞ በመንገደኞች እና በሠራተኞች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ለምሳሌም በብራሰልስ ወይም ልክ በፈረንሳይ በኒስ ከተማ እና በጀርመኑ በርሊን ከተማ ለእየራሳቸው ጉዳይ ከቤታቸው በወጡ ሰዎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት እንደዚሁም በቱርክ እስታንቡል ሰዎች የአዲስ ዓመት ውዜማን በሚያከብሩበት ወቅት እንደ ተፈጸመው የአሸባሪዎች ጣቅት ያሉትን” በዋቢነት መጥቀስ እንደ ሚቻል ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸው የዓለም ማኅበረሰብ ለሰላም ግንባታ የበኩሉን እገዛ እንዲያደርግ ጨምረው አሳስበዋል።

“ሰላም” አሉ ቅዱስነታቸው “ሰላም ስጦታ፣ ተግዳሮት እና ቁርጠኛነትን” ይጠይቃል ካሉ ቡኋላ እያንዳንዳችን እና በአጠቃላይ ሁላችን ይህንን ሰላም እንድንቀበል፣ መልስ እንድንሰጠው እና በጥንቃቄ አጥብቀን እንድንይዘው እና ለሌሎችም ጥቅም ማዋል እንደ ሚገባን አሳስበው መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.