2016-12-26 15:30:00

ብፁዕ ካርዲናል ዛናሪ፥ ሕፃናት እጅግ ለስቃይ የተዳረጉበት ዓለም


በሶሪያ የቀጣጠለው ጦርነት ይኸው ስድስተኛው ዓመቱን እያስቆጠረ ባለበት በአሁኑ ወቅት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. በዓለ ልደት መከበሩ ሲገለጥ፡ በሶሪያ የቅድስት መንበር ሐዋያዊ ልኡክ ብፁዕ ካርዲናል ዛናሪ በደማስቆ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፥ በሶሪያና በጠቅላላ በተለያዩ ግጭት በሚታይባቸው የዓለማችን ክልሎች በእጅጉ ለስቃይ የሚዳረጉት ሕጻናት ሴቶችና በእድሜ የገፉ ናቸው፡ በተለይ ደግሞ የሕጻናት ስቃይ ላይ ያተኮረ ስብከት የለገሱ ሲሆን። ብፁዕነታቸው ከቅዳሴው ፍጻሜ በኋላ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ፥ በዓለ ልደት የኢየሱስ ሕፃን በዓል ነው። የቅድስት ቤተሰብ በዓል ነው ካሉ በኋላ በቀጥታ የሶሪያ ሕፃናትን በማሰብ በዚያ ክልል ባለው ግጭትና ሁከት እጅግ ተጠቂው ሕፃናት ናቸው። በዚህ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ባለው ብርዳማው የአየር ጠበይ ብዙ ሕፃናት የሚገኙበት የአገሪቱ ዜጋ ተፈናቅለው ሕፃናት አለ ቤተሰብ አለ ምግብና የሚጠጣ ውሃ ሕይወታቸውን ለማዳን ሲጨናነቁና ጸአተኞች ሲሆኑ እያየን ነው። ብዙዎች ተገድሏል ቆስሏል ብዙዎች አካለቸውን ሰንክሏል። በእውነቱ ይኽ የሶሪያው ጦርነት በብዛት ለሞትና ለስቃይ የዳረገው ሕፃናትን ነው፡ የንጹሓን እልቂት ነው፡ በክልሉ ካለው ሁኔታ አንጻር በሶሪያ በዓለ ልደት ምን እንደሚመስል ለመገመቱ አያዳግትም።

በዓለ ልደት ቤተሰቦችን ቅድስት ቤተሰብን የቤተ ልሔም በድኽነት የተወለደው የማርያምና የዮሴፍ የስደት ጉዞ የተፈናቃዮች መጠለያ የሌላቸው በሮች የተዘጉባቸው የጎዳና ተዳዳሪዎች በሥራ አጥነት የሚሰቃየው አባት እናቱን ያጣውን ሁሉ እንድናስብ ግድ ይለናል። በዓለ ልደት ይኸንን ሁሉ እንድናስብና እንድናስተነትን ግድ ይለናል።

ኢየሱስ በተወለደበት ወቅት የሆነው ያጋጠመው ቅድስት ቤተሰብ የወረደባት መዓትና መከራ ማረፊያ ማጣት አሁንም በብዙዎች ሕይወት ሲደገም ይታያል። የወቅታዊው ዓለም የድህነት ምልክቶች ናቸው። በኅብረተሰ ዘንድ የበታች በሚባሉት በእረኞች ግንዛቤ ያገኘ ልደት። በግርግም ውስጥ ተወለደ። በእውነቱ የእረኞች መተባበር ለእኛ ጸጋ ሆኖልናል። ለጠማው በድኽነት ለተጠቃው ለሚሰቃየው ሁሉ መተባበር ለመዳናችን ምክንያት ይሆንልናል። የአንዱ መተባበርና በፍቅር ሥራ መትጋት ለዙዎች የመዳን ምክንያት ይሆናል። በሶሪያ ውስጥ በአሁኑ ወቅት 13 ሚሊዮን የሚገመቱ ዜጎች እርዳታ ያሻቸዋል። በዚህ አጋጣሚም ለከፋ አደጋ ተጋልጦ ለሚገኘው ለሶሪያ ሕዝብ ድጋፍ እርዳታ በማቅረብ ግብረ ሠናይ የተሰማሩት የዓለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶችና የበጐ ፈቃድ አባላት በእውነቱ ልናመሰግናቸው ይገባል። እነዚህ የግብረ ስናይ አካላት ልክ እንደ እረኞች ጌታን ለመቀበል ዝግጁነት ያሳዩ ያንን መልካም ፈቃድ በማወቅም ባለ ማወቅም የሚወክሉ ናቸው ብሏል።

በሶሪያ ያለው ማኅበረ ክርስቲያን በክልሉ ያለው ውጥረትና ሁከት እየተፈታተነው አሁንም በተስፋ ይኸው በጦርነትና በግጭት ውስጥ በዓለ ልደት ለስድተኛ ጊዜው እያከበረ ነው፡ ጦርነቱ ከተቀጣጠለበ ጊዜ ጀምር ያከበራቸው በዓለ ልደት ሁሉ ያንን የሰውን ልጅ ለማዳን ሲል የመጣውን ጌታ በተስፋ የመቀበሉ ግብረ እምነት አብነት ሆኖ  አቢይ የእምነት ምስክርነ ነው። የመብራት ኃይል መቋረጥ በሚትይበት በአገሪቱ ክልል ሳይቀር ክርስቲያኖች የበዓለ ልደት መግለጫ ጥድና የጌታን ልደት የሚያበስረው ትርኢት መግለጫ ሁሉ በማቆም በዓሉን በአቢይ እምነት አክብሮታ።

በአለፖ ያሉት ባሲሊካዎች አቢያተ ክርስቲያን ካቴድራሎ በጦርነቱ ምክንያት ወድሟል ገሚሳዊ ወይንም ምሉአዊ ውድመት ያጋጠማቸው በመሆኑ ምክንያት በዓለ ልደት ሊከርባቸው አልተቻለም። ሆኖም ከሁሉም በላይ ያን የሚመጣው ጌን በልብ መቀበል ነው፡ በልባችን የተቀበልነው ጌታ ለእርስ በእርስ መደጋፍና መቀራረብ ይገፋፋናል። በመሆኑም በልባችን የጌታን ልደት በማክበር በዓለ ልደቱን ለማክበር በሚቻልበት ሥፍራ ሁሉ እንደ ማኅበረ ክርስቲያን ሱታፌ ለመኖር ችለናል በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.