2016-12-26 12:36:00

ቅዱስነታቸው "የገናን በዓል በምናከብርበት ወቅት ምዕመናን በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ሕጻናትን ማሰብ ይገባቸዋል" አሉ።


እንደ አውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በታኅሣሥ 24/2016 ምሽት ላይ በተከበረው የክርስቶስ ልደት ወይም የገና በዓል መስዋዕተ ቅዳሴ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ መሪነት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ታካሂዶ የነበረ ሲሆን ቅዱሰታቸው በእለቱ ባሰሙት የወንጌል ቃል ሁሉም ክርስቲያኖች በቤተልሄም በከብቶች በረት ውስጥ በተወለደው ክርስቶስ መንፈስ በመሞላት በዛሬው ጊዜ በስቃይ ላይ ለሚገኙ ልጆችን ሁሉ የርኅራኄ ስሜት ይሰማቸው ዘንድ ጥሪ አድርገዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመንካት ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያስተላለፉት ስብከት ዋና ጭብጥ አሳብ የነበረው እና አጽኖት ስጥተው የገለጹት “በአሁኑ ጊዜ የሚወለዱ ሕጻናት በተለይም ደግሞ በጦርነት ውስጥ በሚገኙ ሀገራት የሚወለዱ ሕጻናት የእናት እና የአባታችውን ፍቅር አግኝተው የልጅነት ነፃነታቸውን አጣጥመው ሳይሆን እያደጉ የሚገኙት በተቃራኒው የቦንብ ናዳን እና ውርጅብኝን በመሸሽ በመሬት ውስጥ በተቆፈረ ምሽግ ውስጥ ራሳቸውን ደብቀው መሆኑን ገልጸው በጠጫማሪም በተለያዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ችግሮች ምክንያት ከተለያዩ የዓለም ስፍራዎች የሚሰደዱ ስደተኞች ልጆችም ቢሆኑ በተመሳሳይ መልኩ ደረጃቸውን ባልጠበቁ እና አደገኛ በሚባሉ በጥሩ ደረጃ ላይ በማይገኙ መርከቦች እና ጀልባዎች ሥር ታጉረው በስቃይ ላይ እንደ ሚገኙም ገልጸው ይህ እውነታ በጣም አሳዛኝ እንደ ሆነ ገልጸዋል።

“እሲቲ! በነፃነት እንዳይወለዱ እየተደረጉ ያሉ ሕጻናት ሐዘን ይሰማችው! (ውርጃ)፣ እስቲ! ማንም ሰው የጥማታቸውን እና የርሃባቸውን ችግር መልስ ባለመስጠቱ እያለቀሱ የሚገኙት ሕጻናት ለቅሶ ይሰማችሁ!፣ እስቲ! በእጆቻቸው የመጫወቻ ቁሳቁሶችን ሳይሆን የጦር መሣሪያን ያነገቡ ሕጻናት ስቃይ ይሰማችሁ” ብለዋል ቅዱስነታቸው።

ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ቲቶ በጻፈው መልዕክቱ በምዕራፍ 2,11 “ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦልና” ይላል። የቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ቃል የዛሬውን ቅዱስ ምሽት ሚስጢር ያስታውሰናል፣ የእግዚኣብሔር ፀጋ ተገልጦልናል፣ የእርሱም የፀጋ ስጦታ በነፃ የሚሰጥ ስጦታ ነው፣ እግዚኣብሔር አንደኛ ልጁን ለእኛ በመስጠቱ ለእኛ ያለውን ፍቅር በግልጽ አሳይቶናል።

ይህ ምሽት የክብር ምሽት ነው፣ ይህም ክብር በመልዐክት አማካይነት በኢየሩሳለም፣ በእኛ አማክይነት ደግሞ በዓለም ውስጥ የታወጀ ክብር ነው።

ይህ ምሽት የደስታ ምሽት ነው፣ ምክንያቱ ከእዚህ ቀን ጀምሮ እና በሚቀጥሉት ጊዜያ ሁሉ የዘላለም አምላክ የሆነው እግዚኣብሔር ሁልጊዜም ቢሆን ከእኛ ጋር በመሆኑ የተነሳ ነው። እርሱ ከእኛ ስለማይርቅ ጭምርም ነው ደስ ሊለን የሚገባን። እርሱን በስማይ እና በተለያዩ ርቆ በሚገኙ ቦታዎች ሳይሆን ከአሁን ቡኋላ ልንፈልገው የሚገባው እርሱ በቅርበት ስለሚገኝ ፍለጋችንን አቃሎልናል። እርሱ ሰው ሆኖ በመካከላችን በመወለዱ የተነሳ ራሱን ከሰውነት ባሕሪው ሊያርቅ በፍጹም አይፈልግም።

ይህ ምሽት የብርሃን ምሽት ነው። ይህም ብርሃን  በትንቢተ  ኢሳያስ በምዕራፍ 9.1 እንደ ተጻፈው በጨለማ ውስጥ ለሚጓዙት ሁሉ ብርሃን የሚሆናቸው፣ በቤተሊሔም በጨላም ውስጥ ለነበሩ እረኞች ያበራ ታላቅ ብርሃን ያስገኘ ምሽት ነው።

እረኞችም ቀላል በሆነ መልኩ “ለእኛ ሕፃን ተወልዶልናል” በማለት ብርሃኑ በገለጸላቸው መሠረት የእግዚኣብሔርን ክብር አዩ። ይህ ሁሉ ደስታ፣ ይህ ሁሉ ክብር የተገለጸላቸው መልዐክት ባሳዩዋቸው አንድ ምልክት አማክይነት በመመራት “በጨረቅ የተጠቀለለ አንድ ሕፃን በበረት ውስጥ ታገኛላችሁ” ብለው መልዐክት በነገሩዋቸው መሠረት ነው ይህንን ክብር እና ብርሃን ሊያገኙ የቻሉት።

ይህም ምልክት ዛሬም ቢሆን ኢየሱስን ለማግኘት የሚረዳን ምልክት ነው። የክርስቶስን ልደት በሚገባ ማክበር ከፈለግን እነዚህን ምልክቶች መርምረን ማወቅ ይጠበቅብናል። በጣም ዝቅተኛ በሆነ ስፍራ መወለዱ፣ በትህትና በበረት ውስጥ መተኛቱ፣ በጣም ጥሩ በማይባል ጨርቅ ተጠቅሎ መገኘቱ፣ ነገር ግን በእነዚ ነገሮች ሁሉ ውስጥ እግዚኣብሔር ነበር።

በእዚህ ረገድ ቅዱስ ወንጌላችን የሚለን ነገር እርስ በእርሱ የሚጋጭ ይመስላል። ምክንያቱም ይመጣል የተባለው፣ ንጉሥ፣ አስተዳዳሪ፣ በጊዜው ከነበሩት ሁሉ ኋይለኛ የሆነ መሲሕ ይመጣል ነው ወንጌላችን የሚለን። ነገር ግን በተቃራኒው እግዚኣብሔር በእነዚህ ነገሮች ተመስሎ አላመጣም ነበረ። ራሱን በታላላቅ ቤተ መንግሥት ውስጥ በመወለድ አልገለጸም፣ ነገር ግን በትህትናና በድኽነት፣ እዩኝ እዩኝ በሚል ስሜት ሳይሆን በጣም ዝቅ ባለ ሕይወት፣ በጉልበት እና በኋይለኛነት ሳይሆን ራሱን ዝቅ በማድረግ መምጣቱ ሁሉንም ሰዎች አስገርሞ ነበር።

እርሱን መገናኘት ከፈለግን እንደ እነዚህ ዓይነት ስፍራዎች በመሄድ፣ በመንበርከክ፣ ራሳችንን ዝቅ በማድረግ፣ ትህትናን መላበስ ያስፈልገናል። የተወለደው ሕጻን ታላላቅ የሚባሉ የቅዤት ሕይወትን ትተን ተጨባጭ የሆኑ ነገሮች ላይ ማተኮር እንደ ሚገባን ጥሪ ያቀርብልናል። በእዚህም ረገድ የእርካታ እጦት፣ ሐዘኔታን ማስወገድ የምንችለው ራሳችንን ዝቅ ስናደርግ ብቻ ነው። እነዚህንም ነገሮች በሕይወታችን በመተግበር ደስተኞች እንሆን ዘንድ እርሱ ይረዳናል፣ በትሕትና የእግዚኣብሔር ልጆች መሆን እንችላለን፣ ሰላም፣ ደስታን እና የሕይወት ትርጉምን እንረዳለን።

በማኅበረሰቡ ተገለው የነበሩ እረኞች ነበሩ ይህንን የመጀመሪያ ብርሃን እንዲያዩት የተደረገው። በጊዜያቸው የተገለሉ እና የተናቁ ነበሩ። ነገር ግን በእግዚኣብሔር ፊት ማንም ቢሆን የተገለለ አይደለም፣ እረኞቹ የመጀመሪያ የክርስቶስ ልደት ምስክር መሆናቸው የሚያሳየው ይህንን እውነታ ነው። በራሳቸው የሚታማመኑ፣ ሁሉም ነገር አለኝ ብለው የሚኮሩ፣ በቤታቸው ሁሉም ነገር የነበራቸው ሰዎች ሳይሆኑ የኢየሱስን መወለድ በቅድሚያ ያዩት፣ በተቃራኒው ምንም ነገር የሌላቸው እረኞች ነበሩ የክርስቶስን ወልደት በቅድሚያ የመሰከሩት በዐይናቸው ያዩት። ይህንንም በሉቃስ ወንጌል ውስጥ እንደ ተገለጸው በፍጥነት ነበር መልዐኩ ባዘዛቸው መሰረት የተገበሩት። እኛም ኢየሱስ እንዲገለጽልን እንፍቀድለት። በመተማመን ወደ እርሱ እንጓዝ። ከእርሱ ተገልያለው፣ ጥሩ ሰው አይደለሁኝም የሚለውን አመለካከት በማስወገድ ወደ እርሱ እንቅረብ። አዳኝ የሆነውን ኋይሉን በታላቅ ስሜት ሄደን እንንካ፣ ወደ እግዚኣብሔርም ራሳችንን እናቅርብ፣ ለአፍታ ያህል በገና ዛፍ ሥር ቆመን በመመልከት በምናባችን የኢየሱስን መወለድ እየሰላሰልን ብርሃኑን፣ ሰላሙን፣ ድኽነቱን እና ተጥሎ እንደ ነበረ እናስብ። ከእረኞቹ  ጋር በመሆን ወደ ኢየሱስ ውልደት ተጨባጭ በሆነ መልኩ ራሳችንን እናስገባ፣ ማን እንደ ሆንን ለኢየሱስ እንገረው፣ ከእርሱ መራቃችንን እና ቁስላችንን ሁሉ ለእርሱ እናሳየው እንገረው።

ይህንንም ስናደርግ ብቻ ነው ትክክለኛውን የገና በዓል ጣዕምን ልናውቅ እና ልናጣጥም የምንችለው፣ በእግዚኣብሔር መወደድ ምንኛ አስደሳች ነገር መሆኑንም መገንዘብ የምንችለው በእዚሁ መልክ ብቻ ነው። ከማሪያም እና ከዮሴፍ ጋር በመሆን በጸጥታ በገናው ዛፍ ስር በመቆም ኢየሱስ የሕይወት እንጀራ መሆኑን እናስብ። የእርሱን ትሁት እና ዘላለማዊ ፍቅርን በማሰብ አማስግንኋለሁ፣ ይህንንም ሁሉ ትሕትና ያደረከው ለእኔ ስትል ነው እንበለው ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.