2016-12-24 12:43:00

ቅዱስነታቸው የዓለም የሰላም ቀንን አስመልክተው ያስተላላአፉት መልእክት ክፍል 5


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በታኅሣሥ 3/2009 ዓ.ም. የዓለም የሰላም ቀንን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት ትኩረቱን ዓለማችን እያጣች ያለውን “ነውጥ አልባ” የሆነ የፖለቲካ ባሕል መልሳ ትጎናጸፍ  ዘንድ ሁሉም ሰዎች በተለይም የዓለም የፖሌቲካ ኋይሎች የበኩላቸውን አስተዋጾ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ ማድረጋቸውና  ለግጭቶች ወታደራዊ ምላሽ መስጠት ግጭቶችን የባሰ ከማፋፋም የዘለለ ፋይዳ እንደ ሌለውም መገለጻቸውን በታኅሣሥ 5/2009 ዓ.ም. ባስተላለፍነው የዜና ስርጭት መዘገባችን ይታወቃል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።


ይህንን የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘት በተከታታይ ለማቅረብ ቃል በገባነው መሰረት እነሆ ዛሬ አምስተኛ  ክፍል እናቀርብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል።

ቁጥር 4

ነውጥ አልባ እንቅስቃሴ ነውጥ ከተቀላቀለበት እንቅሳቃሴ የተሻለ ብቃት አለው

አንድ አንዴ ነውጥ አልባ እንቅስቃሴ እንደ ሽንፈት፣ የተሳትፎ ማነስ ወይም ደግሞ እንደ ተቃውሞ ማነስ ተደርጎ ይቆጠራል ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ ትክክል አይደለም። ቅድስት እማሆይ ትሬዛ እንደ የአውሮፓዊያኑ የቀን አቆጣጠር በ1979 ዓ.ም. የዓለም የሰላም ሽልማት በተሸለሙ ወቅት ስለ ነውጥ አልባ እንቅስቃሴ ጠቃሚነት ባስተላለፉት መልዕክት “እኛ በቤተሰባችን ውስጥ አውዳሚ የሆኑ ቦንብ እና ጥይት አያስፈልግንም። ሰላምን ለማምጣት አብሮ መሆን እና እርስ በእርስ መዋደድ በቂ ነገሮች ናቸው። በእነዚህም ነገሮች እገዛ በዓለም ውስጥ የሚታዩትን ክፉ ነገሮች ሁሉ በብቃት ማሸነፍ እንችላለን” ብለው ነበር። የጦር ኋይል ሁልጊዜም ቢሆን አታላይ ነው። “የጦር መሣሪያ አዘዋዋሪዎች በተቀላጠፈ ሁኔታ ሥራቸውን በሚሰሩበት ወቅት በጣም ጥቂት የሚባሉ ምስኪን የሰላም ጠበቆች የአንድ ሰውን ነብስ ለመታደግ ይንቀሳቀሳሉ፣ ለእንደነዚህ አይነቱ ምስኪን የሰላም ጠበቆች ቅድስት እማሆይ ትሬዛ “ይህንን የሚወክሉ የእኛ ዘመን አይነተኛ የሰላም አምድ ናቸው”። ባለፈው መስከረም ወር ለእማሆይ ትሬዛን የቅድስና ምዕረግ በመስጠቴ ከፍተኛ የሆነ ደስታ ይሰማኛል። “ሰዎችን በመቀበል እና የተወለደም ይሁን በማዕጸን ውስጥ የሚገኙትን እንዲሁም ተጥለው የነበሩ ሰዎች ሕይወት እንዳይጠፋ በመከላከል ለሁሉም ሰዎች ተደራሽ ለመሆን ያሳዩት የነበረውን ጥረት፣ በመንገድ ላይ ተጥለው ሞታቸውን ይጠባበቁ የነበሩ ሰዎች ፊት በመንበርከክ እግዚኣብሔር የሰጣቸውን ክብር መልሰው እንዲጎናጸፉ በማድረጋቸው የተነሳ ድምጻቸው ኋያል ሊባል በሚችሉት ሀገራት ውስጥ በማስተጋባቱ የተነሳ እነርሱ ማለትም ኋያላን የሚባሉ ሀገራት የደቀኑትን አደጋ እንዲረዱ አድርገዋል፣ ይህም እነርሱ የሰው ልጅ በድኽነት እንዲማቅቅ በቀዳሚነት አስተዋጾ ስላላቸው ቅድስት እማሆይ ትሬዛ ኋያላኑ ሀገራት ይህንን እንዲረዱ አድርገው አልፈዋል።

ለእዚህ ኋያላን ሀገራት ለደቀኑት አደጋ ቅድስት እማሆይ ትሬዛ በተልዕኮዋቸው ከሚልዮን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች በስቃያቸው ወቅት ደርሰውላቸዋል፣ ቁርጠኛ የሆነ ፍቅር አሳይተዋል፣ በሰውነታቸው ላይ የሚገኘውን ቁስላቸውንም ሳይጸየፉ አክመዋል፣ በስቃይ ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ሕይወት በመታደግ ለሁሉም ሰዎች አቅማቸው በፈቀደ መልኩ ተደራሽ በመሆን መልስ ሰጥተዋል።

በቁርጠኝነት ላይ የተመሰረተ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ የተተገበረው ነውጥ አልባ እንቅስቃሴ አስገራሚ የሆነ ለውጥ ማምጣቱን ከእዚህ መረዳት እንችላለን። በእዚህም ረገድ ህንድን ከቅኝ ግዛት ለማላቀቅ ማህተመ ጋንዲ የፈጸመውን ተግባር፣ ማርቲን ሉተር ኪንግ መቼም ቢሆን ሊቀረፍ የማይችለውን የቆዳ ቀለምን ያማከለ የዘረኝነት አባዜ እንዲወገድ ያደርገው  ነውጥ አልባ እንቅስቃሴ ያስገኘው ታላቅ እምርታ መቼም ቢሆን ሊዘነጋ የማይችል ነው።

ሴቶች ለየት ባለ ሁኔታ ነውጥ አልባ እንቅስቃሴን በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ድርሻን አበርክተዋል።  በላይቤሪያ የነውጥ አልባ የሰላም እንቅስቃሴ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ የሰላም ውይይት እንዲፈጠር በማስቻል በላይቤሪያ ሰዎችን በከፍተኛ ሁኔታ ሊያጫርስ ይችል የነበረውን የእርስ በእርስ ጦርነት ተወግዶ ሰላም እንዲሰፍን ጥረት ካደረጉ በሺዎች ከሚቆጠሩ ሴቶች መኸከል ግቦዌኔ በአብነት መጥቀስ ይቻላል።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የዓለም የሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉትን መልዕክት አምስተኛ ክፍል ሙሉ ይዘቱን ነበር ስትከታተሉት የቆያችሁት ቀጣዩን እና ስድስተኛውን ክፍል በሚቀጥለው ሰኞ በታኅሣሥ 17/2009 ዓ.ም. እናቀብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.