2016-12-22 15:55:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የሰኞ የታኅሣሥ 12/2009 ዓ.ም. ዜና።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በታኅሣሥ 12/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት ባስተላለፉት ልማዳዊ የጠቅላላ አስተምህሮ ወቅት እንደ ገለጹት ምዕመናን  የአዳኛችን መወለድ ለሚያበስረው መልካም ዜና ልባቸውን መክፈት ይኖርባቸዋል ማለታቸው ተገለጸ።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ቀጥሎ የሚገኘውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያስተላለፉት አስተምህሮ ትኩረቱን የክርስቲያን ተስፋ በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያደረገ እንደ ነበረም የታወቀ ሲሆን እንደ አውሮፓዊያኑ የስርዐተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር አራተኛ የስብከተ ገና ሳምንት የመጨረሻ ቀናት ላይ መሆነችውን ባስታወሰው አስተምህሮዋቸው ከክርስቶስ መወለድ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን መልዕክት ለመቀበል መዘጋጀት ይገባናል ማለታቸውም ታውቁዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.