2016-12-21 15:25:00

ቅዱስነታቸው ምዕመናን የአዳኛችን መወለድ ለሚያበስረው መልካም ዜና ልባቸውን መክፈት ይኖርባቸዋል ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በታኅሣሥ 12/2009 ዓ.ም. በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች በተገኙበት ባስተላለፉት ልማዳዊ የጠቅላላ አስተምህሮ ወቅት እንደ ገለጹት ምዕመናን  የአዳኛችን መወለድ ለሚያበስረው መልካም ዜና ልባቸውን መክፈት ይኖርባቸዋል ማለታቸው ተገለጸ።

ሙሉ ዜናውን ከእዚህ በታች ያለመውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያስተላለፉት አስተምህሮ ትኩረቱን የክርስቲያን ተስፋ በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያደረገ እንደ ነበረም የታወቀ ሲሆን እንደ አውሮፓዊያኑ የስርዐተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር አራተኛ የስብከተ ገና ሳምንት የመጨረሻ ቀናት ላይ መሆነችውን ባስታወሰው አስተምህሮዋቸው ከክርስቶስ መወለድ ጋር ተያይዞ የሚመጣውን መልዕክት ለመቀበል መዘጋጀት ይገባናል ማለታቸውም ታውቁዋል።

 

የቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ አስተምህሮ ጠቅላላ ይዘት

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ

በእዚህ የስብከተ ገና የመጨረሻ ቀናት የክርስቲያን ተስፋ በሚል አርዕስት የማስተላልፈው ጠቅላላ አስተምህሮ የገና በዓል ሚስጢር ላይ የሚያጠነጥን እና ተስፋ ወደ ዓለማችን እንደ ሚመጣ የሚገልጽ ነው።  ቃል የገባውን በመፈጸም ልጁን በመላክ ከድንግል ማሪያም እንዲወለድ በማድረግ እግዚኣብሔር መንግሥቱን በምድር ላይ በመመስረቱ የተነሳ ተስፋችን ወደ ዘላለም ሕይወት እንዲለወጥ አድርጉዋል።

ይህም ተስፋ እውነት እና ታማኝ ነው፣ የሚያድን እና የሚበዢ ጭምር ነው። ክርስቶስ ሥጋን ለብሶ በመምጣቱ ወደ እግዚኣብሔር ሽቅብ የምንወጣበትን መንገድ ከፍቶልናል። በአሁኑ ወቅት በቤታችን እና በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ የገናን ዛፍ በምናዘጋጅበት ወቅት በእዛ ዛፍ ውስጥ ለሚገኘው የተስፋ መልዕክት ትኩረት ልንሰጥ ይገባል። በትንሿ የቤቴሊሄም ከተማ ውስጥ የእግዜብሔር ፍቅር ለትልቁም ይሁን ለትንሹም በአጠቃላይ ለእያንዳንዳችን ተገልጹዋል። የእግዚኣብሔርን ቃል አምና በተቀበለችሁ በማሪያም በኩል የተስፋ እናታችንን እናያለን። ዮሴፍም ቢሆን ለሕጻኑ ኢየሱስ  (ትርጉዋሜውም እግዚኣብሔር ያድናል) የሚል ስም በማውጣቱ የተስፋ ምልክት ሆኖዋል።በመላእክት የታወጀው የሰላም መልዕክት በእረኞች ተደምጡዋል። እኛም የአዳኛችንን መወለድ ለሚያበስረው መልካም ዜና ልባችንን መክፈት እና የፍትህ፣ የሰላም የቅድስና ምንግሥትን ይዞልን ይመጣል የሚለውን ተፋችችን እናድስ ካሉ ቡኋላ ከምዕመናን ጋር የመለከ እግዚኣብሔርን ጸሎትን ደግመው እና ቡራኬን ከሰጡ ቡኋላ የእለቱ ዝግጅት ተጠናቁዋል። 

 








All the contents on this site are copyrighted ©.