2016-12-20 09:53:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የሰኞ የታኅሣሥ 10/2009 ዓ.ም. ዜና።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቼስኮ በታኅሣሥ 9/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ አስተምህሮ ለመከታተል ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ባተላለፉት ልማዳዊ በሆነ አስተምህሮዋቸው እንደ ገለጹት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማሪያም በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት ኢየሱስን እንደ ጸነሰችው ገልጸው “የእግዚኣብሔር ልጅ በማህጸኗ ለማደር በመጣበት ጊዜ በደስታ እንዳስተናገደችሁ” ጨምረው ገልጸዋል።

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የሰኞ የታኅሣሥ 10/2009 ዓ.ም. ዜና ሙሉውን ስርጭት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ለማዳመጥ ትችላላችሁ።

በእዚህ ለየት ባለ ሁኔታ “እግዚኣብሔር በአንዲት ሴት ማህጸን በማደር ከእርሷ ሥጋን ለብሶ ለሰው ልጆች እጅግ በጣም ቅርብ ሆነ” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እግዚኣብሔር እኛን በፀጋው  በመቅረብ፣ አንድኛ ልጁን በስጦታነት ለእኛ በመስጠት፣ በሕይወታችን ውስጥ ለመግባት መጥቱዋል” ብለዋል።

“ታዲያ እኛ ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? ልንቀበለውና እንዲቀርበን ማድረግ ይጠበቅብናል ወይስ እንቢ በማለት ከውስጣችን አውጥተን መጣል ይጠበቅብናል? በማለት ጥያቀን በማንሳት ስበክታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ማሪያም ራሷን በነጻነት ለእግዚኣብሔር በስጦታነት እንዳቀረበች፣ የሰው ልጆችን እጣ ፋንታን እንደቀየረች ሁሉ እኛም ኢየሱስን ተቀብለን እና እለት በእለት ልንከተለው ቃል በመግባት ከእርሱ የመዳን እቅድ ጋር በመተባበር ራሳችንን እና ዓለምን በማዳን ሂደት ውስጥ የበኩላችንን አስተዋጾ ማድረግ እንችላለን ብለዋል።

ስለዚህም እኛም እግዚኣብሔርን ለማግኘት በምናደርገው ፈልጋ ወቅት ሁሉ የማሪያምን አብነት መከተል ይገባናል ያሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር እኛን እንዲቀርበን ማድረግ የምንችለው እና ፍቅርን መገንባት የሚቻለው በእዚህ ዓይነቱ መንገድ መጓዝ ስንችል ብቻ ነው ብለዋል።

ልክ በዛሬው የወንጌል ቃል ላይ እንደ ተጠቀሰው ከማሪያም ጋር ጎን ለጎን ሊታይ የሚገባው እጮኛዋ የነበረው ዮሴፍ እንደ ሆነ በመጥቀስ አስተምህሮዋቸው የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ማሪያም በድንገት ጸንሳ በመገኘቷ ግራ ታጋብቶ ነበር ካሉ ቡኋላ “ጥርጣሬ እና ጭንቀት ውስጥ ገብቶ በነበረበት ወቅት” እግዚኣብሔር መልእክተኛውን ውደ እርሱ በመላክ “እርሷ የጸነሰችው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት መሆኑን” አስረድቶአት ነበር ብለዋል።

“በእዚህ ለየት ባለ ከፍተኛ ጥርጣሬ እና ጭንቀት እንዲሁም በዙ ጥያቄዎች በልቡ ውስጥ በሚመላለስበት ወቅት፣ ሙሉ በሙሉ እምነቱን በእግዚኣብሔር ላይ ጥሎ ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የእግዚኣብሔርን ግልጸት አምኖ ከተቀበላ ቡኋላ በስውር ሊፈታት አቅዶ የነበረውን ሐሳብ በመቀየር ማሪያም እጮኛው እንድትሆን ወደ ቤቱ እንደ ወሰዳትም” ጨምረው ገልጸዋል።

ዮሴፍ ማሪያምን በመቀበሉ የተነሳ በእግዚኣብሔር ኋይል የተጸነሰውን እና በማህጸኗ ውስጥ የሚገኘውን ልጇንም መቀበሉን ያሳያል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ዮሴፍ መልካም እና ትሁት ሰው መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አስተምህሮዋቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት ዮሴፍ የፈጸመው ተግባር እግዚኣብሔር ሁል ጊዜ ቅርባችን እንደ ሆነ መተማመን እንደ ሚኖርብን ያስተምረናል ያሉት ቅዱስነታቸው እግዚኣብሔር በሚቀርበን ጊዜያት ሁሉ እርሱን ማመን ይጠበቅብናል፣ ዮሴፍ እግዚኣብሔር ይመራን ዘንድ ለእርሱ እራሳችንን በማስገዛት በመልካም ፈቃድ እና በመታዘዝ መኖር እንደ ሚገባን ያስተምሮናል ብለዋል።

በእምነታቸው የተነሳ ማሪያም እና ዮሴፍ “በቅድሚያ እየሱስን ተቀበሉት ለእኛም የገናን በዓል ሚስጢር እንድናውቅ አደረጉን” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእዚህም የተነሳ በመጀመሪያ ደረጃ “ራሳችንን የእግዚኣብሔርን ልጅ ለመቀበል መልካም የሚባል ባሕሪን በመፈጸም እንድንገኝ” በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ “ሁል ጊዜም ቢሆን የእግዚኣብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም እንድንተጋ እና በእርሱ በመታመን እንድንከተለው” አስተምረውናል ብለዋል።

በእነዚህ ሁሉት ሐሳቦች መኸከል “እግዚኣብሔርን መቅረብ” የሚል ጭብጥ እናገኛለን ያሉት ቅዱስነታቸው ይህንንም ተመሳሳይ መልዕክት በእዚህ በሚመጣው የገና በዓል በድጋሚ በመግለጽ “አማኑኤል” እግዚኣብሔር ከእኛ ጋር ነው” የሚለውን መተግበር ያስፈልጋል ብለዋል ቅዱስነታቸው።

ቅዱስነታቸው በአስተምህሮዋቸው ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት “ለተወሰነ ጊዜያት በጸጥታ በመቆየት ማሪያም እናታችን እና ቅዱስ ዮሴፍ ወደ ቤተሊሄም እየሄዱ መሆናቸውን በምናባችን ለመመልከት እንሞክር” ካሉ ቡኋላ በድካም እና በደስታ እየተጓዙ ይገኛሉ፣ በግርግር  እና በጉጉት ውስጥ ሆነው እጻኑ የሚወለድበትን ቦታ እየፈለጉ ይገኛሉ፣ በጣምም ተጨንቀዋል የሚሉትንና የመሳሰሉ  ስሜቶችን በምናባችን ልንስል እንችል ይሆናል ካሉ ቡኋላ ይህም የጉዞ ሂደታቸው ትክክለኛ የገናን በዓል ስሜት ይገልጽልናል፣ ይህም ኢየሱስ እንደ ሚቀርበን እና እግዛኢብሔር ከእኛ ጋር በመሆን በእዚህ በዓል ወደ እርሱ እንድንቀርብ፣ የፍቅር፣ የትሕትናና የርኅራኄ ፀጋውን ሊለግሰን ይመጣል ካሉ ቡኋላ ከምዕመናን ጋር የመልአከ እግዚኣብሔርን ጸሎት አብረው ደግመው እና ቡራኬን ስጥተው ለእለቱ የተዘጋጀውን አስተምህሮ አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.