2016-12-20 09:34:00

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራነቸስኮ የዓለም የሰላም ቀን በተከበረበት ወቅት አስተላልፈዉት የነበረው መልዕክት ክፍል 3።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በታኅሣሥ 3/2009 ዓ.ም. የዓለም የሰላም ቀንን አስመልክተው ያስተላለፉት መልዕክት ትኩረቱን ዓለማችን እያጣች ያለውን “ነውጥ አልባ” የሆነ የፖለቲካ ባሕል መልሳ ትጎናጸፍ  ዘንድ ሁሉም ሰዎች በተለይም የዓለም የፖሌቲካ ኋይሎች የበኩላቸውን አስተዋጾ ያደርጉ ዘንድ ጥሪ ማድረጋቸውና  ለግጭቶች ወታደራዊ ምላሽ መስጠት ግጭቶችን የባሰ ከማፋፋም የዘለለ ፋይዳ እንደ ሌለውም መገለጻቸውን በታኅሣሥ 5/2009 ዓ.ም. ባስተላለፍነው የዜና ስርጭት መዘገባችን ይታወቃል።

ይህንን የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘት በተከታታይ ለማቅረብ ቃል በገባነው መሰረት እነሆ ዛሬ ሦስተኛውን  ክፍል እናቀርብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።

የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የሰላም መልዕክት ሙሉ ይዘቱን እንደ ሚከተለው ተርጉመነዋል።

ቁጥር 2

ስነ-ምግባር የገደለው ዓለም

ባለፈው ምዕተ ዓመት ዓለማችን ሁለት ታላላቅ የሚባሉ ጦርነቶችን አካሄዳ የነበረች ሲሆን የኒውክለር ጦር መሳሪያ አደጋ እና በጣም ብዙ ሊባሉ የሚችሉ ገዳይ የሆኑ ግጭቶችም በአሁን ወቅት እያስተናገደች በመገኘቷ የተነሣ ሰላማችን አደጋ ላይ ይገኛል። ምንም እንኳን አሁን በዓለማችን የመገናኛ አውታሮች ተስፋፍተው የሚገኙ ቢሆንም እንኳን ዓለማችን ከባለፉት ምዕተ ዓመታት በበለጠ ወይም ባነሰ መልኩ በብጥብጦች እየታመሰች ትሁን ወይም አትሁን መለየት ያዳግታል።

በእዚህ ረገድ እነዚህ ነውጦች በዓይነታቸው የተለዩ እና ደረጃቸውም የተለያየ በተናጠል የሚደረጉ ነውጦች ከፍተኛ የሆነ ስቃይ በማድረስ ላይ ይገኛሉ። በተለያዩ አህጉራት እና ሀገራት የሽብር ጣቃቶች፣ የጠቀናጁ የወንጄል ተግባራት እና አንድ አንዴም ልጨበጡ የማይችሉ ነውጦች ለምሳሌም በስደተኞች ላይ የሚደረስው ስቃይ፣ በሰው ልጆች ሕገወጥ ዝውውር የሚደርሰው መከራ፣ በአከባቢ ስነ-ምዕዳር ላይ የሚደርሰው ውድመትን በማሳያነት መጥቀስ ይቻላል። እነዚህ ተግባራት ወዴት ነው እየመሩን የሚገኙት? ነውጥ ዘላቂ የሆነ መፍትሄዎችን ልያስገኝ ይችላል? ወይስ ደግሞ ወደ በቀል እና ገዳይ ወደ ሆኑ አደገኛ ግጭቶች ማኅበረሰቡን በመምራት የተወሰኑ የጦር አበጋዞችን ነው ተጠቃሚ የሚያደርገው?

ነውጥ ለእዚህ በስነ ምግባር እጦት ለሚሰቃየው ዓለማችን መድኋኒት ሊሆን አይችልም። ነውጥን በነውጥ ለመቀልበስ መሞከር አስገዳች ወደ ሆነ ስደት እና በቃላት ሊገለጽ ወደ ማይችል ስቃይ ይመራል። ምክንያቱም በጣም ብዙ ሊባሉ የሚችሉ የየሀገራቱ ሀብት ለጦር መሳሪያ ግዢ በማዋል በአንጻሩ ለእለት እለት ተግባራት የሚውለው ሐብት ከወጣቶች አረጋዊያን እና ቤተሰቦች ጎሮሮ ላይ ተነጥቆ በጦር አበጋዞች ወደ ሚመሩ ድርጅቶች እና የዓለማችን ኋያላን ወደ ሚባሉ ሀገርት የእነዚ በብጥብጥ የሚሰቃዩ ሀገራት ሐብት ወደ ሐብታሞቹ እና ጉልበታሞቹ ሀገራት ይሄዳል። ከእዚህም ሁሉ በላይ የሚያሳዝነው ይህ ተግባራቸው ወደ ሞት፣ አካላዊ እና መንፈሳዊ ጉዳቶችን ማስከተሉ ነው።

ክቡራን እና ክቡራት የዝግጅታችን ተከታታዮች ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ የዓለም የሰላም ቀንን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉትን መልዕክት ሙሉ ይዘቱን ሁለተኛ ክፍል አቅርበንላችኋል ቀጣዩን እና አራተኛውን ክፍል በሚቀጥለው ረብዕ እናቀብላችኋለን እንድትከታተሉን ከወዲሁ እንጋብዛለን።








All the contents on this site are copyrighted ©.