2016-12-20 10:59:00

ር.ሊ.ጳ ፍራነቸስኮ ወጣቶች አያቶቻቸውን ማዳመጥ ይኖርባቸዋል ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሣሥ 10/2009 ዓ.ም. ለወጣት ካቶሊኮች  ባስተላለፉት የማበረታቻ መልዕክታቸው እንደ ገለጹት ወጣቶች ከአያቶቻቸው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ማጠናከር እንደ ሚኖርበቻው ገለጹ።

ቅዱስነታቸው በጣሊያን ከሚገኙው “Azione Cattolica Italiana” ከተባለው ማሕበር ከተውጣጡ  ወጣት ካቶሊክ ምዕመናን ጋር በተገናኙበት ወቅት እንደ ገለጹት በእዚህ በገና ወቅት ከኢየሱስ መምጣት ጋር ተያይዞ የሚመጣው ደስታ የሚጨምረው እና ሊበዛ የሚችለው ከሌሎች ጋር ይህንን ደስታ መካፈል ስንችል ብቻ ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በተጨማሪም ወጣቶቹ በእዚህ በስብከተ ገና ወቅት የሚገኘውን የደስታ ስጦታን በመቀበል በቤተሰባቸው፣ በትምህርት ቤታቸው፣ በቁምስናቸው እና በአጠቃላይ በሁሉም ስፍራ ምስክርነትን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ጨመረው እንደ ገለጹት ወጣቶቹ ለየት ባለ ሁኔታ ይህንን የስብከተ ገናን ደስታ ከአያቶቻቸው በአጠቃላይም ከአዛውንቶች ጋር መካፈል እንደ ሚጠበቅባቸው ገልጸው እነዚህን በእድሜ የገፉ ሰዎች “የሕይወት ጥበብ” ስላላቸው እነርሱን ማዳመጥ ይገባል ብለዋል።

“እስቲ አንድ የምትፈጽሙት ተግባር ልስጣችሁ፣ ከአያቶቻችሁ ጋር ተነጋገሩ፣ ጥያቄዎችን ጠይቁዋቸው፣ የታሪክ ትውስታ አላቸው፣ የሕይወት ተመኩሮም አላቸው፣ ይህም እናንተን በሕይወታችው ጉዞ በምትራመዱበት ወቅት የሚረዳችሁ ትልቅ የሆነ ስጦታ ነው” ቅዱስነታቸው ብለው እንደ ነበረም ተገልጹዋል።

አያቶቻችሁም ቢሆን እናንተን ለማድመጥ፣ የእናንተን ተነሳሽነት እና የሰነቃችሁትን ተስፋ ለመረዳት ፈቃደኛ ሊሆኑ ይገባል ያሉት ቅዱስነታቸው “ሰላም እና አንድነት ይሰፍን ዘንድ በቁርጠኝነት እየሠሩ የሚገኙትን ቤተሰቦች አጋጣሚውን ተጠቅመው አመስግነው ይህንንም ተግባራቸውን ወጣቱን ትውልድ ተጠቃሚ በሚያደርግ መልኩ አጠናክረው መቀጠል እንደ ሚገባቸው አደራ ብለዋል።

Azione Cattolica Italiana’ የተሰኘው የወጣቶች ማሕበር በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፒዮስ አስረኛ እንደ አውሮፓዊያን የቀን አቆጣጠር በ1905 ዓ.ም. የተመሰረተ እና ፓሌቲካዊ ተግባራትን የማያከናውን በጳጳሳት ሥር የሚተዳደረ መንፈሳዊ ተቋም ነው።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.