2016-12-17 10:56:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የሰኞ የታኅሣሥ 8/2016 ዓ.ም. ዜና።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እውነት መናገር አለባቸው፣ በተመሳሳይ መልኩም ሰዎች አቅማቸው በፈቀደ መልኩ የሚለግሱትን ነገሮች በደስታ መቀበል አለባቸው፣ ይህም ቀዳሚ ተግባራቸው በማድረግ የተቀረውን እግዚኣብሔር ይፈጽመው ዘንድ ለእርሱ መተው ይኖርባቸዋል” ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት በታኅሣሥ 6/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ  የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት መሆኑም ጨምሮ ተገልጹዋል።

የእዚህን ዜና ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ትችላላችሁ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት በቅዱስ መጥምቁ ዩሐንስን ታሪክ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ይህም እንደ የአውሮፓዊያን የስርዓተ-ሉጥርጊያ አቆጣጠር በሦስተኛው የስብከተ ገና ሳምንት ውስጥ የሚነበቡ ምንባባት ጭብጣቸውን በአገልግሎት ላይ በማድረግ በተለይም ደግሞ በበረሃ የሚኖር ሰው፣ ስለ ንስኋ የሚሰብክ እና የተጸጸቱትን ማጥመቅ በሚሉት ሐሳቦች ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ሆነም ታውቁዋል።

ፈሪሳዊያንን እና የሕግ ሙሁራንን ጨምሮ ብዙ ሰዎች በመጥምቁ ዩሐንስ ለመጠመቅ ወደ በረሃ ሄደው እንደ ነበር በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ፈሪሳዊያን እና የሕግ ምሁራን ከነበረባቸው ችግሮች ለመላቀቅ በመጥምቁ ዩሐንስ ለመጠመቅ ሳይሆን ወደ በረሃ የሄዱት ነገር ግን በተቃራኒው ሊዳኙት መሄዳቸውን ጠቁመዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.