2016-12-17 10:45:00

ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ “የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እውነት መናገር አለባቸው" ማለታቸው ተገለጸ።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ “የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እውነት መናገር አለባቸው፣ በተመሳሳይ መልኩም ሰዎች አቅማቸው በፈቀደ መልኩ የሚለግሱትን ነገሮች በደስታ መቀበል አለባቸው፣ ይህም ቀዳሚ ተግባራቸው በማድረግ የተቀረውን እግዚኣብሔር ይፈጽመው ዘንድ ለእርሱ መተው ይኖርባቸዋል” ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት በታኅሣሥ 6/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ  የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት መሆኑም ጨምሮ ተገልጹዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት በቅዱስ መጥምቁ ዩሐንስን ታሪክ ላይ ያጠነጠነ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን ይህም እንደ የአውሮፓዊያን የስርዓተ-ሉጥርጊያ አቆጣጠር በሦስተኛው የስብከተ ገና ሳምንት ውስጥ የሚነበቡ ምንባባት ጭብጣቸውን በአገልግሎት ላይ በማድረግ በተለይም ደግሞ በበረሃ የሚኖር ሰው፣ ስለ ንስኋ የሚሰብክ እና የተጸጸቱትን ማጥመቅ በሚሉት ሐሳቦች ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ሆነም ታውቁዋል።

ፈሪሳዊያንን እና የሕግ ሙሁራንን ጨምሮ ብዙ ሰዎች በመጥምቁ ዩሐንስ ለመጠመቅ ወደ በረሃ ሄደው እንደ ነበር በመግለጽ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ፈሪሳዊያን እና የሕግ ምሁራን ከነበረባቸው ችግሮች ለመላቀቅ በመጥምቁ ዩሐንስ ለመጠመቅ ሳይሆን ወደ በረሃ የሄዱት ነገር ግን በተቃራኒው ሊዳኙት መሄዳቸውን ጠቁመዋል።

በእለቱ በተነበበው የቅዱስ ወንጌል ቃል ላይ እንደ ተጠቀሰው ኢየሱስ ሕዝቡን “ምን ልታዩ ወደ በረሓ ወጣችሁ? በንፋስ የሚወዛወዝ ሸንበቆ ለማየት ነውን? ደግሞስ ምን ልታዩ ወጣችሁ? ቀጭን የሐር ልብስ የለበሰ ሰው ለማየት ነውን? ቀጭን የሐር ልብስ የሚለብሱና በቅምጥል የሚኖሩማ በነገሥታት ቤት ይገኛሉ ብሎ ሕዝቡን እንደ ጠየቀ ያስታወሱት ቅዱስነታቸው ቀጭን የሐር ልብስ የለበሱ ሰዎች አንድ አንዴም በጳጳሳት ቤትም እንደ ሚገኙ ጠቆም አድርገው አልፈዋል።

ነገር ግን በእለቱ ወንጌሉ እንደ ተጠቀሰው ሕዝቡ ወደ በረሓ የወጣው ከነቢያት ሁሉ በላይ የሆነውን ለማየት እንደ ነበረ የጠቀሱት ቅዱስነታቸው ኢየሱስም ከሴቶች ሁሉ ከተወለዱት ሰዎች በላይ የሆነ እና የመጨረሻው ነብይ ከሚባለው ከመጥመቁ ዩሐንስ በላይ እንደ ሆነም ጨምረው ገልጸዋል።

ስለመጥመቁ ዩሐንስ ታላቅነት በማውሳት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ጌታ እንዲያከናውን የጠየቀውን ነገር በታማኝነት በማከናወኑ የተነሳ” ታላቅ ነቢይ የሚለውን መጠሪያ ለማግኘት መብቃቱንም ጨምረው ገልጸዋል።

መጥመቁ ዩሐንስ ለመጠመቅ ከመጡ ሰዎች መኋከል እነማን እንደ ነበሩ በሚገባ ተረድቶ ነበር፣ በተለይም ሕዝቡን በመበዝበዝ የሚታወቁ ቀራጮችም በመኽከላቸው እንደ ነበሩም ከማወቁ የተነሳ “በሕግ ከተፈቀደላችሁ በላይ አትጠይቁ” ይላቸው ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው መጥምቁ ዩሐንስ አገልግሎቱን የጀመረው እነዚህን የመሳሰሉትን ጥቃቅን የሚባሉ ነገሮችን በመጠየቅ እና በማጥመቅ የመጀመሪያ ደረጃ አገልግሎቱን ጀምሮ እንደ ነበረም ቅዱስነታቸው ጨምረው ገልጸዋል። 

ምንም እንኳን መጥምቁ ዩሐንስ ታላቅ፣ ጠንካራ፣ በጥሪው እርግጠኛ የሆነ ቢሆንም ቅሉ “ጭልምልም ያሉ ወቅቶች በሕይወቱ ይንጸባረቁ ነበር፣ ይህም ከጥርጣሬ የመነጨ ጨለማነት ነበር” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ይህም የጥርጣሬ ስሜት የጀመረው ዩሐንስ በእስር ቤት በነበረበት ወቅት ነበር ምንም እንኳን ኢየሱስ እርሱ የጠበቀው ዓይነት ነብይ ሆኖ ባያገኘውም አጥምቆት እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

ከእዚህ ጥርጣሬው የተነሳ መጥመቁ ዩሐንስ ማረጋገጫን በመሻት የእርሱ የነበሩትን ሁለት ደቀ መዛሙርት ማረጋገጫ ያመጡለት ዘንድ እና እርሱ ይመጣል የተባለው መስህ እንደ ሆነ ወይም እንዳልሆነ እዲጠይቁት  ወደ ኢየሱስ ልኮዋቸው እንደ ነበር በስብከታቸው የጠቀሱስት ቅዱስነታቸው ኢየሱስም የመጥመቁ ዩሐንስን  ትክክለኛ መልስ በመስጠት አስተካክሎት እንደ ነበረም ጨምረው ገልጸዋል።

በእርግጥም ኢየሱስ ለዩሐንስ ደቀ-መዛሙርት “ዓይነ ስውራን ያያሉ፣ መስማት የተሳናቸው ይሰማሉ፣ ሙታንም ይነሳሉ” የሚሉትን በዓይናቸው ያዩትን ማረጋገጫዎች ይመሰክሩ ዘንድ መልሶ እንደ ላካቸውም ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ እንደ ገለጹት “መጥመቁ ዩሐንስ ቀዳሚ የሆኑ ተግባራትን ለምሳሌም ሐዋሪያዊ ጥንካሬን ይሰጠን ዘንድ እና በእውነታ ላይ የተመሰረት፣ በሐዋሪያዊ ፍቅር የተሞላ፣ ህዝቦችን ከነማንነታቸው መቀበልን ያስተምረን ዘንድ ልንጠይቀው ያስፈልጋል፣ ቀሪውን ነገር እግዚኣብሔር ያከናውነዋል ካሉ ቡኋላ  በተጨማሪም እምነታችንን ጠንካራ መሰረት ላይ እንድንገነባ የሚራዳንን መልካም የሆነ የጥርጣሬ ጸጋ ይለግሰንም ዘንድ መጠይቅ አስፈላጊ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ታላቅ የሆነው ነገር ግን በመግሥተ ሰማይ ከሁሉም ያነሰው መጥመቁ ዩሐንስ በጌታ መንገድ ላይ በታማኝነት መመላለስ እንድንችል ይረዳን ዘንድ ልንማጸነው ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ለእለቱ ያዘጋጁትን ስብከት አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.