2016-12-16 16:44:00

ቅዱስ አባታችን፥ ተስፋ ለክርስትና ሕይወት ነዳጅ ነው


እ.ኤ.አ. ታህሳስ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አዳራሽ ሮማ የሚገኘው የሕፃነ ኢየሱስ ሕክምና ቤት ህሙማን ሕጻናት ወጣቶች የህክምና ቤቱ መሥተዳድር አባላት ሐኪሞች በጠቅላላ የሕክምና ባለ ሙያዎችን ተቀብለው መሪ ቃል መለገሳቸው የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ጃዳ አኵይሊኖ ገለጡ።

ቅዱስነታቸው በህክምና ቤቱ ከሚረዱት ሕፃናት ሕሙማን ውስጥ 150 ለመሳተፍ የቻሉትን በፊት በተቀመጡበት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን የሕክምና ቤቱ የመሥተዳድር ምክር ቤት ሊቀ መንበር ማሪየላ ኤኖክ እንዲሁም እ.ኤ.አ. ታህሳስ 17 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢጣሊያዊ ታዋቂው ድምጻዊ ክላውዲዮ ባሊዮነ በባንጕይ አስፈላጊ የሕክምና መሣሪያ ያሟል የሕፃናት ማከሚያ ቤት ለመገንባት ገቢ ለማሰባሰብ በሚካሄደው የጥዑም ውሁድ ሙዚቃ መርሃ ግብር ለመሳተፍ አገረ ቫቲካን የሚገኙት የረፓብሊካዊት ማእከላዊት አፍሪቃ አገር ርእሰ ከተማ ባንጕይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ዳይኡዶነ ንዛፓላይንጋ ተሸኝተው በዚህ በጳውሎስ ስድስተኛ የጉባኤ አደራሽ “ተስፋ ለክርስትና ሕይወት ነዳጅ ነው” የሚል ህሳብ ላይ ያጠነጠነረ አስተምህሮ የለገሱ ሲሆን፡ ልብን  ዘግቶ ሳይሆን ልብን ከፍቶ መኖር ደስታን ይሰጣል ያሉት ቅዱስነታቸው ታማሚ ሕፃናቱን ስቃይ ያለባቸው ቢሆንም ጽናት የሚታይባቸው ጠንካራ ደስታንና ደግነትን አንግበው ዕለታዊ ህላዌን በመጋፈጥ ከሚኖሩት ውስጥ በዚያ ማከሚያ ቤት የሚሠሩ የሕክምና ባለ ሙያዎች ውስጥ ላቀረቡላቸው ጥያቄ በተመስጦ በማዳመጥ አንድ በአንድ መንፈስንና አካላዊ ብርታትን የሚሰጥ አባታዊ ምዕዳን ለግሷል።

አዲት የሕክምና ባለ ሙያ በዚያ ማከሚያ ቤት ያለው የአሠራር ሂደት የህሙማን ሕፃንትና ወላጆች ሁኔታ ዙሪያ ስትገልጥ ቅዱስነታቸው ይኸንን ሃሳብ ተንተርሰውም በእውነቱ በሚሰቃዩት ሕፃናት ጉዳይ በተመለከተ ለምን ለስቃይ ተዳረጉ ንጹሓን ለስቃይ ለምን ለሚለው ጥያቄ መልስ የለኝም፡ ኢየሱስም’ኳ አንድ ቀመራዊ መልስ አይሰጥም። … ኢየሱስ በዚህ ዙሪይ የሰጠው ስብከትም ሆነ መላ ምታዊ ሃሳብ አላቀረበም ለማቅረብ ይቻለውም ነበር። ነገር ግን እንዲህ አላደረገም። በመካከላችን እየኖረ ለምን እንደምሰቃይ አላብራራልንም። ሆኖም ለምን እንደምንሰቃይ በመሰቃየት መልስ ሰጥቶናል። ለዚህ ሰብአዊ ተመክሮ መልስ ለመስጠት በመካከላችን ሆኖ ለሚሰቃየው ፍቅሩን በመግለጥ ስለዚህ ለምን ሳይሆን ለማን በሚለው መንገድ ነው መልስ የሚሰጠን። ትልቁ በሽታ ቀቢጸ ተስፋነት ነው። እየተዛመተ ያለው በሽታ እርሱ ነው። ሕፃናት የዚህ በሽታ ፍቱን መድሃኒት ናቸው በተለይ ደግሞ በጠና የታመሙት ሕፃናት፡ ቅዱስ ጳውሎስ በተስፋ ነው የዳንነው ይላል። ይኽ እውነተኛ ተስፋ መስካሪያን ናቸው። ይኽ ተስፋ ለክርስትና ሕይወት ነዳጅ ነው።

ሰረና 27 ዓመት ዕድሜ ያላት በዚህ በሕፃነ ኢየሱስ ማከሚያ ቤት ሕክምና መከታተል የጀመረቸው ገና የ 13 ዓመት ዕድሜ እያላት መሆኑ በመግለጥ ይህች በከባድ ሕመም የተጠቃቸው ወጣት በአሁኑ ወቅት ሐኪም ለመሆን በስነ ሕክምና መንበረ ጥበብ ታማሪ ለመሆን የበቃችና ሐኪም መሆን የሕይወት ተስፋ በሚል አጋላለጥ በመግለጥ ከስቃይዋ የሕይወት ተስፋ የመሆን ጥሪ ለመቀበል ችያለሁ ስትል ስቃይዋን ለጥሪዋ ብሶል እንደሆናት ቅዱስነታቸው የስቃይዋን ትርጉምን ተንትነው፡ ወቅታዊው ዓለም ስቃይ ህመም መታየት ፈጣን ውጤት ልታይ ልታይ ባይነት የሚል ሆኗል ኢየሱስ ግን ምድራዊ ሕይወቱን በትህትና ነው የኖረው። በአሁኑ ወቅት እንደሚደረገው የጨቅላነት ጣፋጩ ዓመታት ሳታጣጥም ወደ ጎልማሳነት የሚያሻግር ፈጣን ባህል አማካኝነት ሳይሆን በቤተሰብ ውስጥ ባህርያዊ እድገቱን ጠብቆ ከማርያምና ከዮሴፍ እየተማረ እንደ ማንኛውም ሕፃን ባህርያዊ እድገቱ ተጠብቆለት ነው ያደገው። እግዚአብሔር በትስብእቱ ኀይለኛና ብርቱ ሳይሆን እንደ ማንኛውም ሕፃን ደካማ ገዛ እራሱን ለመከላከል እንደማይችል ሆኖ ነው የተገለጠው። ሰብአዊነት ቦታና ጊዜ ይፈልጋል።

ይኽ ሕፃነት ኢየሱስ ማከሚያ ቤት ባለ ታሪክ እጅግ እያደገ የስነ ምርምርና የስነ ግኝት ጥበቦች ያስጨበጠና የተካነ የእደ ጥበብ ምንጣቄ ተክኖ በአሁኑ ወቅት ልክ እንደ ቀድሞው ታዋቂ የሥነ ሕክምና ተመራማሪ ሊቃውንት የሚያገለግሉበትና የሚያፈራም ነው። እንደ ስሙም በዚህ ሳይታጠር ኵላዊነት ባህርይ በመላበስም ከተለያዩ የዓለምችን ክልሎች ህሙማን ሕፃናትን በማስመጣትም ሆነ የሕክምና ሊቃውንቱን በመላክ አቢይ ግልጋሎት ይሰጣል።

ይኽ ንብረትነቱ የቅድስት መንበር የሆነው ማከሚያ ቤት ሕፃነ ኢየሱስ የሚል መጠሪያ ሲሰጠው አለ ምክንያት አይደለም። አገልግሎት ኢየሱሳዊ በመሆኑ ኵላዊ ነው ብሏል።

በዚህ የማከሚያ ቤቱ መንበረ ጥበብ የሚማሩት ለሥራው ዓለም ፍጆት ሳይሆን የላቀው የሰው ልጅ ክብር እንዲከበር ለማድረግ የተጠሩ መሆናቸው አውቀው በእውቀትና በጥበብ ተክነው የሕይወት ባህል የሚያስፋፉ ይሁኑ ያሉት ቅዱስነታቸው አያይዘው፡ ሥራ ለማኅበራዊ ጥቅም ላይ ያነጣጠረ በደሞዝ ተከፋይነትም ለእራስ ጥቅም ያተኰረ ነው ሆኖም የእራስ ጥቅም ለማኅበራዊ ጥቅም የሚበጅ እንጂ ማኅበራዊ ጥቅም ዕዳ ለሚያደርግ ግላዊ ጥቅም የሚያተኩር መሆን የለበትም እንዳውም ሥራ ተልእኮ ኃላፊነትና ጥሪም ነው ማገልገል ገዛእ እራስ ለመስጠትና ለማፍቅር የሚያግዝ መሆን አለበት እንዳሉ አኵይሊኖ አስታውቋል። በመጨረሻም ንግግር ያስደመጡት የማከሚያ ቤቱ መሥተዳድራዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ማሪየላ ኤኖክ ይኽ ታዋቂው ማከሚይ ቤት የሥልጣን ወይንም የትርፍ ማካበቻ ማእከል ሳይሆን ስለ ሕይወት ሕይወት የሚሰጥበት ማእከል ነው የሚል ሃሳብ እንዳሰመሩበት አኵይሊኖ ይጠቁማሉ።








All the contents on this site are copyrighted ©.