2016-12-15 11:39:00

ከቫቲካም ሬዲዮ የአማሪኛ የስርጭት ክፍል የተላለፈው የረዕቡ የታኅሣሥ 5/2016 ዓ.ም. ዜና።


ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሣሥ 3/2009 ዓ.ም. ለዓለም የፖለቲካ ኋይሎች ባስተላለፉት የሰላም መልዕክት ዓለማችን እያጣች ያለውን “ነውጥ አልባ” የሆነ የፖለቲካ ባሕል መልሳ ትጎናጸፍ  ዘንድ ጥሪ አድርገው ለግጭቶች ወታደራዊ ምላሽ መስጠት ግጭቶችን የባሰ ከማፋፋም የዘለለ ፋይዳ እንደ ሌለውም ጭምረው አሳስበዋል።

ሙሉ ዜናውን ከእዚህ በታች ያለውን ተጫወት የሚለውን ምልክት በመጫን ማዳመጥ ይችላሉ።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮ ይህንን መልዕክታቸውን ያስተላለፉት ባለፈው ሰኞ እለት ሲሆን ይህም በመጭው ታኅሣሥ 23/2009 ዓ.ም. የዛሬ 50 ዓመት ገደማ በጊዜው የነበሩ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጳውሎስ 6ኛ  ዓለማቀፍ የሰላም ቀን ይከበር ዘንድ ጥሪ ባደርጉት መሰረት ሲሆን ቅዱስነታቸው ይህ አሁን ያስተላለፉት የሰላም ጥሪ ይህንን የሰላም ጥሪን የማስቀጠል ባሕልን ተከትሎ የተተገበረና የእዚህን የሰላም ጥሪ 50ኛ ዓመትን ለመዘከር ታስቦ የተላለፈ የሰላም መልዕክት መሆኑም ጨምሮ ተግልጹዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.