2016-12-14 16:20:00

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መእክት በዳካ ለተካሄደው ለዓለም አቀፍ ጉባኤ


እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 9 ቀን እስከ ታህሳስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. በባግላደሽ ርእሰ ከተማ ዳካ “ስደትና ልማት” በተሰኘው ርእስ ዙሪያ በመከረው ዓለም አቀፍ ጉባኤ ቅድስት መንበርን ወክለው የተሳተፉት የስደተኞችና ተጓዦች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ የስካላብሪያኒ ማኅበር አባል አባ ጋብሪኤለ በንቶሊዮ እንደነበሩ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ጠቁሞ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መንግሥታትና የክልሎች የፖለቲካ ባለ ሥልጣናት በዓለማችን እየተከሰተ ያለው የሕዝቦች ጸኣትና መፈናቀል የጠቆሰው ዓመጽ መፍትሔ እንዲያገኝ በማድረጉ ተግባር በመተባበር ይኽ ማኅበራዊ ክስተት መፍትሔ እንዲያገኝ አደራ እንዲበራቱ ማለታቸው ወደዚሁ የዳካ ጉባኤ በቅዱስነታቸው ስም መልእክት ያስተላለፉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ፒየትሮ ፓሮሊን እንዳሰመሩበት አክሎ ያመለክታል።

ለዳካው ጉባኤ የቅዱስነታቸውን መልእክት በማስደገፍ ንግግር ያስደመጡት አባ በንቶሊዮ “ይሴባሕ” የተሰየመውን የቅዱስ አባታችንን ዓዋዲ መልእክት ዋቢ በማድረግ የዓለም አቀፍ ኤኮኖሚ በኃላፊነት የሚያስሥተዳድር ዓለም አቀፍ መሥተዳድራዊ ሥርዓትና አካል ያለው አስፈላጊነት ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ ከመሆኑ ባሻገር ይኽ ሥርዓትና አካልም ነጠላ ኤኮኖሚዎች ተከስቶ ያለውን የኤኮኖሚ ቀውስ ተጋፍጦ ሊያቃልለውና ደረጃ በደረጃ መፍትሔ የማሰጠት ብስለት የሁሉም ሕዝቦች በተለይ ደግሞ የድኾችን ጥቅም በማስቀደም ከዚሁ ጋር በማካተትም የጦር መሣሪያ ምርት ቅነሳ በማነቃቃና እግብር ላይ በማዋል የሕዝቦች ምግብ የማግኘት ሰብአዊ መብትና ክብር በሙላት በመዋስ ሰላም ለማረጋገጥ ተፈጥሮ የመንከባከብ ኃላፊነት የሚያበክር የስደተኛው ጸአት ሥርዓት ወጥ እንዳይሆን ይኸንን ማኅበራዊ ክስተት ለማስተዳደር የሚያግዝ ሕግ እንዲያስቀምጥ የተሰኙት ኃላፊነቶችን የሚወጣ መሆን እንደሚገባው አሳስቧል።

አባ በንቶሊዮ ይላሉ የስደተኛው ጸአት እልባት ወይንም በተቀራረበ ደረጃ እየተሻሻለ ሳይሆን በይባስ መጠነ ሰፊ እየሆነ ከደቡብ ወደ ምዕራብ ዓለም የሚጎርፈው የዓለም ሕዝብ ብዛት እጅግ ከፍ እያለ ነው። በርግጥ ለተሰዳጅነት የሚዳርጉት ጠንቆች ሥር ነቀላዊ መፍትሔ ለማሰጠት ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ መፍትሔ ማረጋገጥ ወሳኝ ነው። ከዚሁ ጋር በማያያዝም ስደተኛው በሚተናገድበት አገር በእድገት ሂደት የሚኖረው አወንታዊ አስተዋጽኦ ግምት ከመስጠት ይልቅ እንደ ችግር ብቻ በመመልከት በተለያዩ አገሮች የሚሰጡት መግለጫዎች ወይንም የሚተገበሩ የስደተኛ የማስተዳደሪያ ሕጎች ሰብአዊነት ብሎም የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ማእከል ከማድረግ ይቅል ፍርሃት ማእከል በማድረግ በአሰተናጋጅና በተስተናጋጁ ሰው መካከል መቃቃር እንዲኖር ሲያደርግ ይታያል። ትብብር ሰብአዊነት ማነቃቃት ያስፈልጋል እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍም መግለጫ ይጠቁማል።

ቅድስት መንበር ዘወትር ሰአዊነትና የሰው ልጅ ክብር ማእከላዊ መሆን እንደሚገባው ታሳስባለች። ይኸንን መሠረት በማድረግ የስደተኛው መብትና ግዴታ በማስታወስ ሁሉም ካለው ሁኔታ አንጻር የመብትና የግዴታ ጭምር ባለ ቤት መሆኑ ታስተምራለች። ስለዚህ መብት ጠያቂው ግዴታ ተወጭ ጭምር መሆን እንዳለበት በማስገንዘብ ማኅበራዊ መቃናት እንዲኖር አቢይ አስተዋጽኦ በመስጠት ላይ እንደምትገኝ የስደተኞችና የተጓዦች ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ዋና ጸሓፊ ገልጠው፥ በዚህ አኳያ ስደተኛው ለተስተናገደበት አገር እድገት ያለው ተሳታፊነት ከዚያ እ.ኤ.አ. በ 2030 ዓ.ም. ተደራሽ እንዲሆን ተብሎ ከተወጠነው የልማት እቅድ ጋር በማያያዝ የልማት እቅዱን ለማስጨበጥ ከሚደገፉት ተግባሮች ውስጥ አንዱ ነው ብሏል ያለው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ ቤተ ክርስቲያን ጥንትም አሁንም እውነታውን ግድ የማይል በሰዎች ላይ የሚሰነዘረው ልሙድ ቅድመ ትንተናና ቅድመ ፍርድ ጨርሶ እንዲወገድ በማስተማር ብቅ ለሚሉት ማኅበርዊ ክስተቶች በተጨባጭ አገባብ ገጥሞ የሰብአዊ መብትና ክብር ላይ በማተኰር የሰው ልጅ መብትና ክብር እንዲከበር በማሳሰብ መፍትሔ ንዲያገኙ ትደግፋለች። በዚህ ብቻ ሳትታጠር በዚሁ ጉዳይ ላይ በማነጽና በማስተማር ተዋህዶ ለመኖር የሚያግዝ ፖለቲካ ያለው አስፈላጊነት ለሁሉም አገሮች መንግሥታት ጥሪ ታቀርባለች።

በተቀረው አስተናጋጅና ተስተናጋጁ የእርስ በእርስ መከባበር በግልና በመንግሥታዊ ተቋምነት ደረጃ እንዲረጋገጥና ይኽ ደግሞ ስደተኛው ያለበትን ዘርፈ ብዙ ችግርና ለስደት የዳረገው መዓት መከራ ድኽነት ወዘተርፈ ያስከተለበት ስነ አእምሮአዊ ጫና በማስተዋል ሁሉን ስደተኛ በጥቅል ሳይሆን የእያንዳንዱ ሁነት ከመጣበት ዜጋ የሆነበት አገር ፖለቲካዊ ማኅበራዊ ኤኮኖሚያዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አዛምዶ በተናጥል በመመልከት ተዋህዶ እንዲኖር ማገዝ ስለዚህ በዚሁ ዘርፍ ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠው አቢይ አገልግሎት ግልጽ ነው፡ ይኽ ደግሞ አንዱ የሐዋርያዊ አገልግሎቷ ዘርፍ ነው፡  አገልጋይ ነችና፡ ይኸንን እይታ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ “ምሉእ” በሚለው ቃል ዙሪያ፥ ምሉእ ሰብአዊነት፡ ምሉእ እድገት፡ ከሚለው ሥልጣናዊ ምዕዳናቸው ጋር በማጣመር የምትከውነው አገልግሎት ነው  ያሉት አባ በንቶሊዮ፥ ስደተኛው በተመለከተ የሚሰጡት መግለጫዎች ስለ ስደተኞች መጉረፍ ሲነገር ይኽ ያክል ገቡ ይኽን ያክል ደግሞ በባህር ወይንም በየብስ ጉዞ እያሉ የሞት አደጋ አጋጠማቸው ተሰውረው የቀሩ ሴቶች ሕጻናት እየተባለ በቁጥር ብቻ ሲተነተን እንሰማለ። ሆኖም ሰው ቁጥር አይደለም ሰብአዊ ነው። ክብር ያለው ነው። ስለዚህ የስደተኛው ጣፋጭ የግጥም ቃላት አድርጎ እንደ ረቂቅ ሃሳብ በማቅረብ የስነ ጽሑፍና ድርሰቶች ባህርይ አድርጎ ማስቀመጥ ሳይሆን አካል ለበስ ክብርና መብት ያለው ተጨባጭ ነው። ይኸንን አቢይ ግምት በመስጠት አገሮች መግሥታት የፖለቲካ አካላት ሰብአዊነት ማእከል ያደረገ ፖሊቲካ እግብር እንዲያውሉና ስደተኛው በተራውም ኃላፊነቱን አውቆ ግዲታውን እንዲወጣ ሊደገፍ ይገባዋል።

ስደተኛው ለሚስተናገድበት አገር ኤኮኖሚ ድጋፍ ብቻ ሳሆን በባህል በቋንቋን በኃይማኖት ረገድም ሳይቀር ግባት ነው። ብሔራዊነት ወደ ዓለም አቀፋዊነት የሚሸኝ ተጨባጭ ድጋፍ ነው ካሉ በኋላ፥ ክቡርነታቸው ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ፤ እላይ እንዳስታወሱት ስደተኛውን ተገቢ ድጋፍ ያሻዋል። መብቱንና ኃላፊነቱንም ማሳወቅ ተዋህዶ እንዲኖር መደገፍ፡ አስፈላጊ እንክብካቤ እንዲያገኝ ማድረግ። ነገር ግን ለስደት የሚዳርጉት ጠንቆች መፍትሔ እንዲገግኙ መንግሥታት በዓለ አቀፍ ደረጃ አቢይ ጥረት ሊያደርጉ ይገባቿል። የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ፍትሕና ሰላም እንዲረጋገጥ ማነቃቃት። ጦርነት አመጽ ምግባረ ብልሽት ድኽነት ኢእኩልነት ወይንም አድልዎ የተፈጥሮ ብከላ የበለጸገው ዓለም በድኾች አገር ላይ የሚከተለው የኤኮኖሚ እቅድና የተፈጥሮ ሃብት ብዝበዛ ተግባር የመሳሰሉት ስደት እንዲኖር የሚያደርጉ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ጠንቆች ሁሉ የበለጸገው ዓለም መለስ ብሎ ፖለቲካዊ የኅሊና ምርመራ በማድረግ ሰብአዊነት ቀዳሚነት እንዲይዝ ማድረግ ይጠበቅበታል እንዳሉ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል አስታወቅ።








All the contents on this site are copyrighted ©.