2016-12-13 10:53:00

ቅዱስነታቸው የእናታችን ቅድስት ማሪያም ዘ ጓዳሉፔ በዓል ወላጅ አልባ ልጆች እንዳልሆንን ያስታውሰናል አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሣሥ 3/2009 ዓ.ም. አመሻሹ ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ ፓዚሊካ የላቲን አመሪካ ሀገራት ጠባቂ የሆነችውን የቅድስት ድንግል ማሪያም ዘ ጓዳሉፔን በዓል አስመልክተው መስዋዕተ ቅዳሴን ማሳረጋቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ባሳረጉት መስዋዕትተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት የእናታችን ቅድስት ማሪያም ዘ ጓዳሉፔ በዓል ወላጅ አልባ ልጆች እንዳልሆንን ያስታውሰናል ካሉ ቡኋላ ወንድማቻችንን እና እህቶቻችንን መንከባከብ እንድንችል በፍቅር ዓይኑዋ ታስተምረናለች ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ግለጹት “እርግጠኛ በሆነ መልኩ እምነትን ማክበርና ማገልገልን ከእርሷ መማር ይቻላል ይህም ትምህርት እራሳችንን በምን ዓይነት ሁኔታ እራሳችንን ጨውና ብርሃን ማድረግ እንደምንችል በመርዳት ለራሳችንን ሕይወት እና ለማሕበረሰቡ አገልግሎት ማዋል እንደምንችል ይረዳናል ብለዋል።

በተቃራኒው አሉ ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት በተቃራኒው አሁን የሚገኘው ማኅበረሰብ “ልዩነትን በመፍጠር የተካነ ነው” ካሉ ቡኋላ “ይህም እምነት ሊጣልበት የማይችል ማኅበረሰብ እንደ ሆነም” ጨምረው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “ይህ ማኅበረሰብ ራሱ በሠራው ሳይንሳዊ ፈጠራ የሚኩራራ እና በቴክኖሎጂ የረቀቀ፣ ነገር ግን አብዛኛው የማኅበረስብ ክፍል በሚጠፋብት ወቅት በጭፍን የሚመለከት የጥቂቶች ጌጥ እና ኩራት የሆነ ማኅበረሰብ እየሆነ ማምጣቱንም” ጨምረው ገልጸዋል።

“ተወዳጅ የሆኑት የላቲን አሜሪካ ሀገራት ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናትን በመንገድ ላይ መመልከት እየተለመደ የመጣ ጉዳይ መጥቱዋል” ያሉት ቅዱስነታቸው “በየመንገዱ እና በየባቡር ጣቢያዎቹ ወይም ደግሞ በአገኙበት ሥፍራ ሁሉ እይተኙ ለእነርሱ በሕይወታቸው ምንም ዓይነት ተስፋ እንደ ሌላቸው እየተሰማቸው እንደ ሆነም አበክረው ገልጸዋል።

“በእዚህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ ሁሉ ልክ እንደ ኤሊሳቤጥ ‘ስለ አመንሽ ብጹዕ ነሽ!” ከሚለው ሁኔታ በመማርና እምነትን በማገልገል እናታችንን መምሰል ይጠበቅብናል” ያሉት ቅዱስነታቸው እናታችን ማሪያም ዘ ጓዳሉፔ እናት እንዳለችን ታስታውሰናለች ብለው “ከሁሉም በላይ ማሪያምን ማክበር ከመቼው ጊዜ በላይ መቼም ቢሆን ወላጅ አልባ እንዳልሆንን ያሳስበናል ብለዋል። እናት አለን፣ እናት ባለችበት ሰፍራ ደግሞ ወንድሞች ሊጣሉ ይችላሉ ነገር ግን የተብብር መንፈስ ግን ሁሌም ቢሆን ያሸንፋል በማለት አክለው ገልጸዋል።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማብቂያ ላይ እንደ ገለጹት ማሪያም የነበራት እምነት እንድትወድ እና አገልጋይ እንድትሆን መርቱዋታል ካሉ ቡኋላ “ የማሪያምን መታሰቢያ በዓልን ማክበር ማለት እኛም እንደ እርሷ እንድንነሳ እና ወደ ፊት እንድንራመድ መጠራታችንን ያሳስበናል፣ ይህንንም መከወን የሚገባን የእርሷን ምልከታ በመላበስ እና እርሷ ባሳየችን የምሕረት ተግባራት በመፈጸም ሊሆን ይገባል ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.