2016-12-13 09:47:00

ቅዱስነታቸው በ3ኛው የስብከተ ገና ሰንበት እለት ክርስቲያኖች "ሁል ጊዜ በጌታ ደስ እንዲሰኙ" ጥሪ አቀረቡ።


እንደ አዎርፓዊያን የስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር በትላንትናው እለት ማለትም በታኅሣሥ 2/2009 ዓ.ም. ሦስተኛው የስብከተ ገና ሳምንት በተከብሮ የነበረ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ይህም እለት ቅዱስ ሐዋሪያው ጳውሎስ ወደ ፊሊጲሲዩስ ሰዎች በጻፈው መልዕክቱ ላይ እንደ ገለጸው “ሁል ጊዜም በጌታ ደስ ይበላችሁ አሁንም ደግሜ እላችኋለሁ ጌታ በቅርብ ጊዜ ስለሚመጣ በድጋሜ ደስ ይበላችሁ” ከሚለው ጭብጥ በመነሳትሳ ቤተ ክርስቲያን ይህንን 3ኛ የስብከተ ገናን ሳምንት “የደስታ ሰንበት” ብላ እንደ ሰየመችሁ ይታወቃል።

በእለቱም ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በቅዱስ ጴጥሮ አደባባይ ለተሰበሰቡ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኝዎች ባሰሙት ቃል እንደ ገለጹት የደኅንነት አዋጅ ሁሉምን ነገር የመቀየር ብቃት አለው “በረሃው ይለመልማል፣ መጽናናት እና ደስታ ልባችንን ይሞላል” ማለታቸውም ታውቁዋል።

ቅዱስነታቸው በእለቱ ከማቴዎስ ወንጌል በተወሰደው ታርክ ላይ ተመስርተው “ኢየሱስ ዐይነ ስውር ሆኖ የተወለደውን ሰው መፈውሱን፣ ሽባዎች እንዲራመዱ፣ ለምጽማች ከለምጻቸው እዲነጹ፣ መስማት የተሳናቸው እንዲሰሙ፣ ሙታን እንዲነሱ፣ ድኾች የምስራቹን ቃል እንዲሰሙ ማድረጉን የሚያወሳው ታሪክ” አሉ ቅዱስነታቸው “በቃላት ብቻ የተገለ ነገር ሳይሆን በተግባር የታየ እውነታ መሆኑን” ገልጸው ይህም በኢየሱስ አማካይነት የተሰጠን ደኅንነት በድጋሚ አዲስ ፍጥረት የማድረግ ብቃት እንዳለው ያሳያል ብለዋል።

ስለዚህም በእዚህ ስሜት ተሞልተን ልክ የዛሬው ሦስተኛ የስብከተ ገና ሳምንት እንደ ሚያሳስበን በሐሴት ልንሞላ ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ምክንያቱም ክርስቶስ የሚወለድበት የገና እለት እየቀረበ መሆኑን በየመንገዱ ከምናያቸው ምልክቶች መረዳት ይቻላል ብለዋል።

“እነዚህ ውጫዊ የገና በዓል ምልክቶች ሁልጊዜ ወደ እኛ በመቅረብ ልባችንን ለሚያንኳኳው ጌታ ማቅ ያለ አቀባበል ማድረግ እንደ ሚጠበቅብን ጥሪ ያደርጉልናል” በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም በተጨማሪም ኢየሱስን በድኾች እና በተቸገሩ ሰዎች ውስጥ እንድንፈልግም ያሳስበናል ብለዋል።

ደስተኛ ያልሆነ አንድ ክርስቲያን በሕይወቱ የሚጎለው ነገር አለ ማለት ይቻላል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ዛሬ ልያድነን በሚመጣው ጌታ ምክንያት እንድንደሰት ተጠርተና፣ ስለሆነም ሁላችንም ይህንን ደስታ ከሌሎች ጋር በመካፈል በተለይም ለድኾች፣ ለታመሙ፣ ብቸኛ ለሆኑ እና ደስተኛ ላልሆኑ ሰዎች ምቾትን እና ተስፋን መልሰው ይጎናጸፉ ዘንድ መርዳት ይጠበቅብናል” ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.