2016-12-10 11:00:00

የቫቲካን ሬዲዮ የአርብ የኅዳር 30/2009 ዓ.ም. የአማሪኛ ዜና።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 29/2009 ዓ.ም. እንደ አውሮፓዊያን የስርዓተ ሉጥርጊያ አቆጣጠር የተከበረውን ያለ አዳም ኋጥያት የተጸነሰች እመቤታችን ድንግል ማሪያ አመታዊ በዓልን ለመታደም በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ለተገኙ ምዕመናን እና የሀገር ጎብኚዎች ባደረጉት አስተምህሮ ክርስቲያኖች የማሪያምን አርሃያ ተከትለው ለእግዚኣብሄር ጥሪ “እንዳልከኝ ይሁንልህ” ማለት ይጠበቅባቸዋል ካሉ ቡኋላ ይህም  በኋጥያት ምክንያት ያረጀውን ማንነታችንን ቀይሮ እግዚኣብሔር በሕይወታችን አዲስ ታሪክ እንዲያከናውን እድሉን ይሰጠዋል ብለዋል።

የዜናውን ሙሉ ይዘት ከእዚህ በታች ያለውን የማጫወቻ ምልክት በመጫን ማዳመጥ ይችላሉ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ በተነበቡት ምንባባት ላይ ትኩረታቸውን አድርገው በኦሪት ዘፍጥረት ውስጥ የተጠቀሰውን የአዳም እና የሄዋን ውድቀትን በተመለከተ እና እንዲሁም በሉቃስ ወንጌል ላይ የተጠቀሰውን መልአኩ ገብርኤል ማሪያምን ያበሰረበት ታሪክ ላይ ተመርኩዘው ቃል እግዚኣብሔር ያሰሙ ሲሆን እነዚህ ሁለት ምንባባት በእግዚኣብሔር እና በሰዎች መካከል ለተፈጠረው ግንኙነት ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉ ክስተቶች እንደ ነበሩ ጠቅሰው በአጠቃላይም እነዚህ ምንባባት የመልካም እና የክፉ ነገሮች ሥር መሰረት ምን እንደ ሆነ እንድንረዳ ያስችሉናል ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.