2016-12-07 13:33:00

ቅዱስነታቸው "ክርስቲያኖች ተስፋን ስንቃቸው ልያደርጉት ይገባል አሉ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ ዘወትር ረዕቡ እና እሁድ የጠቅላላ አስተምህሮን እንደ ሚያከናውኑ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው እለት ማለትም በኅዳር 28/2009 ዓ.ም. የሰጡት አስተምህሮ “የክርስቲያን ተስፋ” በሚል ጭብጥ ላይ ያተኮረ እንደ ነበረ የታወቀ ሲሆን የስብከተ ገና ወቅት የመጠባበቂያ ወቅት፣ አጽናኝ የሆነውን የምንጠባበቅበትና ቃል ሥጋ የሆነበትን በማስታወስ የገናን ብርሃን የምንጠባበቅበት ወቅት በመሆኑ የተነሳ ተስፋ የሚለውን ጭብጥ አሁን በያዝነው የስብከተ ገና ወቅት በጥልቀት መመልከት አስፈላጊ ነው በለዋል።

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ!

በዛሬው እለት የማቀርብላችሁ አስተምህሮ የክርስቲያን ተስፋ በሚል ጭብጥ ዙሪያ ነው። ሰይጣን በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ በሚመስልበት በአሁኑ ወቅት ተስፋ የክርስቶስን ጌትነት እንድንገነዘብ በማድረግ ስለሚያጽናናን፣ ኋጥያትን ሁል ጊዜ በአሸናፊነት እንደ ሚወጣ፣ እዲሁም በቀጣይነት በመኋከላችን እንደ ሚገኝ እንድንገነዘብ ይረዳናል። በዚህ የስብከተ ገና ወቅት “ተጽናኑ ተጽናኑ ሕዝቦቼ ሆይ! ተጽናኑ!” የሚለውን አጽናኝ የሆነውን የነቢዩ ኢሳያስን ቃል በድጋሚ እንድንሰማ እድሉን ይከፍትልናል።

ነቢዩም እግዚኣብሔር በስደት በባዕድ ሀገር የሚኖሩ ሕዝቦቹን ወደ የቤታቸው መልሶ ያመጣቸው ዘንድ  በበረሃ ውስጥ ለእርሱ መንገድ እንድናቀና የገባውን ቃል በድጋሚ ያስታውሰናል። ይህም እምነታችንን በማደስ በእግዚኣብሔር የማዳን ኋይል እንድነትማመን ይረዳናል። መጥምቁ ዩሐንስ በይሁዳ ሀገር በሚገኘው በረሃ ያስተጋባውም ቃል ለጌታ መንገድ እንድናዘጋጅ የሚያሳስበን ቃል ነበር። መንፈሳዊ መጽሐፍት የኢየሱስ መወለድ በብዙ ሰዎች ዝግጅት የተደረገበት እንደ ነበረ ያሳዩናል ለአብነትም እግዚኣብሔር የሰጣቸውን ተስፋ እስከ መጨረሻ ድረስ አምነው የተቀበሉ ማሪያም፣ ዮሴፍ ዘካሪያስ እና ኤልሳቤጥን መጥቀስ ይቻላል። ከእነርሱ ተስፋ በመማር በረሃነት የሚያጠቃውን ልባችንን ቀይሮ የደስታ የአተክልት ስፍራ ያደርገው ዘንድ  የአዳኛችንን መምጣት በተስፋ መጠባበቅ ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ አስተምህሮዋቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.