2016-12-06 08:48:00

የኅዳር 26/2009 ዓ.ም. የቫቲካን ሬዲዮ የአማረኛ ዜና።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በኅዳር 25/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ አስተምህሮን ለመከታተል ለተሰበሰቡት ምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች ባስተላለፉት መልዕክታቸው “የእግዚኣብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ነው የሚለው አስተምህሮ ክርስቲያኖች የተልዕኮዋቸው ዋነኛ መልዕክት አድርገው ሊወስዱት ይገባል” ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ የሰጡት አስተምህሮ ትኩረቱን በእለቱ በተነበበውና “የእግዚኣብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ስለሆነች ተጸጽታችሁ ንስኋ ግቡ” በሚለው የወንጌል ቃል ላይ አትኩሮ የነበረ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚህ የወንጌል ቃል ላይ ተመርኩዘው እንዳብራሩት ኢየሱስም የመጀመሪያውን ሚሲዮናዊ አገልግሎቱን ከገሊላ የጀመረው ተመሳሳይ ቃል በመጠቀም ነው ደቀ መዛሙርቱም የመጀመሪያ ሐዋሪያዊ ልምድ እንዲቀስሙ ያደረገው በእዚሁ መልክ ነው ብለዋል።

የኅዳር 26/2009 የአማርኛ ዜናን ያዳምጡ








All the contents on this site are copyrighted ©.