2016-12-05 16:20:00

የፊሊፒንስ ብፁዓን ጳጳሳት ጥሪ


በፊሊፒንስ ደሴቶ ውስጥ በዚያ የምስልምና እምነት ተከታይ ዜጋ አብላጫ በሆነበት በሚንዳናው ደሴት እ.ኤ.አ. ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም. በአንድ በክልሉ በሚገኘው ቤተ ክርስቲያን ላይ ጥቃት መጣሉ ሲገለጥ። አሁንም በካቶሊክ ማኅበረሰብና አቢያተ ክርስቲያን ላይ ተመሳሳይ ጸረ ካቶሊክ ጥቃት ይጣላል የሚል ስጋት እንዳለ የአገሪቱ ብፁዓ ጳጳሳት ምክር ቤት በመግለጥ የአገሪቱ መንግሥት የካቶሊክ ምእመናን ጸጥታና ደህንነት እዲያስጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል።

ጥቃቱን የጣለው ገዛ እራሱን ማውቴ በሚል መጠሪያ የሚገልጠው ከዳኢሽ ማለትም ከአሸባሪው እስላማዊ መንግሥት ጋር ግኑኝነት አለው ተብሎ የሚነገርለት የምስልምና እምነት አክራሪ ቡድን ሊሆን እንደሚችል ጥርጠራው ያለ ሲሆን በርእሰ ብሔር ዱተርተ የሚመራው መንግሥት የምእመናን ሕይወና ጸጥታ ደህንነት ካላስጠበቀ ምእመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን ለመሄድም ሆነ በጋራ በመሰባሰብ እምነቱን ለመኖር የሚያደርገው ክርስቲያናዊ ተግባር ሁሉ እንዳይፈጽም ያዳግቷል ሲሉ ጳጳሳዊ ለኡካነ ወንጌል ማኅበር አባል በፊሊፒንስ በአስፍሆተ ወንጌል የተሰማሩት አባ ጆቫኒ ረ በስልክ ከቫቲካ ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቋል።

ባለፈው እሁድ ጥቃቱ የተጣለበት ክልል ውጥረት የሚታይበትና በዚያ ክልል ያለው አለ መረጋጋት የቅርብ ጉዳይ ሳይሆን የቆየ ነው። በቤተ ክርስቲያኑ አቅራቢያ ከተጣለው ጥቃት ትከትሎ ጥቂት ቀናት በኋላም በአገሪቱ በሚገኘው በተባበሩት የአመሪካ መንሥታት ልኡክ መንግሥት ሕንፃ ክልል አንድ የፍንዳታ ቦምብ ተገኝተዋል። ከዚህ ቀጥሎም ወታደሮችን አሳፍሮ ይጓዝ በነበረው የጦርሰራዊት መኪና ላይም ጥቃት ተጥሏል። ይኽ ሁሉ ጥቃትና የጥቃት ሙከራ መንግሥት ከእነዚህ ኃይሎች ጋር ውይይት በማድረግ ወደ ሰላም እንዲደረስ የሚያደርገው ሙከራ አክራሪው ኃይሉ እምቢ ማለቱና ከዳኢሽ ጋር ግኑኝነት እንዳለው የሚያረጋግጥ ተግባር ነው፡ ምክንያቱም ገዛ እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚጠራው አሸባሪው ኃይል ምርጫ የሚያንጸባርቅ ነውና።

ቤተ ክርስቲያን ሁሌም ውይይት የግጭትና የሁከት መፍትሔ መሆኑ ታሳስባለች በዚሁ ጉዳይ ሥርም በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንና በምስልምና ሃይማኖት መካከል ቀጣይ ውይይትና ግኑኝነት ሲከናወን ይታያል። የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ለሰላም መሰረት ነው ብለው ያምናሉ ሆኖም በሚንዳናው ክልል ነጻ እስላማዊ መንግሥት ለማቆም ያለመ የምስልምና እምነት ተከታይ ኃይል በሃይማኖቶች መካከል የሚደረገው የጋራው ውይይትና ግንኙነት ፈጽሞ አይደግፍም። ሆኖም ይኽ በፊሊፒንስ የሚታየው 50 ዓመታት እያስቆጥረ ያለው ውጥረት ሃይማኖታዊ ነክ ብቻ አድርጎ መመከቱ ስህተት ነው። ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ገጽታም አለው ብለው ውይይት ሰላም ያስገኛል ሆኖም ተወያይ ኃይሎች በተናጥል የሚጠይቁት ግላዊ ፍላጎታቸው ለማርካት ግትርነት ይዘው የሚሳተፉ ከሆነ የሚከናወኑ ውይይቶች ለይስሙላ ሆኖ ነው የሚቀሩት ሲሉ ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.