2016-12-05 14:12:00

ቅዱስነታቸው ፍቅር እና ትህትና ባለበት ሥፍራ ሁሉ የእግዚኣብሔር መንግሥት በእዛ ይገኛል ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በኅዳር 25/2009 ዓ.ም. በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የጠቅላላ አስተምህሮን ለመከታተል ለተሰበሰቡት ምዕመናንና የሀገር ጎብኝዎች ባስተላለፉት መልዕክታቸው “የእግዚኣብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ነው የሚለው አስተምህሮ ክርስቲያኖች የተልዕኮዋቸው ዋነኛ መልዕክት አድርገው ሊወስዱት ይገባል” ማለታቸው ተገለጸ።

ቅዱስነታቸው በእለቱ የሰጡት አስተምህሮ ትኩረቱን በእለቱ በተነበበውና “የእግዚኣብሔር መንግሥት በመካከላችሁ ስለሆነች ተጸጽታችሁ ንስኋ ግቡ” በሚለው የወንጌል ቃል ላይ አትኩሮ የነበረ ሲሆን ቅዱስነታቸው በእዚህ የወንጌል ቃል ላይ ተመርኩዘው እንዳብራሩት ኢየሱስም የመጀመሪያውን ሚሲዮናዊ አገልግሎቱን ከገሊላ የጀመረው ተመሳሳይ ቃል በመጠቀም ነው ደቀ መዛሙርቱም የመጀመሪያ ሐዋሪያዊ ልምድ እንዲቀስሙ ያደረገው በእዚሁ መልክ ነው ብለዋል።

የእግዚኣብሔር መንግሥት ከሞትን ቡኋላ የሚጠብቀን ስፍራ ማለት ብቻ አይደለም በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን ኢየሱስ ያመጣልን መልካም ዜና ነው ካሉ ቡኋላ እግዚኣብሔር አሉ ቅዱስነታቸው በእምነት፣ በትህትናና በፍቅር ተቀባይነትን ያገኘውን “በታሪካችንና በሕይወታችን ውስጥ ግዛቱን ለመመስረት ይመጣል” ብለዋል።

የእርሱ መንግሥት ተካፋዮች ለመሆን የሚያስችሉን ቅድመ ሁኔታዎች አሉ በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም በሕይወታችን ውስጥ ለውጥ ማምጣት ወይም መጸጸት ነው ብለዋል።

“የእዚህን ዓለም አታላይ የሆኑንትን ነገሮች ለምሳሌም ደካምን በመበደል የሚገኝ ስልጣን፣ የሐብት ጥማት፣ ለጌታ መንገድ ከመክፈት ይልቅ በማንኛውም መልኩ ጊዜያዊ ደስታን መፈለግ የመሳሰሉትን ድክመቶችን ማንኛውንም ዋጋ በመክፈል በማሸነፍ ለጌታ መንገድን ማቅናት ያስፈልጋል በማለት አስተምህሮዋቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ጌታ ትክክለኛ የሆነ ደስታን ይሰጠናል እንጂ ነጻነታችንን አይገፍም ካሉ ቡኋላ የኢየሱስ በቤተልሔም መወለዱ ራስ ወዳድነትን፣ ኋጥያትን እና ሙስናን ለማስወገድ እግዚኣብሔር በመካከላችን እንዲኖር አድርጉዋል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በስተምህሮዋቸው ወቅት ምዕመናን ለመጭው የገና በዓል መንፈሳዊ የሆኑ ተግባራትን በመፈጸም መዘጋጀት እንዳለባቸው ጥሪ አድርገው ለእዚህም ዓይነተኛ ዝግጅትን በማድረግ ሕሊናን በመመርመር፣ ኋጥያታቸችንን በመናዘዝ በተለይም ለሚስጥረ ንስኋ ትኩረት መስጠት እንደ ሚገባን አሳስበዋል።

ቅዱስነታቸው የመለዕከ እግዚኣብሔርን ጸሎት ከምዕመናን ጋር ከደገሙ ቡኋላ “በሚቀጥለው ሐሙስ እለት ለሚከበረው ያለ አዳም ኋጥያት የተጸነሰች እመቤታችን ድንግል ማሪያ ክብረ በዓል ምዕመናን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንዲገኙና አብሮዋቸው ጸሎት እኒያደርጉ ጥሪ አቅርበው በእለቱም በጋራ እመቤታችንን የእናትነት አማላጅነቱዋ ከእኛ እንዳይለይ እና ልባችንን መቀየር እንድንችልና የሰላምን ስጦታ ትሰጠን ዘንድ በጋራ ልንማጸናት ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ አስተምህሮዋቸውን አጠቃለዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.