2016-12-05 14:19:00

ቅዱስነታቸው ኢየሱስ ከኋጥያታችን አንጽቶን ይቀይረንና እንደ ገና ይፈጥረን ዘንድ ልንፈቅድለት ይገባል ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በዛሬው እለት ማለትም በኅዳር 26/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት እንደ ገለጹት ኢየሱስ ከኋጥያታችን አንጽቶን ይቀይረንና እንደ ገና ይፈጥረን ዘንድ ልንፈቅድለት ይገባል ማለታቸው ተገለጸ። ቅዱስነታቸው በእለቱ ያደረጉት ስብከት መሰረቱን አድርጎ የነበረው ምንም ዓይነት የአፍረት ስሜት ሳይሰማን ኢየሱስ በልባችን ውስጥ ያለውን ኋጥያት ያነጻ ዘንድ ልንጠይቀው ይገባል በሚል ጭብጥ ዙሪያ ባጠነጠነው ስብከታቸው እንደ ገለጹት በእዚህ ዓይነት መልክ ብቻ ነው እግዚኣብሔር አንዲስ ሰዎች ልያደርገን የሚችለው ብለዋል።

በረሃው ያለመልማል፣ ዓይነ ስውራን ያያሉ ደንቆሮዎችም ይሰማሉ በሚለው ከትንቢተ ኢሳያስ በተወሰደው የመጀመሪያ ምንባብ ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “መታደስ እንደ ሚገባን ያሳስበናል” ሁሉም ነገር “ከአስቀያሚነት ወደ ውበት፣ ከመጥፎ ወደ ጥሩነት “ እንደ ሚለወጥ ያወሳል ካሉ ቡኋላ የእስራኤል ሕዝብ በተስፋ የመሲህን መምጣት ይጠባበቅ የነበረውም የተሻለ አዲስ ለውጥ በመፈለጉ ምክንያት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል።

ኢየሱስ ደኽንነትን በማምጣት ለሕዝቡ የለውጥ ጎዳናን በማሳየቱ፣ በእዚህም ምክንያት ሕዝቡ ይከተለው እንደ ነበረ የሚያስረዳው ታሪክ ይህንን እውነታ የሚያሳይ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሕዝቡ ኢየሱስን ለመከተላቸውም ዋንኛው ምክንያት የነበረው የኢየሱስ መልዕክት ልብን ዘልቆ የሚገባ በመሆኑ ምክንያት ነው ብለዋል።

“ኢየሱስ ስያከናውነው የነበረው ለውጥ “ከአስቀያሚነት ወደ ውበት፣ ከመጥፎ ወደ ጥሩነት የሚለውጥ ለውጥ ብቻ ሳይሆን ኢየሱስ ሁል ጊዜም ሥር ነቀል የሆነ ለውጥ ነው የሚያደርገው” በማለት ብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የማሳመሪያ ወይም የማስዋቢያ ቅባቶችን በመጠቀም የመቀባባት ሥራ ሳይሆን ኢየሱስ የሠራው ሁሉንም ነገር ከውስጥ በመቀየር አዲስ ፍጥረት በማድረግ ዓለምን እንደ ገና ፈጥሮዋታል፣ በኋጥያት ወድቆ የነበረውን ሰው ከወደቀበት በማንሳት አዲስ ሰው አድርጎት አዲስ ዓለመን ፈጥሩዋል ብለው በዛሬው ወንጌል የምናያውም እውነታ ይህ ነው ኢየሱስ ያን ሰው ከበሽታው ከማዳኑ በፊት ኋጣያቱን ነው በመጀመሪያ ደረጃ ይቅር ያለው ብለዋል። ይህም ከበሽታው የተፈወሰው ሰው አዲስ ፍጥረት ሆነ፣ ያልተገባው የነበረው ሰው የተግባ ሰው ሆነ፣ ይህንንም በማድረጉ  በእዚያ የነበሩ የሕግ መምህራን “በኢየሱስ ላይ መመካከር እና ማጉረምረም ጀምረው ነበር” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ኢየሱስ የነበረውን ስልጣን መቀበል ስላልፈለጉ ነው ካሉ ቡኋላ ኢየሱስ እኛ ኋጥያተኞችን አዲዳዲ ሰዎች የማድረግ ችሎታ አለው” ካሉ ቡኋላ ይህ በሽተኛ ሰው የታመመው በአካል ብቻ ሳይሆን መንፈሱም የቆሰለ ስለነበረ ይህንን ለማዳን ከፍተኛ የሆነ እምነት ይጠይቅ ነበር ብለዋል።

ጌታ “ለገና በዓል በታላቅ እምነት በሚገባ መዘጋጀት እንድንችል፣ ነብሳችንም ማዳን እንድትችል፣ የመኖር ሕልውናችንን እንዲፈውስና አዲስ ፍጥረት እንያደርገን መመኘት ታላቅ እምነትን ይጠይቃል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የሕይወታችንን አቅጣጫ ወደ መልካም መንገድ መቀየር የኢየሱስን ሰላም ያስገኛል ብለው ሁል ጊዜም ቢሆን “እኔ ይህንን የማድረግ አቅም የለኝም” የሚለውን ፈተና አስወግደን ኢየሱስ ይቀር ይለን ዘንድ፣ አዲስ ፍጥረት ያደርገን ዘንድ ልንፈቅድለት ይገባል ብለዋል።

“እኛ ሁላችን ኋጥያተኞች ነን። ነገር ግን የኋጥያታችን ሥር መሰረቱ ምን መሆኑን ማወቅ ያስፈልጋል፣ ጌታም ሥር መሰረቱ ድረስ ሄዶ አዲስ አድርጎ ሲፈጥረው፣ ያ መራራር የነበረው ሥር ይጣፍጣል፣ ፍትህን በማከናወን ያብባል፣ አንተም አዲስ ሰው ትሆናለህ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ነገር ግን “አዎን ኋጥያተኛ ነኝ ብለህ ሂጄ ኋጥያቴን እናዘዛለሁ ብለህ ጥቂት በሆኑ ቃላት ብቻ ከተናዘዝክ ቡኋላ በተመሳሳይ መንገድ መጓዝ ብትቀጥል” እና ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት ያደርገኛል ብለህ መጠበቅ እንደ ማይገባን ጨምረው ገልጸዋል።

በንጻሩም ኋጥያታችንን በምንናዘዝበት ወቅት ሁሉ ከሥር መሰረቱ በመናዘዝ ይህን፣ ይህን እና ያን ሰርቻለሁ በእዚህም ከልቤ አፍርያለሁ! ጌታ ሆይ ልቤን እከፍትልኋለሁ እንደ ገና አዲስ አድርገህ ፍጠረኝ በማለት በእውነተኛ እና ጠንካራ በሆነ እምነት ወደ ገና በዓል መጓዝ ያስፈልጋል ብለዋል።

ብዙን ጊዜ አሉ ቅዱስነታቸው ብዙን ጊዜ “ትላልቅ የሚባሉ ኋጥያቶቻችንን ለመደበቅ እንሞክራለን” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በአንጻሩም እንደ ቅናት ያሉትን ነገሮች አቅልለን እንመለከታቸዋልን ነገር ግን ቅናት በጣም መጥፎና አስቀያሚ የሚባል ኋጥያት ነው ምክንያቱም እንደ እባብ የጥላቻን መርዝ የሚዘራና ሌሎችን በጣም የሚጎዳ በመሆኑ ነው ብለዋል።

ቅዱስነታቸው አጋጣሚውን ተጠቅመው እንዳሳሰቡት “ኋጥያቶቻችንን በጥልቀት በመመልከትና ለጌታ በመናገር እርሱም ኋጥያታችንን ሁሉ ይቅር እንዲልና በእምነት ጸንተን ወደ ፊት መጓዝ እንድንችል ያግዘን ዘንድ መማጸን ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠናቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.