2016-12-03 09:15:00

ቅዱስነታቸው ምዕመናን የእግዚኣብሔርን ፀጋ እየተጋፉ መሆናቸው በሚሰማቸው ወቅት ሁሉ የእርሱን እርዳታ አጥብቀው ሊጠይቁ ይገባል


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በኅዳር 22/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ካህናት ደናግላንና ምዕመናን በተገኙበት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት ምዕመናን የእግዚኣብሔርን ፀጋ እየተጋፉ መሆናቸው በሚሰማቸው ወቅት ሁሉ የእርሱን እርዳታ አጥብቀው ሊጠይቁ ይገባል ማለታቸው ተገለጸ።

በእለቱ በስርዓተ ቅዳሴው መግቢያ ላይ በተደረገው ጸሎት ላይ “ያንተ ፀጋ በኋጥያቴ ምክንያት የሚከሰቱትን እንቅፋቶች ያስወግድ” በሚለው ሐረግ ላይ ተመርኩዘው ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሁላችንም ብንሆን የእግዚኣብሔርን ፀጋ የሚቃወም እንቅፋቶች በልባችን ውስጥ እንደ ሚገኙም ጠቅሰዋል።

ከእነዚህ እንቅፋቶች በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችለው ልክ እንደ ሳኦል “በኢየሱስ ረዳትነት ሕይወቱ ከመቀየሩ በፊት የእግዚኣብሔርን ፍቃድ እያደረገ መስሎ ይፈጽም እንደ ነበረው ጥፋት” ዓይነት ከመልካም እምነት በመነጨ መልኩ የእግዚኣብሔርን ፀጋ መጋፋት  “ግልጽ የሆነ እንቅፋት ነው” ብለዋል።

“ግልጽ የሆነ እንቅፋት ጤናማ ነው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በጣም አደገኛ የሚባሉ እንቅፋቶች የሚባሉት ግን በጣም አደገኛ ናቸው ምክንያቱም በውስጣችን የተደበቁ እና የማይታዩ በመሆናቸው ምክንያት ነው አደገኛ ልላቸው የበቃውት ብለዋል። ሁላችንም ብንሆነ እንደ እያንዳንዳችን ሁኔታ የእግዚኣብሔርን ፀጋ የምንጋፋባቸው የየራሳችን መገዶች አሉ በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እነዚህ እንቅፋቶችን ምን እንደ ሆኑ በማወቅና አንጥረን በማውጣት ጌታ ከእነዚህ ያነጻን ዘንድ ልንጠይቀው ያስፈልጋል በለዋል። ይህም እስጢፋኖስ በጊዜው የነበሩ የእግዚኣብሔርን ክብር እንሻለን የሚል አስተሳሰብ የነበራቸው የህግ ሙሁራንን ይወቅስ እንደ ነበረና ይህም የሕይወት ዋጋ አስከፍሎት እንደ ነበር የገለጹት ቅዱስነታቸው “ሁላችንም ብንሆን የተደበቁ እንቅፋቶች ስላሉን ራሳችንን እንዴት ነው እነዚህን እንቅፋቶች ሊፈጠሩ የቻሉት የሚለውን ጥያቄ መጠየቅ አስፈላጊ ነው ካሉ ቡኋላ፣ ሁልጊዜም ቢሆን ወደ ጌታ ለመቅረብ የምናደርገውን ሙከራ ይገቱታል” ብለዋል።

ነገር ግን አሉ ቅዱስነታቸው እነዚህ ነገሮች በሚፈጠሩበት ወቅት ሁሉ እጃችንን አጣጥፈን በዝምታ ይህ የለውጥ ሂደት እንዲከናወን መፍቀድ ይኖርብናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እስቲ እናስብ በተቋማት ወይም ደግሞ በቤተሰብ ውስጥ ለውጥ ለማምጣት ሲታሰብ ብዙ እንቅፋቶች አሉ እነዚህ እንቅፋቶች  እነዚህ ነገሮች ውስጥ እንዲከሰቱ የተደረገው በሰይጣን አማካኝነት ሲሆን ዓላማውም ይህ ለውጥ እንዳይመጣ እና እግዚኣብሔር ጣልቃ እንዳይገባ ከመሻት የመነጨ ነው” ብለዋል።

ቅዱስነታቸው በመቀጠል 3 ዓይነት እንቅፋቶች እንዳሉ ገልጸው ከእነዚህም የመጀመሪያው በዛሬው ወንጌል እንደ ተጠቀሰው “ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ የሚለኝ ሁሉ ወደ እግዚኣብሔር መንግሥት ከቶም አይገባም”                                                                                    እነደሚለው “ባዶ የሆነ የሽንገላ ቃል” በቀዳሚነት ሊጠቀስ የሚችል እንቅፋት መሆኑን ገለጸው በተጨማሪም በአባታቸው ወደ የወይን እርሻ ቦታ እንዲሄዱ የተላኩ የሁለቱ ልጆች ምሳሌ ላይ እንደ ተጠቀሰው አንደኛው “አልሄድም” ካለ ቡኋላ ነገር ግን ትንሽ ቆይቶ ሄዶ ሥራውን እንዳከናወነ ሌላኛው ደግሞ “እሺ” ሄዳለሁ ብሎ ነገር ግን እንደ ቀረው ዓይነት ነው ብለዋል።

በሁለተኛ ደረጃ ሊጠቀስ የሚችለው እንቅፋት “ራሳችንን ጻድቅ ለማስመሰል የምንጠቀምባቸው ቃላት ናቸው” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም ሰዎች ሁልጊዜ ራሳቸውን ነፃ ለማድረግ የሚጠቀሙባቸው ቃላትን የሚያመልክቱና ሁልጊዜም ለመቃወም ምክንያት የማያጡ ሰዎች ናቸው ብለዋል። በጣም ብዙ የሚባሉ ሰበቦችን ማቅረብ የእግዚኣብሔርን መልካም መዐዛን በማራቅ የሰይጣንን ሽታ እንድናሸት ያደርገናል” ያሉት ቅዱስነታቸው ክርስቲያኖች ራሳችውን ጻድቅ አድርጎ መቁጠር አይጠበቅባቸውም ብለው “መጽደቅም ካለብን መጽደቅ የሚገባን በእግዚኣብሔር ቃል ነው” የእዚህ ዓይነት የቃላት እምቢተኝነት “እግዚኣብሔር የሚያሳየንን መንገድ መከተል ትተን የራሳችንን አቋም ማጽናት” እንደ ሆነ ይቆጠራል ብለዋል።

በመጨረሻ ደረጃ የምናገኘው እንቅፋት “የወቀሳ ቃላት” ናቸው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህም የራሳችንን ሁኔታ ስንመለከት ሌሎችን መውቀስ ያካተተ ነው ብለዋል። በእዚህም ዓይነት ሁኔታም ልክ በፈሪሳዊው እና በቀራጩ መኋከል ተፈጥሮ እንደ ነበረው ምሳሌ ዓይነት ነው ብለዋል።

የእግዚኣብሔርን ፀጋ ላለመቀበል የሚደረገው ግፊያ አንድ አንዴ መልካም ገጽታዎች አሉት ያሉት ቅዱስነታቸው “ምክንያቱም እግዚኣብሔር በእኛ ውስጥ ሥራውን እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ በመሆኑ የተነሳ ነው” ካሉ ቡኋላ እርሱም እንቅፋቶችን በማስወገድ የእርሱን ፀጋ መቀበል እንድንችል ይጋብዘናል ብለዋል።

ጌታ ባለበት ቦታ ሁሉ መስቀል አለ በማለት ሰብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ትንሽም ይሁን ትልቅ መስቀሉን አለመቀበል ማለት ጌታን አለመቀበል ማለት ነው ካሉ ቡኋላ ጌታ ብቻ ነው ደኅንነትን ሊያጎናጽፈን የሚችለው ብለዋል። ስለዚህም እንቅፋቶች በሚያጋጥሙን ወቅቶች ሁሉ መፍራት ሳይሆን የሚጠበቅብን ኋጥያታኞች መሆናችንን አውቀን የእግዚኣብሔርን እርዳታ መጠየቅ ይኖርብናል ካሉ ቡኋላ ስብከታቸውን አጠንቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.