2016-12-02 16:28:00

ቅድስት መንበርና አቢይ የእስራኤል ራባያዊ ጉባኤ


በቅድስት መንበር ከአይሁድ እምነት ጋር የሚደረገው ግኑኝነት የሚከታተለው ድርገትና የእስራኤል የአቢይ የአይሁድ እምነት ራባያዊ ጉባኤ እ.ኤ.አ. ከህዳር 28 ቀን እስከ ህዳር 30 ቀ 2016 ዓ.ም. በአይሁድ እምነት ባሕረ ሓሳብ ደሞም ከ 27 እስከ 29 ማርቸሽቫን 5777 ዓ.ም. የተካሂደው ስብሰባ ጉባኤው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው የጋራ መግለጫ መጠናቀቁ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍልጫ ይጠቁማል።

የእስራኤል የአይሁድ እምነት አቢይ ራባያዊ ጉባኤ በአባልነት ዳኒኤል ስፐርበር፡ አቭራሃም ስታይንበር፡ ሞሰ ዳጋን፡ ኦደድ ዋይነር ያቀፈውን ቡድን የመሩት የጉባኤው ሊቀ መንበር አቢይ መምህር ዳቪድ ሮሶን ሲሆኑ፡ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ፒየርባቲስታ ፒዛባላ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ኣቡነ ብሩኖ ፎርተ፡ ብፁዕ አቡነ ጃቺንቶ ቡሎ ማርኩዞ ብፁዕ አቡነ ፒየር ፍራንቸስኮ ፉማጋሊ የሳሊዚያን ማኅበር ካህን የድርገቱ ዋና ጸሓፊ ኣባ ኖርበርት ሆፍማን በአባልነት ያቀፈውን  የቅድስት መንበር ልኡካንን የመሩት ደግሞ ብፁዕ ካርዲናል ፐተር ኮድዎ አፒያ ቱክሶን መሆናቸው የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ ሁለቱ ሊቀ መናብርት በጋራ በቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ መግለጫ መስጠታቸውንም አስታውቋል።

የተሰጠው የጋራው መግለጫ የጠቀሰው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል፥ ለሁለቱ ሃይማኖቶች ባህሎች አቢይ ተግዳሮት የደቀነው የሰውን ልጅ ነጻነትና ብዙኅነትን በመካድ የሰው ልጅ ቅዱስ ሕይወትን የሚያረክስ በሃይማኖት ስም የሚፈጸመው አመጽና ሃይማኖትን የሚያረክስ እኩይ ተግባሮች መሆናቸው ጉባኤ እውቅና ሰጥቶና እሁንም በተለያየ መልኩ ቀጣይነት የያዘው አሰቃቂ ጸረ ስብአዊ ተግባር እየሆነ በሰዎች ላይ የአቢይ ስቃይ ምክንያት መሆኑ በማመን፥ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ልኡካኑ የሚታየው ዓመጽና መዓት ሁሉ መፍትሔ እንዲያገኝና ሰላም ፍትሕና ተፈጥሮንና ፍጥረትን መንከባከብ በተሰኙት እሴቶች ላይ የጸና የአዲስ ዓለም ስርዓት ግንባታ ዙሪያ ሁሉም የሃይማኖቶች እንዴት ባለ መልኩና ሂደት እስተዋጽኦ ሊያበረክቱ  ይችላሉ በሚለው ቅዉም ሃሳብ ሥር በመመልከት “ሃይማኖቶች የሰው ልጅ ሕይወት ጥበቃና እንክብካቤ የእያንዳንዱ ሰው ክቡር መለያ የሚጠይቅ የሰው ልጅ ሕይወት ያለው መለኮታዊ ቅዱስነትን እውቅና የሚሰጡና ናቸው። ከዚህ አኳያ ለተፈናቃዮና ለስደተኛው የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር፡ የሁሉ ሰው ልጅ ነጻነት በማነቃቃት ማስተናገድ ያስፈልጋል” በሚል ሥርወ ሃሳብ አማካኝነት እንደገለጡት ሲያመለክት።

የአይሁድ እምነት ልኡካን በበኵሉም ማንኛውም ወደ ዓመጽ ጦርነት በተለይ ደግሞ አብርሃማዊ አናስር ያላቸው ሃማኖቶች በጽናት እንዲቃወሙት የሚያመላክታቸው በውስጣቸው ያለው እሴት መመዘኛ ወደ ጥቃት አመጽና ጦርነት የሚቃጡ የተለያዩ ምክንያቶች ሊቃወሙትና እንዲሁም እንደ የመለኮት ህላዌና ፈቃድ ፅብርቅ በሰው ልጅ ዘንድ ያለው ፈቃድና ነጻነት የሚለው ክብሩ ብሎም የብዙኅነት አክብሮት እንዲኖራቸው ግድ ይላቸዋል የሚለው ሃሳብ ተኮር መግለጫ መስጠቱ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ ገልጦ፥ ከዚሁ ጋር በማያያዝም በዚህ ባለንበት ዘመን በሰው ልጅ ላይ የተደቀኑት ተጋርጦዎች ፊት በቃልና በሕይወት የተቀባብሎና ተከባብሮ የመኖር  ተግባር በተለይም ካንተ የተለየውን ለመብትና ክብር ረገጣ በቀላሉ ሊጋለጥ የሚችለውን እራሳቸው ለመከላከ ብቃቱም ሆኑ አቅሙም የሌላቸውን ሁሉ ድጋፍና ጥበቃ ሙሉ ተቀባይነት እንዲኖራቸው አብነት በመስጠት የሚመሩ የሃይማኖት መሪዎች አስፈጊ መሆናቸውንም በምስልምና ሃይማኖት ተከታይ አገሮች የሰው ልጅ ሰብአዊ መብትና ክብር እንዲሁም ብዙኅነት ማክበር ያለው አስፈላጊነት ያበከረው በማራከሽ የተካሄደው ጉባኤ ያወጣው ሰንድ ያማከለው ሃሳብ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ በጋራው ሰነድ ተሰምሮበታል ሲል ይጠቁማል።

ከአንድ ዘመን በላይ ያስቆጠረው በካቶሊካና አይሁድ መካከል የጸናው እርቅና በጋራ በሚካሂዱት ውይይቶችና ግኑኝነቶች ሁሉ በአይሁድ ሃይማኖትና በክርስትና እምነት ተከታዮች መካከል መልካም ግኑኝነት እንዲኖር ከማድረጉም አልፎ ይኸው እነዚህ የሁለቱ ሃይማኖቶች ምእመናን ለመላው የሰው ልጅ ቤተሰብ ሰላም ለመፍጠር እንዲተጉ መጠራታቸው ለሰላም ግንባታ ንቁ ተሳታፊያን እንዲሆኑ እያደረገ ነው። ስለዚህ ይኸንን ሃሳብ ያካተተው የጋራው መግለጫ አዲሱ ትውልድ ለሰላምና ለእርስ በእርስ የመከባበሩ ተግባር እንዲያነቃቃ የሚያበቃው ተገቢ ሕንጸት እንዲያገኝ አስፈላጊ ነው የሚል ሃሳብ ያካተተ መሆኑም የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታውቋል።

በዚህ በተካሄደው የጋራው ውይይት ወቅታዊነት ያላቸው አንገብጋቢ ማሕበራዊ ሰብአዊ ወዘተርፈ ነክ ጉዳዮች ዙሪያ በመምከር ኵላዊ መከባር የተሰኘውን መርሆ መሠረት የሁሉም ሃይማኖቶች የስግደትና የአምልኮ ስፍራ  እንዲሁም የአይሁድ እምነት ተከታዮች ያላቸው ታሪካውያን ቅዱሳን ሥፍራዎች ማክበር የተሰኘው ነጥብ የተካሄደው ስብሰባ እንዳሰመረበት የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ በማያያዝ በቅርቡ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት ስነ ምርምርና የባህል ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር ያጸደቀው ውሳኔ ዙሪያ ውይይት ከተካሄደበ በኋላ ውሳኔው ፖለቲካዊ ክህደትና የመጽሓፍ ቅዱስ ታሪክ የሚቃረን ነው በማለት ሁሉም አገሮችና ሃይማኖቶች የምስራቅ ኢየሩሳሌም ክልል ታሪካዊና ሃይማኖታዊ ቁርኝቱን እንዲያከብሩ ከሁለቱ የተጋባእያን ወገን ጥሪ መተላለፉንም ያስታውቃል።








All the contents on this site are copyrighted ©.