2016-11-30 16:22:00

ቅዱስ አባታችን አመሪካዊው የፊልም ቀራጭና ደራሲ ማርቲን ስኮርሰዘን ተቀብለው አነጋገሩ


የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ዜጋ ማርቲን ስኮርሰዘ “Silence-ዝምታ” በሚል ርእስ ሥር የኢየሱሳውያን ልኡካነ ወንጌል ስደትና መከራ በጠቅላላ በ 1600 ዓመታት በጃፓን የከፈሉትን የደም ሰማዕትነት ታሪክ የሚያወሳ ፊልም ቀራጺና ደራሲ የፊልሙ ቀዳሜ ትርኢት በአገረ ቫቲካን ለማቅረብ የነበራቸው ፍላጎት አወንታዊ ምላሽ በማግኘቱ ምክንያት ይኸው እ.ኤ.አ. ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. የፊልሙ ቀዳሜ ትርኢት በአገረ ቫቲካን ለማቅረብ ሮማ የገቡ ሲሆን። እኚህ ታዋቂና ዝነኛ የፊልም ቀራጭና ደራሲ ስኮርዘሰ እ.ኤ.አ. ህዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን ሐዋርያዊ መንበር በሚገኘው በሰዲያሪ መለስተኛ አዳራሽ  ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋራ እንደተገናኙ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አስታውቋል።

ስኮርሰዘ ይኽ ፊልም እ.ኤ.አ. በ 1966 ዓ.,ም. ጃፓናዊ ደራሲ ሹሳኩ ኤንዶ ክውን በልበ ወለድ መልክ በደረሱት በጃፓን የኢየሱሳውያን የደም ሰማዕትነት ታሪክ ላይ ተንተርሰው የደርሱት ሲሆን፥ እ.ኤ.አ. በ1549 ዓ.ም. የኢየሱሳውያን ማኅበር መሥራች ቅዱስ ኢግናዚዮስ ዘሎዮላ ቀዳሜ ተከታይ ጋደኛ የሆነው ቅዱስ ፍራንቸስኮ ሳቨሪዮ የክርስትናን እምነት ወደ እሩቅ ምስራቅ ክልል በማድረስ ሆኖም የክርስትና እምነት ላይ በተቀበሉትና በልኡካን ወንጌል ጭምር በወቅቱ በጃፓን በነበረው ወታደራዊ አምባ ገነን መንግሥት ለሞና ለስቃይ መዳረጋቸውን የሚያወሳ ፊልም በእውነቱ በእኚሕ ኢየሱሳዊ ካህን እያሉ ወደ እርቁ ምስራቅ ወንጌላዊ ልኡክ ለመሆን ጥልቅ ጉጉት የነበራቸው  በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮና በፊልሙ ቀራጭ መካከል ስለ የእምነት ሰማዕትነት ጉዳይ ለየት ባለ መልኩም በጃፓን የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት የከፈሉት የደም ሰማዕትነት ዙሪያ እንደተወያዩ የገለጠው የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል መግለጫ አክሎ፥ ይኽ ፊልም በተባበሩት የአመሪካ መግሥታት እ.ኤ.አ. ከታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. በኢጣሊያ ደግሞ እ.ኤ.አ. ከጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ለትርኢት እንደሚቀርብ ጠቅሶ በአገረ ቫቲካን ሮማ የሚገኙት የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት አበይት የቅድስት መንበርና የሮማዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስነታቸው የቅርብ ተባባሪዎች አበይት አካላት ብፁዓን ካርዲናሎችና ጳጳሳት በተገኙበት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓም. ለቀዳሜ ትርኢት እንደሚቀርብ አስታውቋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.