2016-11-29 12:40:00

ቅዱስነታቸው ኢየሱስን ለመገናኘት ከፈለግን ወደ እርሱ መጓዝ ይጠበቅብናል ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትንው እለት ማለትም በኅዳር 19/2009 ዓ.ም. በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት የክርስቲያን እምነት እንደ አንድ ምናባዊ ሐሳብ ወይም ፊሎዞፊ ሳይሆን ከኢየሱስ ጋር መገናኘትን የሚጠይቅ ነው ካሉ ቡኋላ ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ ልንከተላቸው የሚገባን ሦስት ነገሮች እንዳሉ ጠቁመው እነዚህም በጸሎት ነቅቶ መጠበቅ፣ መመጽወትን ልምዳችን ማድረግ እና በምስጋና ሐሴት ማድረግ የሚሉትን በቀጣይነት በሕይወታችን መተግበር እንደ ሚገባን ገልጸዋል።

“አሁን ባለንበት የገና ወቅት የምንመኘው ፀጋ” ኢየሱስን የመገናኘት ፀጋ ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በእለቱ ያሰሙት ስብከት ኢየሱስን መገናኘት በሚል ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጠነ እንደ ነበረም ታውቁኋል።  በእዚህ በያዝነው ዓመት ስራዓት ሊጡርጊያችን የሚያሳየን (የአውሮፓዊያን የስርዓት ሉጥርጊያ) ከኢየሱስ ጋር መገናኘት አስፈላጊ መሆኑን ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው በተለይም ደግሞ በእናቱ ማህጸን ውስጥ፣ ከመጥምቁ ዩሐንስ፣ ከእረኞች እና ከሰባሰግል ጋር ሆኖ ሊገናኘን እንደ ሚመጣ ያሳየናል ብለዋል። ይህ ሁሉ የሚያሳየን የስብከተ ገና ሳምንታት “ወደ ፊት በመራመድ ኢየሱስን ለመገናኘት የምንጓዝበት ወቅት እንጂ ተገትረን የምንቆምበት ወቅት አለመሆኑን ነው” ብለዋል።  

እንዴት ብንራመድ ነው ኢየሱስን መገናኘት የምንችለው? የሚለውን ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ምን ዓይነት ባሕሪዎቻችን ናቸው ኢየሱስን እንድንገናኝ የሚረዱን?” በማለት ጥያቀን አንስተው “እንዴትስ ነው? ኢየሱስን ለመገናኘት ልቤን ማዘጋጀት የሚችለው? የሚለውንም መጠየቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

በዛሬ መስዋዕተ ቅዳሴያችን መግቢያ ላይ የተደረገው ጸሎት ሦስት ባሕሪያት እንዲኖሩን ያሳስበናል፣ በጸሎት መትጋት፣ በትጋት መለገስና በምስጋና ሐሴት ማድረግ የሚሉት ናቸው። ስለዚህም ነቅቼ መጸለይ አለብኝ። በመለገስም መትጋት ይኖርብኛል፣ ምጽዋትን መመጽወት ብቻ ሳይሆን የሚጠበቅብን የሚያበሳጩንን ሰዎች በትዕግስት መመልከት፣ በቤቴም ውስጥ ቢሆን ልጆቼ በሚበጠብጡ ወቅት ሁሉ መታገስ ወይም ደግሞ ባልና ሚስት በችግር ውስጥ በሚገቡበት ወቅት መታገስ  በአጠቃላይ ለሁሉም ትዕግስትን በማሳየት የወንድማማችነት ልገሳንም ማጠናከር ያስፈልጋል ልገሳ ሁሌም ቢሆን አስቸጋሪ ነገር መሆኑን ማወቅ መልካም ነው። እንዲሁም ጌታን በማመስገን በሚገኘው ደስታ ሐሴትን ማድረግ። የህንን ጉዞዋችንን ኢየሱስን ለመገናኘት መጓዝ የሚጠበቅብን በእዚህ መልኩ ነው። ከእርሱ ጋር ተገቢ በሆነ መልኩ ለመገናኘት መጓዝ ያስፈልጋል። ተገትሮ መቆም አያስፈልግም። ጌታን መገናኘት ያስፈልጋል።

ነገር ግን አሉ ቅዱስነታቸው ስብከታቸው በቀጠሉበት ወቅት “እርሱ አስገራሚ ጌታ በመሆኑ የተነሳያ ልጠበቅነው ነገር ሊከሰት ይችላል” ብለው ጌታ ራሱ “በአንድ ቦታ ተገትሮ የቆመ አይደለም”። እርሱን ለመገናኘት ወደ እርሱ በምጓዝበት ወቅት ሁሉ እርሱም እኔን ለመገናኘት ወደ እኔ ይጓዛል፣ ከእርሱ ጋር በምንገናኝበት ወቅት እርሱ እኔን ለመገናኘት እኔም ደግሞ እርሱን ለመገናኘት የነበረን ጉጉት በመሳከቱ በተለይም ደግሞ ከእኔ ቀድሞ እርሱ እኔን ለመገናኘት የመኝ ስለነበረ ግንኙነቱ አስደናቂ ይሆናል ብለዋል።

ቅዱስነታቸው ስብከታቸውን በቀጠሉበት ወቅት እንደ ገለጹት “ይህ ከኢየሱስ ጋር የሚደርገው አስደናቂ ግንኙነት የተፈጠረው በቅዲሚያ እርሱ ስለፈለገ ነው። እርሱ ሁሌም ቀዳሚ ነው። እኛን ለመፈለግ ሁልጊዜም ይጓዛል”። የመቶ አለቃው ማሳሌ የሚያሳየን ይህንኑ ነው ብለዋል።

ጌታ ሁል ጊዜ ከእኛ በላይ አስቀድሞ ይሄዳል። አኛ አንድ እርምጃ በምንጓዝበት ወቅት ሁል ጊዜም እርሱ አሥር እርምጃ ይራመዳል። የተትረፈረው ፀጋው፣ ፍቅሩ፣ እኛን ከመፈለግ ፈጽሞ የማይደክመው የእርሱ ርኅራኄ፣ እንዲያውም አንዳንድ ጊዜ ለምጻም እንደ ነበረው እንደ ሶሪያዊው ንዕማን በጥቃቅን ነገሮች ጌታን መገናኘት በጣም ትልቅ ነገር እንደሆነ አድርገን እንስባለን። ነገር ግን ቀላል አይደለም። እርሱም ራሱ እግዚኣብሔር የፈጸመውን አስደንቂ ነገር በተመለከተ ጊዜ በጣም ተገርሞ ነበር። ስለዚህም እኛን የሚፈልገን፣ የሚጠባበቀን እንዲሁም እኛን የሚጠይቀን ትንሽ የሚባል መልካማነትን ብቻ ነው፣ ስለዚህም የእኛ እግዚኣብሔር የሚስገርም አምላክ ነው።

እርሱን ለመገናኘት ፍላጎት ማሳየት ይገባናል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከእዚያም እርሱ ራሱ ይረዳናል በቃሉ እንደ ተናገረው “ምንም እንኳን ብዙን ጊዜ ከእርሱ ርቀን የምንገኝ ቢመስልም፣ እርሱ ግን በሕይወታችን ሁሉ ከእኛ ጋር ይሆናል፣ ጠፍቶ እንደ ተገኘው ልጅ አባት ሁልጊዜም ይጠባበቀናል” ብለዋል።

“ብዙውን ጊዜ” አሉ ቅዱስነታቸው “እርሱን ለመቅረብ መፈለጋችንን ይመለከታል፣ ገና በመንገድ ላይ ሳለንም እኛን ለመገናኘት ይወጣል” በማለት ስብከታቸውን የቅጠሉት ቅዱስነታቸው ከጌታ ጋር መገናኘት በጣም አስፈላጊ ጉዳይ ነው” ካሉ ቡኋላ “እምነት አንደ አንድ ጽንሰሐሳብ ወይም ደግሞ ፊሎዞፊ ወይም ሐሳብ አይደልም፣ ነገር ግን ከጌታ ጋር መገናኘት ነው” የሚለው የበኔዴክቶስ 16ኛ አባባል ሁሌም ልቤን ይነካኛል ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከኢየሱስ ጋር መገናኘት “አንድ ሰው በእርሱ ምሕረት ካልተዳሰሰ” በፍጹም ሊተገበረ የማይችል ነገር ነው ካሉ ቡኋላ ያለምንም እምነት ጸሎተ ሐይማኖትን በቃል እንደ መድገም ይቆጠራል ብለዋል።

የሕግ ጻህፍት በጊዜው የነበረውን ህጎች፣ የማይለወጡ የእምነት አስተምህሮዎችን፣ የስነ-ምግባር ደንቦችን፣ በአጠቃላይ ሁሉንም ጠንቅቀው ያውቃሉ። እምነት ግን አልንበራቸውም ምክንያቱም ልባቸው ከእግዚኣብሔር ርቆ ስለነበረ ነው። ከእርሱ መራቅ ወይም እርሱን ለመገናኘት ፍላጎት ማሳየት። የእዚህን ዓይነቱን ፀጋ ነው ዛሬ የንጠይቀው፣ “እግዚኣብሔር አባታችን ሆይ በመልካም ሥራ የታጀበ ክርስቶስን ለመገናኘት የሚያስችለንን ፍላጎት በልባችን ያኑር፣ በጸሎት ተግተን እንድንገኘ፣ በልገሳም እንድንበረታ በሐሴት ተሞልተን እንድናመሰግንህም ትረዳን ዘንድ ለእዚህም ጸጋህን እንማጸናለን።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.