2016-11-23 12:11:00

ቅዱስነታቸው ለጌታ ታማኝ ከሆንን ሞት በፍጹም አያስፈራንም ማለታቸው ተገለጸ።


ቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በትላንትናው እለት ማለትም በኅዳር 13/2009 በቅድስት ማርታ የጸሎት ቤት ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ወቅት ባሰሙት ስብከት በጌታ የምናምን ሰዎች ከሆንን ሞትን መፍራት የለብንም  ካሉ ቡኋላ ነገር ግን በፍጹም እንደ ማንሞት በመቁጠርና ሕይወታችን ተሸጋጋሪ እንዳልሆንቸ በሚያስተምር ጥራዝ ነጠቅ አስተምህሮ ላይ ከመመርኮዝ መጠንቀቅ ይግባናል ማለታቸው ተገለጽ።

በእለቱ ከዩሐንስ ራእይ በተወሰደው ምንባብ ላይ ተመርኩዘው ቅዱስነታቸው ያደረጉት ስብከት ትኩረቱን አድርጎ የነበረው ሁላችንም በመጨረሻ የፍርድ ቀን ከኢየሱስ ጋር ፊት ለፊት እንደ ምንገናኝ በሚያወሳው ጭብጥ ሐሳብ ላይ ተመርኩዞ የነበረ ሲሆን በስብከታቸውም ስለ መጨረሻ ቀን ሕይወታችን እንድናስብ ጌታ ይጠራናል ካሉ ቡኋላ ምክንያትም ሁላችንም ሙዋቾች በመሆናችን የተነሳ ነው ብለዋል።

ብዙን ጊዜ ስለነዚህ ነገሮች ማንሳት አንፈልግም በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ምክንያቱም ሁላችንንም የሚያጋጥመን እውነታ በመሆኑ ምክንያት ነው ካሉ ቡኋላ ብዙን ጊዜ ሙታንን በምናስታውስበት ወቅት  ሁሉ ጥለውት ያለፉትን መልካም ነገሮች እናስባለን የእዚህ ዓየነቱ መልካም ነገር ነው በመጨረሻ የፍርድ ቀናችን ነጻ ልያወጣ የሚችለው ብለዋል።

“በኢየሱስ ፊት ለፍርድ የምቀርብበት ቀን ምን ይመስላል? የሚለውን በሚገባ ካሁኑ ማሰብ ያስፈልጋል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “ስጥቶን ስለነበረው መክሊት ቢጠይቀኝ እና እንዴት እንደ ተጠቀምኩት ቢጠይቀኝ፣ እርሱ የዘርው ዘር በልቤ በወደቀ ጊዜ ልቤ ምን ይመስል ነበር ብሎ ቢጠይቀኝ መንገድ ላይ እንደ ወደቀው ዘር ነው ውይስ እሾህ ሥር እንደ ወደቀው ዘር ነው ብለኝ፣ ስለ እግዚኣብሔር መንግሥት ቢጠይቀኝ፣ የእርሱን ቃል እንዴት ነው የተቀበልኩኝ? በተከፈተ ልብ ነው? ለሁሉም መልካምነት እንድያብብ አድርግያለሁ?” የሚሉትን ጥያቄዋች ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ወቅት አንስተዋል።

ሁላችም ብንሆን አንድ ቀን በኢየሱስ የፍርድ ወንበር ፊት መቆማችን አይቀሬ መሆኑን በማሳሰብ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ለሐሳባቸው ማጠናከሪያ ይሆን ዘንድም ክርስቲያኖች መታለል የለባቸውም የሚለውን የወንግል ቃል ጠቅሰው ባይተዋርና ልዩ በሆኑ ሐሳቦች ላይ ተመስርተን የእኛ ሕይወት ተሸጋጋሪ አይደለችም  በሚል ጥራዝ ነጠቅ አስተሳሰብ በማትኮር እንደ ማንሞት በመቁጠር መኖር እንደሌለብንና ከእነዚህ አታላይ ከሆኑ ሐሳቦች መቆጠብ አለብን ብለዋል። “ጌታ በሚመጣበት ወቅት” አሉ ቅዱስነታቸው በማከልም “እንዴት ነው የሚያገኘን? በብዙኋን መኋል ሆነን ነው የሚያገኘን ወይስ በብቸኝነት ሕይወት ውስጥ ነው? የሚሉትን ጥያቄዎች ለታዳሚዎች ሰንዝረዋል።

“አስታውሳለሁ ልጆች እያለን በትምህርተ ክርስቶስ አራታ ነገሮችን ተምረናል እነዚህም ፣ ሞት፣ ፍርድ፣ ገሃነብ ወይም ገነት” የሚሉት መሆናቸውን በመጥቀስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ከፍርድ ቡኋላ የሚከተለው እድል ሊገጥመን ይችላል “ነገር ግን አባት ሆይ ይህ አስፈሪ ነገር አይደለም? ‘አይደለም ምክንያቱም ይህ እውነት የሆነ ነገር ነው ምክንያቱም ልብህን ካልተንከባከብከው በስተቀር ይገጥምሃል ነገር ግን እግዚኣብሔር ከአንተ ጋር ነው፣ በአንጻሩ ከእግዚኣብሔር ተለይተህ ከኖርክ ግን ችግር ልያጋጥምህ ይችላል። በእዚህ ዓይነት የብቸኝነት መንግድ በመሄድ ከጌታ በቀጣይነት የራቀ ሕይወት አደጋ አለው” ይህም አሰቃቂ ጉዳይ ነው” ብለዋል ቅዱስነታቸው።

ቅዱስነታቸው በስብከታቸው ማጠቃለያ ላይ ለታዳሚዎች እንደ ገለጹት ስለመጨረሻ የፍርድ ቀን እንዲያስቡና እንዴት እንደ ሚጋፈጡት እንጂ እንዴት እንደ ሚፈሩት ማሰብ እንደ ሌሌባቸው አሳስበው ምክንያቱም በእለቱ ከተነበበው ምንባብ በድጋሚ በመጥቀስ “ጌታ እስከ ሕይወታችሁ ፍጻሜ ድረስ በታማኝነት ኑሩ እኔም ደግሞ የሕይወትን አክሊል እሰጣችኋለሁ” ያለውን አጽናኝ ቃል ማሰብ ይገባል ብለዋል።

“ለጌታ ታማኝ ሆኑ መኖር አያሳፍረንም። እያንዳንዳችን ለጌታ ታማኝ በምንሆንበት ወቅት ሁሉ ሞት በሚመጣበት ወቅት ልክ እንደ የአዚዚው ቅዱስ ፍራንቸስኮ ‘እህቴ ሞት ሆይ ነይ. . .’ ማለት እንጂ መፍራት የለብንም” በመላት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው የፍርድ ቀን በሚመጣበት ወቅት ጌታን እየተመለከትነው ‘ጌታ ሆይ ብዙ ኋጥያቶች ሰርቻለሁ ነገር ግን ታምኝ ለመሆን ማክሬም ነበር” ብንለው ጌታችን መልካም በመሆኑ ይህንን ምክር እለግሳችኋለሁ . . .‘እስከ ሕይወታችሁ ፍጻሜ ድረስ ታማኝ ሁኑ እኔም የሕይወትን አክሊል አጎናጽፋችኋለው- ይላል ጌታ” ካሉ ቡኋላ “በእዚህ አይናት ታማኝነት በምንጓዝበት ወቅት ሁሉ ማትን አንፈራም፣ ስንሞትም የመጨረሻው ፍርድ አያስፈራንም” በማለት ስብከታቸውን አጠንቀዋል።

 








All the contents on this site are copyrighted ©.