2016-11-21 14:44:00

ቅዱስነታቸው "እግዚኣብሔር ሁል ጊዜ በምሕረቱ ይቀበለናል" ማለታችው ተገለጸ።


በኅዳር 29/2008 ዓ.ም. በመካከለኛው አፍሪካ በባንጉዊ ከተማ በይፋ የተከፈተው ቅዱስ ልዩ የምሕረት ዓመት በትላንትነው እለት ማለትም በኅዳር 11/2009 ዓ.ም. የክርስቶስ ንጉሥ በዓል በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በተከበረበት እለት ከሰባ ሺ በላይ ምዕመናን በተገኙበት በቅዱስ አባታችን ፍራንቸስኮ በይፋ መዘጋቱ ታወቀ። ቅዱስነታቸው በእለቱ ባደረጉት ስብከት እንደ ገለጹት ምዕመናን በምንም ዓይነት መልኩ ፊታቸውን ከእውነተኛው ንጉሥ ከሆነው ከኢየሱስ ፊት እንዳያዞሩና ሁሉን የምታስተናግድ፣ ነጻ፣ ሚሲዮናዊና ድኽ ነገር ግን በፍቅር የበለጸገች ቤተ ክርስቲያን ለመገንባት መጣር እንድሚኖርባቸው አሳስበዋል።

“ለተቀበልናቸው የፀጋ ስጦታዎች እውቅናን በመስጠትና ይህንንም በብርታት በቃል እና በተግባር ለመመስከር፣ የእርሱን መሐሪ ፍቅር በማሰብ ይህንን ቅዱስ በር እንዘጋለን” በማለት ስብከታቸውን የጀመሩት ቅዱስነታቸው “አንጪ የሆነው መንፈስ ቅዱስ በአዳኛችን በኢየሱስ ላይ ያለንን ተስፋ እንዲያድስ፣ በየዋህ ልብ ለሚፈልጉት ሁሉ የእርሱ የመሕረት በር ሁል ጊዜ ክፍት እንደ ሆነ፣ ወደ መንግሥቱ የሚመራን ብቸኛው በር እርሱ ብቻ መሆኑን እንድንረዳ ያግዘን ዘንድ መጠየቅ ያስፈልጋል” ብለዋል።

በእለቱ በተከበረው የክርስቶስ ንጉሥ በዓል ላይ ተኩረቱን ባደርገው ስብከታቸው “ያለውን ዓይልና ክብር ተጠቅሞ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት አሽናፊ መምሰል ሲገባው ተሸናፊ ይመስል ነበር” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “መስቀል የእርሱ ዙፋን ሆነ፣ አክሊሉ እሾህ ነው፣ ይዞት የነበረው ውድ የሆነ ብትር ሳይሆን የሸንበቆ ብትር ነበር፣ ውድ የሆነ ካባ ሳይሆን የነበረው ነገር ግን እጀ ጠባብ ነበር ልብሱ፣ በእጁ ያጠለቀው የሚያብረቀርቅ የወርቅ ቀለበት ሳይሆን በስቃይ የተበሳ እጅ ነበር፣ ምንም ዓይነት ውድ የሆነ ንብረት ስላልነበረው በሰላሣ ብር ተሸጠ የሚሉትን በምንመለከትበት ወቅት የእርሱ ንግሥና እርስ በእሩስ የሚጋጭ ይመስላል” ብለዋል።

ክርስቶስ ራሱን ዝቅ በማድረግ የሰው ልጆችን  መከራን ተላብሶ ኑሮ ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ አድማሱን በማስፋት ሕይወት ያላቸውን ሁሉ ለማቀፍና ለማዳን መምጣቱን አስታውሰዋል።

“በምንም ዓይነት ሁኔታ አላወገዘንም፣ በእኛ ላይ አሸናፊ ሆኖ ለመታየትም አልፈለገም፣ ነፃነታችንን በፍጹም አልተጋፋም፣ ነገር ግን የዋህ በሆነ ፍቅር ሁሉንም ይቅር የሚል፣ ተስፋ የሚያደርግ፣ ሁሉንም የሚደግፍ መንገድን አበጀ” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነትቻው “ይህ ፍቅር ብቻ ነው ተቃዋሚዎቻችን የሆኑትን ኋጥያት፣ ሞትና ፍርሃትን ያሸነፈውና አሸንፊ ሆኖ የሚቀጥለው” ብለዋል።

በታላቅ ደስታ ኢየሱስ የፍቅር ንጉሥ መሆኑን ልንገነዘብ ያስፈልጋል በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ኢየሱስን የሕይወታችን መዐከል ሳናደርገው እርሱን እንደ ዓለም ንጉሥ መቁጠርና  የታሪክ ሁሉ መዐከል አድርገን መውሰድ አዳጋች ነው ብለው የእርሱን የአነጋገሥ ዘይቤን ልንቀበል ያስፈልጋል ካሉ ቡኋላ በእለቱ በተነበበው ወንጌል ላይ ቅዱስነታቸው ተመርኩዘው ኢየሱስ በመስቀል ላይ በነበረበት ወቅት የነበሩትን ሶስት ዓይነት ታዳሚዎች ማለትም ሁኔታውን በእሩቅ ሆነው ይከታተሉ የነበሩ ሰዎች፣ በመስቀሉ አጠገብ የነበሩ ሰዎችና ከጎኑ የተሰቀለው ወንበዴ መሆናቸውን አብራርተዋል።

በፊለፊቱ በሩቁ ቆመው የነበሩ ሰዎች መስቀሉን ይመለከቱ ነበር፣ ምንም ዓይነት ቃል አልተናገሩም ነበር፣ ወደ መስቀሉም ለመጠጋት አልደፈሩም ነበር በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “በሕይወታችን በሚገጥሙን ሁኔታዎች ወይም ደግሞ ፍላጎቶቻችን ስይሟሉ በሚቀሩበት ወቅት ሁሉ እኛም ንጉሥ የሆነው የኢየሱስ የሚያሳየንን ትሁት ፍቅር ላለመላበስ በመፈለግና የእኛ ራሳችንን ምቾት ብቻ በመሻት ራሳችንን ከእርሱ ለማራቅ እንሞክራለን” ብለዋል።

በመስቀሉ አጠገብ የነበሩ ሰዎች ደግሞ የሕዝቡ መሪዎች እና አለቆች፣ ወታደሮች እና ከሁለቱ ወንበዴዎች አንዱ እንደ ነበሩ በማስታወስ  ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ሁሉም በኢየሱስ ላይ ይሳለቁበትና “ራስህን አድን” በማለት ይናጋሩት እንደ ነበረ ጠቅሰው ከመስቀል ላይ ወርዶ ኋያልነቱንና የበላይነቱን ማሳየት ከባድ ሊባል የሚችል ፈተና እንደ ነበረ ጠቅሰው በእዚህ ረገድ ኢየሱስ ምንም ዓይነት የቃል ምላሽ ስይሰጥ ለእነርሱ ያለውን ፍቅር ማሳየት ቀጥሎ እንደ ነበረ ገልጸዋል።

“የእግዚኣብሔር መንግሥት እንዴት እንደ ሚተገበር በፍጥነት በመርሳት ለስልጣን ያለንን ጉጉትና ስኬት ወንጌልን ለማሰራጨት ፈጣን እና ቀላል ዘዴ መስሎ ይታየናል” በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው ይህ ቅዱስ የምሕረት ዓመት በሕይወታችን አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንድናውቅና የሕይወታችን መዐከል አድርገን እንድንወስድ ረድቶናል ብለው ይህ የምሕረት ወቅት እውነተኛውን የንጉሣችንን ፊት እንድንመለከት በመርዳት በፋሲካ የበራውን ወጣትና ቆንጆ የሆነውን እንዲሁም ሁሉን አቀፍ፣ ነጻ፣ ታማኝ፣ የቁሳቁስ ድኽ የሆንች ነገር ግን በፍቅር የበለጸገችና ሚስዮናዊ የሆንችውን  የቤተ ክርስቲያን ፊት እንድንመለከት ረድቶናል ብለዋል።

በመጨረሻም ከኢየሱስ ጎን ተሰቅሎ የነበረው ወንበዴ ሰው ኢየሱስን “ዛሬ በመንግሥትህ አስታውሰኝ” ያለውን በማስታወስ ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “እርሱ በኢየሱስ ማመኑን በመግለጹ “ዛሬ በምንግሥቴ ከእኔ ጋር ትሆናልህ” የሚለውን የኢየሱስን ማረጋገጫ ማግኘቱን ገልጸው “ለእግዚኣብሔር ቦታ በምንሰጥበት ወቅት ሁሉ፣ እርሱ እኛን እንደ ሚያስታውሰን” ግልጸው “እርሱ ኋጥያታችንን መሉ በሙልና ለዘላለም ይደመስሳል ምክንያቱም እርሱ እኛ እንደ ምናደርገው  ክፉ ነገሮቻችንን ብቻ በማስታወስ ላይ የተጠመደ ባለ መሆኑና አምላክ ሁል ጊዜም ኋጥያታችንን ሳይሆን የሚያስታውሰው ነገር ግን ተወዳጅ የሆኑ ልጆቹን ነው የሚያስታውስው ካሉ ቡኋላ ማመን ሁሉንም ነገር በአዲስ ሁኔታ እንድንጀምርና እውን እንድናደርግ ይረዳናል ብለዋል።

“እግዚኣብሔር በእኛ እንደ ሚተማመን እኛም ደግሞ የተጠራነው ተስፋን ለማጠናከርና ለሌሎች እድል ለመስጠትና የምሕረት መሳሪያዎችም ለመሆን ነው በማለት ስብከታቸውን የቀጠሉት ቅዱስነታቸው “የእርቅን በር መቼም ቢሆን ዝግ እንዳናደርግ ፀጋውን ይሰጠን ዘንድ መጠየቅ ይኖርብናል” ብለው “ይቅርታን በማድረግ ከክፋት ባሻገር በመጓዝ ልዩነቶች ሳያግዱን ማንኛውንም ዓይነት ምቹ የተስፋ መንገድ መጓዝ ይጠበቅብናል ፣ ይህንንም መንገድ በምንጓዝበት ወቅት ሁሉ እመቤታችን ማሪያ አብራን ትጓዝ ዘንድ መማጸን ያስፈልጋል” በማለት ስብከታቸውን አጠንቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.