2016-11-21 16:25:00

ልዩ ቅዱስ የምሕረት ዓመት ቢጠናቀቅም ምሕረት የቤተ ክርስቲያን ማእከላዊ አገልግሎት መሆኑ መቼም አያቋርጥም


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ያወጁት እ.ኤ.አ. ታህሳስ 8 ቀን 2015 ዓ.ም. በላቲን ሥርዓት በተከበረው በንጽሕት ድንግል ማርያም ዓመታዊ በዓል በይፋ ያስጀመሩት ልዩ የምሕረት ዓመት በላቲን ሥርዓት ዓመታዊ በዓለ ክርስቶስ ዘንጉሥ ሕዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም. የተጠናቀቀ ሲሆን፥ ቅዱስነታቸው ስለ መንፈሳዊ መለወጥ ጥሪ በማቅረብ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ ምንነት እርሱም የእግዚአብሔር ምሕረት አብሳሪ መሆን ነው፡ ቤተ ክርስቲያን ይኸንን የእግዚአብሔር ምሕረት አብሳሪነቷ በምሕረት ዓመት የሚዘጋ ሳይሆን የእግዚአብሔር ምሕረት አያልቅምና ዕለት በዕለት ይኽንን የማያልቀው ምሕረቱን የምታበስር መሆኗ ያስገነዘቡበት ዓመት እንደነበር የታሪክ ሊቅ አጎስቲኖ ጆቫኞሊ የምሕረት ዓመት ፍጻሜ በማስመልከት ከቫቲካ ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በጥልቀት አብራርተው፡ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት የቲዮሎጊያ ሊቃውንት ምሕረት ላይ እንዲያተኩሩ ከማድረጉም አልፎ በእውነቱ ያንን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ያስጀመሩት የሕዳሴ መርሓ ግብር ምን ተመስሎው የሚገልጥ ነው፡ ከዚህ በመንደርደርም የእሳቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት ሐዋርያዊ ስልጣን ትኩረቱ ምን መሆኑ ለመረዳቱ አያዳግትም ብሏል።

ቅዱስ አባታችን የወንጌል ሓሴት በተሰየመው ዓዋዲ መልእክታቸው አማካኝነት ለድኾች ልዩ ትኩረት መስጠት ያለው አስፈላጊነ በመተንተን እግዚአብሔር የሚያዳላ አምላክ አይደለም ነገር ግን ለድኾች ያለው በይልቅ አብልጦ የመውደዱ ባህርይ አለው በማለት ለይተው የሚያብራሩት ጥልቅ ሐዋርያዊ ሃሳብ ብዙ ሙግዶት እያጋጠመው መሆኑ ለማንም የተሰወረ አይደለም። ስለዚህ ከዚህ አንጻር በእውነቱ ነቢይ ናቸው ለማለቱ አያዳግትም። የሚሉት የሚናገሩት ወንጌላዊና በጥልቅ የቤተ ክርስቲያን ጠመቅ ትምህርትና ሥልጣናዊ ትምህርቱ የሚያብራራ ነው። ይኸንን የቤተ ክርስቲያን ትምህርት እንዲህ ባለ መልኩ ሲገልጡት ደስ የማይሰኙ ሊኖሩ ይችላሉ፡ የሰዎች ደስ መሰኘትና አለ መሰኘት በመንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው የጌታ መልእክት አይመዘንም። ንግግሩም እውነት እውነት እላችኋለሁ የሚለ ነቢይዊ ነውና፡ ክርስቶስ ድኽነት ለብሶ ድኻው ሥጋችን ለብሶ ነው የመጣው ስለዚህ ከድኻው ጋር መገናኘት የእምነት ተመክሮ ነው።

ያ ተራና ግልጽ የሆነው የእግዚአብሔር ተግባር ምሕረት ነው፡ ይኽ ቅዱስ ዓመት ይኸንን እውነት ለየት ባለ መልኩ እንዲኖር አድርጓል። ይኽ ደግሞ የምሕረት ዓመት በመካከለኛይቱ ረፓብሊክ አፍሪቃ ቅዱስ በር በመክፈት ያስጀመሩበት ሊጡርጊያ ያረጋጥልናል። የህልውናና የከተሞቻችን ጥጋ ጥጉን የተዘነጋውን ማእከልነት የማይሰጠው እንዲማክል አድርጓል። በዚህ የምሕረት ዓመት ምክንያት ከ20 ሚሊዮን በላይ የሚገመቱ መንፈሳዊ ነጋድያን የቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስ በር አልፏል። ሆኖም ቅዱስ በር በሁሉም ሰበካዎች ቁምስናዎች አቢያተ ጸሎት ክፍት ሆኗል። ሁሉም ቅዱስ በሮች እኩል መሆናቸው ቅዱስ አባታችን አስገንዝቧል።

ሌላው አቢይ ትኵረት ያደረጉበትም ለአንድነት ታልሞ ከሌሎች አቢያተ ክርስቲያን ጋር የሚደረገው የጋራው ውይይት ነው፡ ከፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ በርጠለመዎስ ቀዳማዊ እና ከሌሎች የተለያዩ አቢያተ ክርስትያን የበላይ መፍሳዊ መሪዎች በዝክረ 500ኛው ዓመት የሉተር ህዳሴ ምክንያትም ወደ ስዊድን በመሄድ በበዓሉ በመሳተፍ ከሁልም የተለያዩ ሃማኖት መሪዎች ጋር በአሲዚ በመገናኘት የጋራ ውይይት የሚለው ጉዳይ ነው፡ እነዚህ የፈጸሙዋቸው ግኑኝነቶችና ሱታፌዎች በኢየሱስ የተገለጠው የእግዚአብሔር ፈቃድ ነው፡ ሁሉም አንድ እንዲሆኑ የሚለው የጌታ ቃል ያበከረ ተግባር ነው፡ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ራእይ ተመርቶ ቤተ ክርስቲያን የሚኖር የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይነት በቅዱስ አባታን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተግባር እየተመሰከረ ነው በማለት ያካሄዱት ቃለ ምልልስ አጠቃሏል።








All the contents on this site are copyrighted ©.